የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት አያያዝ በተመለከ በጄኔቭ ውይይት ተካሄደ

የካቲት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከተለያዩ አለማቀፍና አገር በቀል የሲቪክ ድርጅቶች የተውጣጡ በኢትዮጵያ የሚታየውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በተመለከተ ድምጻቸውን የሚያሰሙ ድርጅቶች፣በአገሪቱ ስለሚፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት ገለጻ አድርገዋል። በለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት ዶ/ር አወል ቃሲም አሎ፣በኦሮምያ እና በአገሪቱ ስለሚታየው የሰብአዊ መብት ጥሰት ሰፊ ማብራሪያ አድርገዋል።በውይይቱ ላይ ከተገኙት መካከል ዶ/ር አወልንና ዶ/ር ተድላ ደስታን አነጋግረናቸዋል። ከዜናው ቀጥሎ ይቀርባል።