የኬንያው ምክትል አፈጉባኤ በኢትዮጵያው አምባሳደር ላይ ተሳለቁ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ፋራህ ማሊም የተባሉት የኬንያ ፓርላማ ምክትል አፈጉባኤ ምጸታዊ ጽሁፋቸውን ያሰፈሩት በኬንያው ስታንዳርድ ጋዜጣ ላይ ነው። አፈ ጉበኤ ፋራህ ለትችታቸው መነሻ የሆናቸውም በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ሸምሰዲን ሮቤል እርሳቸው የሰጡትን ቃለምልልስ የሚተች ጽሁፍ በማውጣታቸው ነው።

ምክትል አፈ ጉባኤው በጽሁፋቸው ” ኬንያ በአካባቢው ጠንካራ የሆነ ዲሞክራሲ ያላት አገር ስትሆን ኢትዮጵያ ደግሞ ተቃራኒውን ናት ” ካሉ በሁዋላ በኬንያ ጠቅላይ ሚኒሰትሩም ይሁን ፕሬዚዳንቱ ወይም ሌላ ባለስልጣን ለሚሰራው ስራ ተጠያቂ ሲሆን ፣ በኢትዮጵያ ግን እንዲህ አይነቱ ነገር ፈጽሞ የሚታሰብ አይደለም” ብለዋል።

አፈጉባኤው አያይዘውም ” የኢትዮጵያው አምባሳደር ከአምባገነን አገዛዝ የመጡ በመሆናቸው የነጻ ዲሞክራሲ አሰራር ባይገባቸው አይገርም ” ብለዋል።

በኬንያ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ ይቻላል፣ በኢትዮጵያ ግን ሀሳባቸውን በነጻነት የሚገልጹት መጨረሻቸው መቃብር፣ ስደት ወይም እስር ቤት ይሆናል ያሉት አፈ ጉባኤው፣ ወደ ኬንያ የሚጎርፉት ስደተኞች በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ጨቋኝ ስርአት ለመሸሽ ብለው እንደሚያደርጉት ገልጠዋል። ዛሬ በኢትዮጵያ ከአማራ . ከትግራይና ከደቡብ በስተቀር ሁሉም ብሄረሰቦች ነጻ አውጭ እንዳላቸው ያስታወሱት አፈ ጉባኤው ፣ በአዲስ አበባ ያለው መንግስት ለውይይት በር መክፈት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

አምባሳደሩ ንግግሮችን በትክክል ለማዳመጥ ባለመቻላቸው ይቅርታ አደርግላቸዋለሁ ያሉት አፈጉባኤ ፋራህ፣ የኬንያ ጦር ሶማሊያን ለቆ መውጣት እንዳለበት ያቀረቡት አስተያየትን አምባሳደሩ አዛብተው እንደተረዱት ገልጠዋል።

__________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide