ግንቦት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ትናንት “ጥቁር ሰው”የተሰኘውን አዲስ አልበም ክሊፕ በይፋ ባስመረቀበት ጊዜ ፦”ዳግማዊ ምኒልክ” የሚል ተጨማሪ አዲስ ነጠላ ዜማ አሰማ። በሂልተን ሂቴል በተካሄደው በዚሁ የምርቃት ሥነ ስርዓት ላይ ከ 700 በላይ ታዳሚዎች የተገኙ ሲሆን፤መድረኩን የመራው አንጋፋው አርቲስት ተስፋዬ ገሰሰ ነው። በዚህ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የደጃዝማች ባልቻ አባነፍሶ፣ የፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲኒግዴ ...
Read More »በኮልፌ ቀራኒዮ ወይራ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው በተነሳ ተቃውሞ ሰዎች ተገደሉ
ግንቦት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኮልፌ ቀራኒዮ ወይራ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ይዞታ ጋር ተያይዞ በተነሳ ተቃውሞ ሰዎች ተገደሉ የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጡት ግጭቱ የተከሰተው ቤተክርስቲያኑዋ ለትምህርት የምትገለገልበትን ቦታ መስተዳድሩ ለመንጠቅ ሙከራ በማድረጉ ነው። ምእመናኑ የመንግስትን እርምጃ መቃወማቸውን ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አባላት በወሰዱት እርምጃ በርካታ ሰዎች ሲቆስሉ አንድ ፖሊስ መሞቱም ታውቋል። ግጭቱን ተከትሎም በርካታ ምእመናን ...
Read More »በሰሜን ጎንደር ፍጥጫው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል
ግንቦት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከዋልድባ ገዳም ጋር በተያያዘ በሰሜን ጎንደር ህዝብና በመንግስት መካከል ያለው ፍጥጫ፣ ሊፈነዳ መቃረቡን ዘጋቢዎች ከስፍራው ገልጠዋል። የአካባቢው ህዝብ ስንቁን እየያዘ ወደጋዳሙ በመትመም ላይ ሲሆን፣ መንግስትም በደባርቅና አካባቢው በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የፌደራል ሰራዊቱን በትኖአል። አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ሰው፣ በህዝቡና በመንግስት መካከል ያለው ፍጥጫ በመጨመሩ ምናልባትም ሰኔ 21 ግጭት ሊፈጠር ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ...
Read More »ጎንደር ውስጥ የሁለት ሰዎች አስከሬን መሬት ላይ ተጎተተ
ግንቦት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሰሜን ጎንደር ዞን፣ ታች አርማጭሆ ወረዳ፣ በሳንጃ ከተማ ሸፍተዋል ተብለው በተኩስ ልውውጥ የተገደሉ ሁለት ሰዎች አስከሬን ለሦስት ሰዓታት ያህል መሬት ለመሬት እንዲጎተት ተደረገ። በድርጊቱ ያዘኑና ጮኸው ያለቀሱ የከተማው ነዋሪዎች በፖሊስ ቆመጥ ተደብድበዋል። እንደ ፍኖተ ነፃነት ዘገባ፤ ሸፍተዋል ተብለው በተኩስ ልውውጥ የተገደሉት የከተማው ነዋሪዎች አቶ ሸንኮና ከፍያለው እና አቶ ዳኛቸው አያሌው ናቸው። ነዋሪዎቹ ...
Read More »50 የኢትዮጵያ ወታደሮች መገደላቸው ተነገረ
ግንቦት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኦጋዴ ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ)፤ከ 50 በላይ የመንግስት ወታደሮችን ገደልኩ ማለቱን ቪኦኤ ዘገበ። ግንባሩ ጥቃቱን የፈፀመው፤ የ ኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት “ደቦች ሕሪሶ” በተባለ አካባቢ ባለፈው እሁድ ግንቦት 19 ቀን አድርሰውታል ላለው ጥቃት በወሰደው የበቀል እርምጃ ነው። ኦብነግ ባለፉት ሦስት ወራት ስድስት መኮንኖችን ጨምሮ በጠቅላላው 168 ወታደሮችን መግደሉን መግለጫው ያመለክታል። ባለፈው እሁድ ...
Read More »የደቡብ አፍሪካ ስታዲየም በተቃውሞ ድምጽ ተስተጋባ
ግንቦት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰሞኑን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ያደረገውን የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለመደገፍ ወደ ስታዲየም የገቡ በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የአቶ መለስ መንግስትን አጠንክረው መቃወማቸው ተዘገበ። በሺዎች የሚቆጠሩ በደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በጨዋታው ቦታ ተገኝተው ብሔራዊ ቡድናቸውን ለመደገፍ ወደ ደቡብ አፍሪካ-ሮያል ቦፎኬንግ ስታዲየም የተመሙት አረንጓዴ፣ቢጫና ቀይ ባንዲራቸውን እያውለበለቡ ነበር። ተቃውሞው የተጀመረው ...
Read More »በአፋር ክልል በተነሳ ግጭት ከ10 ያላነሱ ሰዎች ተገደሉ
ግንቦት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአካባቢው ተወላጆች ለኢሳት እንደተናገሩት ጥቃቱን የፈጸሙት በሶማሊ ክልል በሚደገፉ የኢሳ የልዩ ሀይል አባላት ናቸው። ትናንት ከጧቱ 12 ሰአት ላይ በመደበኛ ሁኔታ የታጠቁ ልዩ ሀይሎች 10 ሰዎችን መግደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት መንግስት ጥቃቱ ሲፈጸም ሊታደጋቸው አልቻለም (2፡45-03፡08)። ጥቃቱን የፈጸሙት ሀይሎች በሶማሊ ክልል እና በጂቡቲ መንግስት የሚደገፉ ልዩ የኢሳ ሀይል ታጣቂዎች መሆናቸውን የሚናገሩት ...
Read More »የሀሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዛሬም ትምህርት አልጀመሩም
ግንቦት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሃሮማያ /ዓለማያ/ ዩኒቨርስቲ በቴክኖሎጂ ፋኩሊቲ ውስጥ የሚገኘው “የወተር ኢንጂነሪንግ” ዲፓርትመንት የአራተኛ ዓመት ተማሪዎች ባነሱት አካዳሚክ ጥያቄ ሳቢያ ፌዴራል ፖሊስ ወደ ዶርማቸው ገብቶ ስለደበደባቸው በርካታ ተማሪዎች ተጎድተዋል፡፡ መብታቸውን የጠየቁ ተማሪዎች ለሁለት ቀናት የመመገቢያ ካርዳቸውን ተነጥቀው ምግብ እንዳያገኙ መደረጋቸውንና ዩኒቨርስቲው ሙሉ በሙሉ በፌዴራል ፖሊስ ጥበቃ ሥር እንደሚገኝ ተማሪዎች ለዘጋቢያችን ገልጸዋል፡፡ ተማሪዎቹ ” በሀገሪቱ ያሉ ...
Read More »መንግስት ዋልድባ ገዳምን ለማፈራረስ የጀመረውን ዘመቻ በመቃወም ሰልፍ ተደረገ
ግንቦት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሜልበርን መድሃኔዓለም ደብር አስተባባሪነት በተጠራው በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ለመገኘት ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ከተሰባሰበ በኋላ ወደ ፓርላማው ህንጻ አምርቷል። በፓርላማው ጽ/ቤት በመገኘትም መንግስት አለም አቀፍ እውቅና ያለውን የዋልድባ ገዳም ለማፍረስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እንዲያቆም ኢትