(ኢሳት ዲሲ–ጥር 27/2011)የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር በመጪው ረቡዕ በይፋ ትጥቅ ሊፈታ መሆኑ ተገለጸ። ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ግንባሩ ትጥቁን ፈትቶ በሰላማዊ መንገድ ትግሉን የሚቀጥለበትን አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር በዝግጅት ላይ ይገኛል። የግንባሩ ወታደሮች በአምስት ካምፖች እንደሚሰፍሩም የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በሌላ በኩል ለአራት ቀናት ቆይቶ የነበረው የሰዓት እላፊ ገደብ ትላንትና ማብቃቱን የሶማሌ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል። በጅጅጋ ባለፈው ሳምንት የሃይማኖት ግጭት ተከስቷል ...
Read More »የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ይከናወናል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 27/2011)የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዳይከናወን የሚያደርግ ስጋት የለም ሲል የማዕከላዊ ስታስቲክስ ባለስልጣን አስታወቀ። የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሳፊ ገመዴ ለኢሳት እንደገለጹት በሚቀጥሉት ሁለት ወራት የተፈናቀሉት በሙሉ ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ የሚደረግ በመሆኑ ቆጠራው ላይ የሚፈጠር ችግር አይኖርም። ከ1ሚሊዮን በላይ ተፈናቃይ የሚገኝባት ኢትዮጵያ ቆጠራውን ለማካሄድ የሰላምና የደህንነት ሁኔታው አስተማማኝ አይደለም የሚል ስጋት ከተለያዩ ወገኖች በሚሰጥበት በዚህን ወቅት ...
Read More »በደቡብ ጎንደር በመስጊድ ላይ የደረሰው ቃጠሎ ሰላምን በማይፈልጉ ሃይሎች የተፈጸመ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 27/2011)በደቡብ ጎንደር በመስጊድ ላይ የደረሰው ቃጠሎ ኢትዮጵያ ሰላም እንዳትሆን በሚፈልጉ አካላት የተፈጸመ መሆኑን የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን እሰቴ ከተማ ቀበሌ 03 ላይ ሁለት መስጊዶች መቃጠላቸው ታውቋል። የአማራ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ጸሃፊ ሼህ መሐመድ ሐሰን ድርጊቱ ለበርካታ ዘመናት በፍቅር የኖሩትን ህዝቦች ለማለያየት ያለመና ሁለቱንም ወገኖች የማይወክል ነው ብለዋል፡፡ ...
Read More »የቀዳማዊ ሃይለስላሴ ሃውልት በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊቆም ነው
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 24/2011)የቀዳማዊ ሃይለስላሴ ሃውልት በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊቆም መሆኑ ተገለጸ። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዛሬ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ መንግስት ሙሉ ወጪ የተቀረጸው ሀውልት የካቲት ወር መጀመሪያ ላይ ይቆማል። ከ6 ዓመት በፊት ለጋናዊው ታላቅ መሪ ኑዋሚ ንኩሩማ በአፍሪካ ህብረት ዋና ጽህፈት ቤት ውስጥ ሀውልት መቆሙ የሚታወስ ነው። የቀዳማዊ ሃይለስላሴ ሀውልት በወቅቱ ኑዋሚ ንኩሩማ ጋር እንዳይቆም የጊዜው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ...
Read More »ሌተናል ጀኔራል ጥጋቡ ይልማ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሃይል ሆነው ተሾሙ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 24/2011)ኢትዮጵያዊው ሌተናል ጀኔራል ጥጋቡ ይልማ ወንድማገኝ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሃይል (አሚሶም) አዛዥ በመሆን ተሾሙ። ሌተናል ጀኔራል ጥጋቡ ከዚህ ቀደም በቦታው ሲያገለግሉ የነበሩትን ዩጋንዳዊውን ሌተናል ጀኔራል ሲጊይሬን በመተካት ነው የተሾሙት። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሰላም በማስከበር አስተዋጽዖ መከላከያ ሰራዊቷ በተባበሩት መንግስታት ይደነቃል። ለዚሁም በላይቤሪያ፣ በሩዋንዳ፣ በሱዳንና በሶማሊያ ያደረገችው የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ለአብነት ይጠቀሳል። በዚሁ ሳቢያም ኢትዮጵያዊው ሌተናል ጀኔራል ጥጋቡ ...
