ሚያዚያ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በውጭ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ የህጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲኖዶስ በሚል መግለጫው የትንሳኤን በአል በማስመልከት ቃለ ቡራኬ ሰጠ ሲኖዶሱ ለኢሳት በላከው ቃለ ቡራኬ የትንሳኤ በአል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከምታከብራቸው አበይት የጌታ በአላት በታላቅነቱና በክብሩ የመጀመሪያውን ደረጃ የያዘ በአል መሆኑን አስታውሶ ፣ በትንሳኤው የክርስቲአኖች ህይወት ዋስትና ታውጇል፣ ሀሰተኞች የደረደሩት የሀሰት ክስ በሙሉ ተደምስሶ ሞትም ...
Read More »በትናንትናው እለት በአንዋር መስጊድ ሙስሊሞች ተቃውሞአቸውን አሰሙ
ሚያዚያ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እጅግ በርካታ ህዝብ በተገኘበት በዚሁ ስነስርአት ላይ ሙስሊሞቹ የአላህን ታላቅነት ሲያውጁ፣ መንግስት የአህባሽን አስተምህሮ ለማስፋፋት እና የመጅሊስ አመራሮችን ለመሾም የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አውግዘዋል። ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው ሙስሊሞች እንዳሉት መንግስት ለራሱ የሚመቹትን የመጅሊስ አመራሮች ለመሾም እየተንቀሳቀሰ መገኘቱ አበሳጭቶዋቸዋል። ዳውድ ይባላል፣ የ20 አመት ወጣት ነው። መንግስት ሙስሊሞች ላቀረቡት የመብት ጥያቄ ቀጥተኛ የሆነ መልስ ከመስጠት ጥያቄውን ለማድበስበስ መሞከሩን ...
Read More »መንግስት በአማራ ተወላጆች ላይ የወሰደውን እርምጃ ኦነግ አወገዘ
ሚያዚያ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር ባወጣው ጠንካራ መግለጫ የህወሀት አገዛዝ የአማራ ተወላጆች ከደቡብ ክልል እንዲወጡ ማድረጉ ፣ አገዛዙ ህዝብን ከህዝብ በማጋጨት የስልጣን እድሜውን ለማራዘም የሚጠቀምበት ስልት በመሆኑ ሊወገዝ ይገባል ብሎአል። የህወሀት አገዛዝ የአፋር፣ ጋምቤላ ፣ ደቡብና የ ኦሮሞ ተወላጆችን ከማፈናቀል አልፎ ክርስቲያኑን ከሙስሊሙ በማጋጨት የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ይሞክራል የሚለው ኦነግ፣ ...
Read More »ሰሜን ሱዳን የደቡብ ሱዳንን ጦር ለመውጋት ጦሯን መላኩዋ ተሰማ
ሚያዚያ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ከሳምንታት በፊት በደቡብ እና በሰሜን ሱዳን መንግስታት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተጥሶ ሁለቱ አገሮች ወደ ለየለት እና ደም አፋሳሽ ጦርነት እያመሩ መሆኑን የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት አስታውቀዋል። ሁለቱም ድርጅቶች መንግስታቱ የጦርነት ነጋሪት መጎሸማቸውን ትተው ለሰላም እድል እንዲሰጡ ቢወተውቱም፣ መንግስታቱ ግን የሚቀበሉት አልሆነም። ሰሜን ሱዳን የነዳጅ ጉድጓድ ...
Read More »የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በአል በመላው አገሪቱ ተከበረ
ሚያዚያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመላው አገሪቱ የሚገኙ ክርስቲያኖች ያዛሬውን የስቅለት በአል ያሳለፉት በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በመገኘት የስግደትና የጸሎት ስነስርአት በማድረግ ነው። ዘጋቢያችን ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው አንዳንድ ክርስቲያኖች እንዳሉት ቀኑ እየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች በሙሉ የከፈለውን እዳ በማስታወስ ምንጊዜም መልካም ማድረግ እንዳለብን የሚያስገነዘብ ነው ብለዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ከእለት ወደ እለት እየናረ የመጣው የኑሮ ውድነት እና የብር የመግዛት አቅም ...
Read More »ክብርት አና ጎሜዝ የስዊድን ጋዜጠኞች እንዳይፈቱ እንቅፋት ሆነዋል ተባለ
ሚያዚያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የስዊድን ጋዜጠኞችን ለማስፈታት የአውሮፓ ህብረት ወደ ኢትዮጵያ የላካቸው ሉዊስ ሚሸል፣ መለስ ዜናዊ ጋዜጠኞችን የማይፈታቸው በክብርት አና ጎሜዝ የተነሳ መሆኑን ለስራ ባልደረቦቻቸው መናገራቸውን ታማኝ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ለኢሳት ገልጠዋል። መለስ ዜናዊ ጋዜጠኞችን ለመፍታት ይፈልጋል፣ ነገር ግን በውይይታችን ወቅት ደጋግሞ የሚያነሳው ስለ ወ/ሮ አና ጎሜዝ ነው፤ እንደተረዳሁት ለጋዜጠኞቹ መፈታት እንቅፋት የሆነችው አና ጎሜዝ ናት በማለት መናገራቸው ...
Read More »አርሶአደሮች ለአባይ ግድብ መዋጮ እንዲያዋጡ በካድሬዎች እየተዋከቡ መሆኑን ገለጡ
ሚያዚያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የባህርዳር ዘጋቢያችን እንደገለጠው በማዳበሪያ እና በምርጥ ዘር እዳ እየተዋከበ የሚገኘው አርሶ አደሩ አሁን ደግሞ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ቦንድ እንዲገዛ በመታዘዙ ምሬቱን ገልጧል። አንድ አርሶ አደር እናደሉት 50 ኪሎ ማዳበሪያ 900 ብር፣ አንድ ኪሎ ምርጥ ዘር ደግሞ እስከ 250 ብር በመሸት ላይ ሲሆን፣ አርሶ አደሩ ይህንን እዳ ከፍሎ ሳይጨርስ በዚህ አንድ ወር ውስጥ ቦንድ ...
Read More »ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የ2012 የፔን የፅሁፍ ነፃነት አለምአቀፍ ተሸላሚ ሆነ
ሚያዚያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኒዉ ዮርክ ከተማ የሚገኘዉ የፔን አሜሪካ ማእከል በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነትና ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እንዲከበር በፅናት የሚታገለዉና ካለፈዉ መስከረም ወር 2011 ጀምሮ በመለስ መንግሰት በሽብርተኝነት ተከሶ በእስር ላይ የሚገኘዉ ጋዜጠኛና ፀሃፊ እስክንድር ነጋ የዘንድሮዉ የ2012 አለምአቀፍ የባርባራ ጎልድ-ስሚዝ ተሸላሚ እንዲሆን ወሰነ። የፀረ ሽብር ህጉ መንግሰት “ሽብርተኛ” በማለት የሚገምታቸዉን ቡድኖች “ያበረታታሉ” ወይንም “ የሞራል ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት በየወሩ 45ሺህ የቤት ሠራተኞችን ወደ ሳዑዲ እንደሚልክ ተገለፀ
ሚያዚያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሳዑዲ አረቢያ/ ጄዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚገኝ የዉስጥ አዋቂ ምንጭን በመጥቀስ በቀረበዉ በዚሁ መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ ሠራተኞቹን ለመላክ የሚያስችሏትን መሰናዶዎች በማድረግ ላይ እንደምትገኝ ተገልጿል። አሻ-አርክ አል አዉሳት ጋዜጣ እንደገለፀዉ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ኬንያን ጨምሮ ከአራት መንግስታት ጋር የቤት ሰራተኞችን ለመመልመል የጀመረዉ ስምምነት አጥጋቢ ባለመሆኑ ዉለታዉን ካቋረጠ በሁዋላ ኢትዮጵያዉያን የቤት ሰራተኞችን ለመቅጠር ያለዉ ፍላጎት ...
Read More »በደባርቅ ወረዳ የስራ ማቆም አድማ ያደረጉ 9 መምህራን ደሞዛቸውን ተቀጡ
ሚያዚያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ መምህራን እንደተናገሩት መንግስት የደሞዝ ጭማሪ እንዲያደርግ ለማስገደድ የስራ ማቆም አድማ አድርገው እንደነበረ አስታውሰው፣ ይሁን እንጅ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መንግስት የበቀል እርምጃ እየወሰደባቸው ነው። እርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል መምህርት ሀያት ሙሀመድ፣ መምህር ግርማ ሀይሌ፣ ደገፋው ዘላለም፣ አገር በለው ፣ ደስታ ገብረ እግዚአብሄር፣ አየለ መልካሙ እና ሌሎች ሶስት መምህራን የወር ደሞዛቸውን ተቀጥተዋል። ሰሞኑን ...
Read More »