የአልሸባብ ተዋጊዎች ሶማሊያን ለቀው ወደ ፑንትላንድ እየተጓዙ ነው ተባለ

ሚያዚያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቢቢሲ እንደዘገበው ተዋጊዎቹ ወደ ፑንትላንድ የተጓዙት ከኢትዮጵያ ፣ ከኬንያና ከአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ሀይል የሚሰነዘርባቸውን ጥቃት ለመከላከልና ራሳቸውን ለማደራጀት ነው። አልሸባብ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በእየ አቅጣጫው በሚሰነዘርበት ጥቃት እየተዳከመ መምጣቱ ይነገራል። የፑንትላንድ መንግስት የአልሸባብ ወደ ግዛቱ መግባት እንዳሳሰበው እየገለጠ ነው። እንደ ቢቢሲ ዘገባ ታዋጊዎቹ ወደ ፑንትላንድ ማምራታቸው በየመን ከሚገኘው የአልቃይዳ ሀይል ጋር በቀላሉ ለመገናኘት ...

Read More »

የአማራ ተወላጆች ከቤንች ማጂ ዞን እንዲወጡ ማዘዛቸው ኢህአዴግ ደቡቡንና አማራውን ለማጋጨት የቀየሰው ሴራ ነው ተባለ

  ሚያዚያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የአማራ ተወላጆች ከቤንች ማጂ ዞን እንዲወጡ ማዘዛቸው ኢህአዴግ ደቡቡንና አማራውን ለማጋጨት የቀየሰው ሴራ ነው ሲሉ የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ተወካይ ገለጡ የአንድነት ፓርቲ የምክር ቤት አባልና የደቡብ ተወካይ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሺበሺ ለኢሳት እንደተናገሩት በአቶ ሽፈራው ሽጉጤ የተጻፈው መመሪያ አንድን ብሄር ነጥሎ ለማጥቃት ያለመ ነው ኢህአዴግ ከዚህ ቀደም ሲያደርግ እንደነበረው ...

Read More »

እስክንድር ነጋና አንዱ አለም አራጌ የቪዲዮ ማስረጃቸውን አቀረቡ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቃቢ ህግ በእስር ላይ የሚገኙትን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና አንዱአለም አራጌን ሆን ብሎ ለመወንጀል የቪዲዮ ማስረጃዎችን ቆራርጦ አቅርቧል በማለት ተቃውሞአቸውን ሲያሰሙ የቆዩት እስረኞች ዛሬ ሙሉ ቪዲዮ በማቅርብ እንዲታይላቸው አድርገዋል። አቃቢ ህግ የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበሩት አቶ አንዱአለም አራጌ የመለስ መንግስት እንዲወገድ የአመጽ ጥሪ መቀስቀሳቸውን ያሳይልኛል ያለውን ቪዲዮ ቀደም ብሎ ...

Read More »

የሰሜን ሱዳን ፓርላማ አገሪቱ ደቡብ ሱዳንን ለመውጋት ሙሉ ዝግጅት እንድታደርግ ወሰነ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሰሜን ሱዳን ፓርላማ አገሪቱ ደቡብ ሱዳንን ለመውጋት ሙሉ ዝግጅት እንድታደርግ ወሰነ የኢትዮጵያ ጦር እጣ ፋንታ አልታወቀም ደቡብ ሱዳን ሰሞኑን ሄግሊግ እየተባለ የሚጠራውን ዋነኛ የነዳጅ ጉድጓዶችን ከሰሜን ሱዳን ማስለቀቁዋን፣ የሱዳን መንግስት ጦርም  ተሽንፎ አካባቢውን መልቀቁን የመገናኛ ብዙሀን ሲዘገቡ ሰንብተዋል። የሱዳን የመካላከያ ሚኒስትር የሆኑት አብደል ራሂም ሁሴን ለፓርላማው ያቀረቡትን ሪፖርት ተከትሎ ነው አገሪቱ ለሙሉ ጦርነት ...

Read More »

የኬንያው ምክትል አፈጉባኤ በኢትዮጵያው አምባሳደር ላይ ተሳለቁ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፋራህ ማሊም የተባሉት የኬንያ ፓርላማ ምክትል አፈጉባኤ ምጸታዊ ጽሁፋቸውን ያሰፈሩት በኬንያው ስታንዳርድ ጋዜጣ ላይ ነው። አፈ ጉበኤ ፋራህ ለትችታቸው መነሻ የሆናቸውም በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ሸምሰዲን ሮቤል እርሳቸው የሰጡትን ቃለምልልስ የሚተች ጽሁፍ በማውጣታቸው ነው። ምክትል አፈ ጉባኤው በጽሁፋቸው ” ኬንያ በአካባቢው ጠንካራ የሆነ ዲሞክራሲ ያላት አገር ስትሆን ኢትዮጵያ ደግሞ ተቃራኒውን ናት ” ካሉ ...

