አርሶአደሮች ለአባይ ግድብ መዋጮ እንዲያዋጡ በካድሬዎች እየተዋከቡ መሆኑን ገለጡ

ሚያዚያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የባህርዳር ዘጋቢያችን እንደገለጠው በማዳበሪያ እና በምርጥ ዘር እዳ እየተዋከበ የሚገኘው አርሶ አደሩ አሁን ደግሞ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ቦንድ እንዲገዛ በመታዘዙ ምሬቱን ገልጧል። አንድ አርሶ አደር እናደሉት 50 ኪሎ ማዳበሪያ 900 ብር፣ አንድ ኪሎ ምርጥ ዘር ደግሞ እስከ 250 ብር በመሸት ላይ ሲሆን፣ አርሶ አደሩ ይህንን እዳ ከፍሎ ሳይጨርስ በዚህ አንድ ወር ውስጥ ቦንድ እንዲገዛ እዳ ተጥሎበታል ብለዋል።

በክልሉ ውስጥ የሚታየው ችጋር እንኳን ለተጨማሪ ወጪ ኑሮአችንም ለማሸነፍ አላስቻለንም ያሉት አርሶ አደሩ፣ መንግስት ካልራራልን በስተቀር አሁን በሚታየው ችጋር ብዙ ህዝብ ሊጎዳ ይችላል ሲል ስጋታቸውን ገልጠዋል። ከማዳበሪያ ዋጋ መጨመር ባሻገር የፍጆታ እቃዎች መጨመር የገበሬውን ኑሮ አስቻጋሪ እንዳደረገው፣ ገበሬውም በየጊዜው የሚንረውን ኑሮ ለመቆጣጠር ሲል በእህል ላይ ዋጋ ለመጨመር መገደዱን ፣ ይህን በተቃራኒው የከተማውን ኑሮ አስከፊ እንዳደረገው ገልጠዋል።

አቶ መለስ በቅርቡ አርሶ አደሩ የቦንድ ግዢ እንዲፈጽም ለማድረግ እየሰሩ መሆናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።

___________________________________________________________________________________________________ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide