በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ኦህዴድ ሁለት ከፍተኛ አመራሮችን ከሃላፊነት አነሳ

ኢሳት (የካቲት 23 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል ዳግም የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሁለት ከፍተኛ አመራሮችን ከሃላፊነት አነሳ። በፓርቲው ውስጥ የተፈጠረውን የስልጣን ክፍተት ለመሙላትና ዳግም ባገረሸው ተቃውሞ ዙሪያ ለመምከርም ኦህዴድ በአዳማ ከተማ ከረቡዕ ጀምሮ የሚካሄድ አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱንም ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። የኦህዴድ ጽ/ቤት ሃላፊና የኢህአዴግ ስራ አስፋጻሚ የነበሩት አቶ ዳባ ደበሌና የፓርቲው የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርና የጸጥታ ...

Read More »

በወልድያ ከተማ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ

ኢሳት (የካቲት 23 ፥ 2008) በወልድያ ከተማ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ እያደረጉ እንደሆነ ከስፍራው የደረሰን ዜና አመለከተ። ከወሎ ወልዲያና ወደተለያዩ ከተሞች የሚደረገው የትራንስፖርት አገልግሎት እንደ ኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከ10 ሰዓት ጀምሮ መቋረጡን ለኢሳት የደረሰ መረጃ ያስረዳል። በአድማው ከአሽከርካሪዎች በተጨማሪ የተሽከርካሪ ባለንብረቶችም ተቀላቅለዋል ተብሏል። የመንግስት ካድሬዎች ሾፌሮችንና የተሽከርካሪ ባለቤቶችን እያስፈራራ ቢሆንም፣ ከባህርዳር ደብረታቦርም ጭምር አድማው ሊስፋፋ እንደሚችል እየተነገረ እንደሆነ ...

Read More »

በቅርቡ ኢትዮጵያን የሚጎበኙት ዲቪድ ካሜሩን የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ጉዳይ የመወያያ አጀንዳ እንደሚያደርጉት ታወቀ

ኢሳት (የካቲት 23 ፥ 2008) በቀጣዩ ወር በኢትዮጵያ ጉብኝት የሚያደርጉት የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን በጉብኝታቸው ወቅት የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ጉዳይ የመወያያ አጀንዳ እንደሚያደርጉት ተገለጠ። የብሪታኒያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተለያዩ አካላት የቀረበባቸውን ግፊት ግምት ውስጥ በማስገባት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫናን እንዲያደርጉ በማሳሰብ ላይ መሆናቸውም ታውቋል። በቀጣዩ ወር መጨረሻ ላይ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው የሚያደጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን 120ኛውን የአድዋ ድል አከበሩ

የካቲት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያ ፋሺስት ጣሊያንን ድባቅ የመታችበት የአድዋ ድል 120ኛ አመት በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጭ በሚኖሩ ዜጎች ተከብሯል። የአድዋን ድል በማስመልከት አርበኞች ግንቦት7 ባወጣው መግለጫ ፣ ሀገራችን ኢትዮጵያን ለመውረርና ህዝቧን በውርድትና በባርነት ለመግዛት የዘመተብንን የጣሊያንን ጦር አለምን ማስደነቅ ብቻ ሳይሆን የታሪክን አቅጣጫ ቀይሯል ብሎአል።አድዋ ሲነሳ ልንረሳው የማንችለው ነገር “በግር በፈረስ ከሀገራችን ልዩ ...

Read More »

የገዢው መንግስት አመራሮች ህብረተሰቡ የጦር መሳሪያ ግዥውን እንዲያቆም እየተማጸኑ ነው፡፡

የካቲት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ክልል አመራሮች በክልሉ ጠረፋማ ከተሞች በመዘዋወር ህብረተሰቡ አጠናክሮ የያዘውን የመሳሪያ ግዥ እንዲያቆም ሲማጸኑ ተሰምተዋል፡፡ ወጣቱ አመቱን ሙሉ በተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር የቀን ስራ በመስራትና ከእርሻ የሚያገኙትን ገቢ በቀጥታ ለጦር መሳሪያ ግዥ ማዋላቸው የገዢውን መንግስት አመራሮችን አሳስቧቸዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በመፋፋም ላይ ባለው ወቅታዊ ችግር ምክንያት በዜጎችና በመንግስት መካከል በሚታየው ፊት መዟዟር ...

