ሜትረ አርቲስ አፈወርቅ ተክሌ አረፉ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ታዋቂው ሰአሊ ሜትረ አርቲስ አፈወርቅ ተክሌ በተወለዱ በ80 አመታቸው ማረፋቸውን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።

በሸዋ ክፍለ ሀገር አንኮበር ወረዳ የተወለዱት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ፣ በስእሉ አለም ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ብርቅ ልጆች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ።

አርቲስቱ በእኤአ በ1947 ኢንጂነሪነንግ ለመማር ወደ እንግሊዝ አገር  ቢላኩም ፣ በመጨረሻ ግን ስነ ስእል አጥንተው መመለሳቸው ታውቋል። አርቲስት አፈወርቅ በጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ፖርቱጋልና ግሪክ በሚገኙ የትምህርት ተቋማትም የስነ ጥበብ ትምህርት ተከታትለዋል።

የአርቲስ አፈወርቅ የመጀመሪያ አደባባይ ስራ ተደርጎ የሚወሰደው በአዲስ አበባ የሚገኘውን የቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴደራልን ያሳመረበት ነው። አርቲስቱ በአፍሪካ አንድነት ድርጅት መስታውቶች ላይ የሳላቸው አፍሪካን ሙቭመንት፣ አፍረካን አትሞስፌር፣ አፍሪካን ዩኒቲ፣ የሚባሉ ስእሎቹ ዘወትር ይታወሳሉ።

የአጼ ሀይለስላሴ የስነጥበብ ሽልማት የመጀመሪያው አሸናፊ የሆኑት አርቲስ አፈወርቅ ፣ በመኖሪያ ቤታቸው እጅግ ውብ የሆነ ሚዩዚየም አላቸው።

የቀብር ስነ ስርዓታቸው ቅዳሜ በ9 ሰዓት ቤተሰቦቻቸው፣ የሙያ አጋሮቻቸው፣ ወዳጅና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ለማወቅ ተችሎአል።

__________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide