በቴፒ ግጭት ከ10 በላይ ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 24/2011)በቴፒ በተቀሰቀሰው ግጭት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ10 በላይ መድረሱ ተነገረ።

በአካባቢው  በአዲስ  ዓለም  ቀበሌ   በሸካ አመራሮች  ተደራጅተዋል የተባሉና  ጉርማሾ ተብለው  የሚጠሩ  ቡድኖች  ጥይት ሲተኩሱ እንደነበር የአይን እማኞች ተናግረዋል።

ይህንኑ ተከትሎም በደቡብ ልዩ ሃይል ከ10 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና በርካታዎቹም መቁሰላቸውን የአካባቢው ሰዎች ተናግረዋል።

በቴፒ አካባቢ የተነሳው ግጭትን ለማብረድ መከላካያ ወደ አካባቢው ጣልቃ መግባቱ ተነግሯል።

በአካባቢው በተነሳው ብሄር ተኮር ግጭት ከ10 ሰዎች በላይ በልዩ ሃይል ተገድለዋል ከመባሉ በተጨማሪ ሁለት ሰዎችም በከባድ  ቆስለዋል ።

ሁለቱ  ሰዎች  በከባድ  ቆስለው  አማን ሆስፒታል  ሪፈር ተፅፎላቸዋል  በህክምና  ላይ እንደሚገኙም መረጃዎች አመለክተዋል ።ብዙ ቤቶችም  ተቃጥለዋል  ።

ከማሻና ከጌጫ ታጥቀው  የመጡ ቡድኖች  ጀምበሬ  በሚባለው  ቀበሌ  አንድ  ሴትና ወንድ  ገድለው  ተሰውረዋል ።

የቴፒ ወጣቶች  ከፀጥታ  ኃይሎች  ጋር  ተፋጠዋል ።  ግጭቱ የተቀሰቀሰው በሸክቾ እና  በቴፒ ተወላጆች  መካከል  መሆኑም ታውቋል።

የአካባቢው ወጣቶች የወረዳውን  ማረሚያ  ቤት  ሰብረው  የግፍ እስረኞችን አስፈትተዋል፣  በጥበቃ  ላይ የነበሩ  ሰባት  ፖሊሶችም  በወጣቶች  ተገድለዋል ነው የተባለው

ዛሬም ከእርምጭ ወደ ቴፒ የተደራጁ ሃይሎች ጥቃት ሊያደርሱ ሲመጡ ዝንኪ ቀበሌ ላይ ሶስቱ ተገድለው መገኘታቸው ነው የታወቀው።

የያዙት መታወቂያም የእርምጭ ቀበሌ ሲሆን የሸካ ብሔረሰብ ተወላጆች መሆናቸውም በመታወቂያው ላይ ሰፍሯል።

በአካባቢው  በአዲስ  ዓለም  ቀበሌ  በሸካ አመራሮች  ተደራጅተዋል የተባሉና  ጉርማሾ ተብለው  የሚጠሩ  ቡድኖች  ጥይት ሲተኩሱ ነበር ተብሏል። ከሰዓት  በኋላ  መሀመድ  ጅንሱ የተባለ ግለሰብ በሸካ ፖሊስ  በሽጉጥ  ተመቶ ሞቷል ።

በቴፒ የተቀሰቀሰው ግጭት በርካታ ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን እስካሁን ለችግሩ እልባት አለማስገኘቱ የአካባቢዎቹን ነዋሪዎች እያሳሰበ ይገኛል።