Read More »ተማሪዎች ራሳቸውን ከፖለቲካ ነጋዴዎች መጠቀሚያነት ይጠብቁ ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 24/2011)ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጡ። የከፍተኛ ትምህር ተቋማት ተማሪዎች ራሳቸው ከፖለቲካ ነጋዴዎች መጠቀሚያነት እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በኢትዮጵያ ወንጀል ሰርቶ በመንግስትም ተረጋግጦ ያልታሰረ ሰው የለም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። የክልል ጥያቄ ህገመንግስታዊ ቢሆንም የክልል ስያሜ ማግኘት ብቻውን መፍትሄ አይሆንም ሲሉ ገልጸዋል። በቅርቡ የጸደቀው የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ኮሚሽን የተቋቋመው ክልል ለመሸንሸን አይደለም ብለዋል። ኮንትሮባንድ የኢትዮጵያን ...
Read More »በቴፒ ግጭት ከ10 በላይ ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 24/2011)በቴፒ በተቀሰቀሰው ግጭት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ10 በላይ መድረሱ ተነገረ። በአካባቢው በአዲስ ዓለም ቀበሌ በሸካ አመራሮች ተደራጅተዋል የተባሉና ጉርማሾ ተብለው የሚጠሩ ቡድኖች ጥይት ሲተኩሱ እንደነበር የአይን እማኞች ተናግረዋል። ይህንኑ ተከትሎም በደቡብ ልዩ ሃይል ከ10 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና በርካታዎቹም መቁሰላቸውን የአካባቢው ሰዎች ተናግረዋል። በቴፒ አካባቢ የተነሳው ግጭትን ለማብረድ መከላካያ ወደ አካባቢው ጣልቃ መግባቱ ተነግሯል። በአካባቢው በተነሳው ብሄር ተኮር ግጭት ...
Read More »በአፍሪካ ሙስናን መዋጋት ተስፋ አስቆራጭ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2011)በአፍሪካ ሙስናን ለመዋጋት የሚደረገው እንቅስቃሴ ተስፋ አስቆራጭ ነው ሲል ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። በሙስና ጉዳይ ላይ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ጥናት የሚያደርገው ተቋም ይፋ እንዳደረገው የአፍሪካ ሀገራት አሁንም በሙስና ግንባር ቀደም ሆነው ቀጥለዋል። በአለም አቀፍ ደረጃ ሙስና የተንሰራፋባቸው ሃገራት በአብዛኛው በአፍሪካ ይገኛሉ ብሏል ተቋሙ። ሶማሊያ ሙስና ስር የሰደደባት በመባል በቀዳሚነት ስትጠቀስ ደቡብ ሱዳን ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች። ቦትስዋናና ሲሼልስ አንጻራዊ መሻሻል ...
Read More »በሱዳን ሁለተኛ ወሩን ያስቆጠረው ተቃውሞ እንዲያበቃ ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2011)በሱዳን ሁለተኛ ወሩን ያስቆጠረው ተቃውሞ እንዲያበቃ የሐገሪቱ ጦር ሃይሎች ኢታማዦር ሹም አሳሰቡ። በሌላም በኩል የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሳዲቅ አልመሐዲ ልጅ ከተቃውሞው ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉች በኋላ መለቀቋ ተሰምቷል። መንግስት 30 ሰዎች እንደተገደሉ ባመነበትና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የገለጹበት ተቃውሞ 42ኛ ቀኑን አስቆጥሯል። በሱዳን የተጀመረው ተቃውሞ እየበረታ መቀጠሉ ያሳሰባቸው የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ጄኔራል ኡመር አልበሽር ተቃውሞውን ...
Read More »በእስራኤል የአንድ ኢትዮጵያዊ መገደልግጭት አስከተለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2011)በእስራኤል የአንድ ኢትዮጵያ መገደልን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ግጭት አስከተለ። ከሶስት ቀናት በፊት በቴለቪቭ በእስራኤል ፖሊስ ተተኮሶበት የተገደለው ኢትዮጵያዊ ጉዳይ በእስራዔል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ቁጣ ቀስቅሷል። ለሁለት ቀናት ሲደረግ የነበረው ተቃውሞ ከትላንት ምሽት ጀምሮ ወደ ግጭት መቀየሩንም ለማወቅ ተችሏል። በግጭቱ አምስት ኢትዮጵያውያን የተጎዱ ሲሆን ከእስራዔል ፖሊሶችም ጉዳት የደረሰባቸው እንዳሉ መረጃዎች ያመለክታሉ። ፖሊስ ዘጠኝ ኢትዮጵያውያንን ማሰሩም ታውቋል።
Read More »