Read More »

ሜትረ አርቲስ አፈወርቅ ተክሌ አረፉ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ታዋቂው ሰአሊ ሜትረ አርቲስ አፈወርቅ ተክሌ በተወለዱ በ80 አመታቸው ማረፋቸውን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል። በሸዋ ክፍለ ሀገር አንኮበር ወረዳ የተወለዱት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ፣ በስእሉ አለም ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ብርቅ ልጆች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። አርቲስቱ በእኤአ በ1947 ኢንጂነሪነንግ ለመማር ወደ እንግሊዝ አገር  ቢላኩም ፣ በመጨረሻ ግን ስነ ስእል አጥንተው መመለሳቸው ታውቋል። አርቲስት አፈወርቅ በጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ህይወታቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር እየተበራከተ ነው

ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ በፍትህ ፣ በመልካም አስተዳዳር እጦት ና በችጋር ህይወታቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር እየተበራከተ ነው የኢሳት የክልል ወኪሎች አጠናክረው የላኩት መረጃ እንደሚያሳየው በተለይ በደቡብ ክልል ከማዳበሪያ እዳ ጋር በተያያዘ፣ በመልካም አስተዳዳር እጦትና የኑሮ ውድነቱን ለመቋቋም የተሳናቸው ዜጎች ራሳቸውን ማጥፋት እንዳማራጭ አድርገው እየተጠቀሙ ነው። በያዝነው ወር ብቻ በዳውሮ ዞን ውስጥ ሁለት አርሶአደሮች የማዳበሪያ እዳ መክፈል ...

Read More »

የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት በገዳሪፍ ጥቃት ይቅርታ ጠየቀ

ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት በገዳሪፍ አስተዳዳሪ ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ይቅርታ ጠየቀ በአርማጭሆ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጥቃቱን የፈጸሙት የገዳሪፍ አስተዳዳሪ የሆኑት ካርም አል አባስ ከአማራ ክልል ፐሬዚዳንት አያሌው ጎበዜ ጋር ለመነጋገር ወደ አካባቢው ሲያመሩ ነው። ኢሳት በትናንት ዜናው ጥቃት የተፈጸመባቸው የካርቱም አስተዳዳሪ መሆናቸውን ቢዘግብም ፣ ሱዳን ትሪቢዩን ዛሬ ይዞት በወጣው ዘገባ ግን አስተዳዳሪው የካርቱም ሳይሆን ...

Read More »

ቤይሩት ከ60 – 80ሺህ የሚገመቱ ኢትዮጵያዉያን ይኖራሉ ተባለ

ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሊባኖስ ቤይሩት ከ60-80ሺህ የሚገመቱ ኢትዮጵያዉያን ይኖራሉ ተባለ፣ ከነዚህ ዉስጥ ህጋዊ የሆኑት 43ሺህ ብቻ ናቸዉ በብሪታኒያ የሚታተመዉ ጋርዲያን ጋዜጣ ይህን የገለፀዉ በቅርቡ በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንሱላ ደጃፍ ላይ በአስቀጣሪዋ በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድባ ወደ አዕምሮ ህክምና ሆስፒታል ከተወሰደች በሁዋላ እራሷን ሰቅላ አጥፍታለች ስለተባለችዉ የሁለት ልጆች እናት ዓለም ደቻሳ ባወጣዉ ዘገባ ላይ ነዉ። የጋዜጣዉ ዝግጅት ክፍል በኢትዮጵያ ...

Read More »

200 የሚሆኑ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ሰራተኞችን ከስራ ሊያሰናብት ነው

ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢህአዴግ 200 የሚሆኑ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ሰራተኞችን ከስራ ሊያሰናብት መሆኑ ታወቀ ቢ ፒ አር እየተባለ በሚጠራዉ የመንግስት የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች የግምገማ ዉጤት መሰረት እንዲሰናበቱ የተወሰነባቸዉ ሰራተኞች በጥበቃ፤ በጥገናና በፅዳት ሙያ ለረዢም አመታት ሲያገለግሉ ከነበሩ የኤጀንሲዉ ሰራተኞች መካከል እንደሆኑ ተገልጿል። ከመካከላቸዉ የ15 አመት የስራ አገልግሎት ዘመን ያሏቸዉና አብዛኛዎቹ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የቤተሰብ ...

Read More »