Read More »

በኦህዴድ ውስጥ ሹም ሽሩ ቀጥሏል

የካቲት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ አንዱ ክንፍ የሆነው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ስራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት የኦሮሚያ ከልል አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ከሀላፊነታቸው ተነሱ። ምንጮቹን በመጥቀስ ሪፖርተር እንደዘገበው የክልሉ አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ኩቹ ከሀላፊነታቸው የተነሱት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ኦህዴድ በኦሮሚያ ክልል እየተነሳና ዳግም እያገረሻ የሚገኘውን የፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ ...

Read More »

የሰማያዊ ፓርቲ አደራጅ 7 አመት እስር ተፈረደበት

የካቲት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአርባ ምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አደራጅ የሆነው አቶ በፍቃዱ አበበ የ7 አመት እስር ቅጣት ተበየነበት፡፡ የካቲት 22/2008 ዓ.ም ከፍተኛው ፍ/ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት ቅጣቱን ያስተላለፈ አቶ በፍቃዱ ለግንቦት ሰባት ‹‹ሲያደራጅና ሲመለምል›› ነበር በሚል ነው። አቶ በፍቃዱ ‹‹አሁንም ሆነ፣ ወደፊት አሸባሪ አይደለሁም፡፡ ግፍ ተፈጽሞብኛል›› ሲል ችሎት ፊት ተናግሯል፡፡ የዕለቱ ዳኛ በበኩላቸው ‹‹ግፍ ...

Read More »

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም አስከባሪነት ከተሰማሩ አገራት ድሃ አገራት ከፍተኛውን ቁጥር መያዛቸውን ጥናቶች አረረጋገጡ።

የካቲት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው ዓለማት ግጭት ባለባቸው አገራት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር ሆነው በሰላም አስከባሪን ከተሰማሩ አገራት ውስጥ ከፍተኛውን የሰራዊት ድርሻ ካሰማሩ አገራት ተርታ ኢትዮጵያ በቀዳሚነት ተሰልፋለች። ጥናቱ እንደ አውሮፓዊያን ዘመን አቆጣጠር በ2016 ዓ.ም በሰላም አስከባሪ ጦር የተሰማሩ አገራትን ዝርዝር ጥናታዊ አሃዝ አውጥቷል። ኢትዮጵያ 8 ሽህ 326 ሰራዊት በማሰለፍ በቀዳሚነት ደረጃ ላይ ስትመደብ ...

Read More »

በአሜሪካ ሜሪላንድ ሞንትጎመሪ ካውንቲ የመጋቢት ወር የአድዋ ድል ወር ተብሎ እንዲከበር ወሰነ

ኢሳት (የካቲት 22 ፥ 2008) ኢትዮጵያውያን በህብረት ወራሪውን የጣሊያንን ጦር የደመሰሱበት የአድዋ ድል በዓል ወርሃ መጋቢት (ማርች) ተሰይሞለት የአድዋ ድል ወር ተብሎ ታሪኩ እየተወሳ እንዲከበር የአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት ምንትጎመሪ ካውንቲ በአዋጅ ወሰነ። መታሰቢያው የካቲት 23 ወይም ማርች 1,  120ኛው የአድዋ ድል እንዲከበር በመጥቀስ አጼ ምኒሊክና እቴጌ ጣይቱ የመሩት ጦር በወራሪው ጣሊያን ላይ የተቀዳጀው ድል ኢትዮጵያን ከቅኝ ግዛት ነጻ ያወጣት ሃገር ...

Read More »

በእስራዔል የወንጀል ምርመራ እንዲቋረጥ መደረግን ተከትሎ ተቃውሞ ተደረገ

ኢሳት (የካቲት 22 ፥ 2008) በእስራዔል ከአንድ ኢትዮጵያዊ ሞት ጋር በተያያዘ ሲካሄድ የነበረ የወንጀል ምርመራ ኣንዲቋረጥ መደረግን ተከትሎ በእየሩሳሌም የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ማክሰኞ ምሽት ተቃውሞ አደረጉ። በከተማዋ በሚገኘው የፖሊስ ዋና ጽ/ቤት ከተጀመረው ተቃውሞ በተገናኘ ስምንት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የእስራዔል መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የሃገሪቱ ፖሊስ በፀጥታ ሃይሎች በደል ተፈጽሞበት ራሱን ባጠፋው ዮሴፍ ሳላምሳ ላይ ሲያካሄድ የነበረውን የወንጀል ምርመራ ምክንያቱ ...

Read More »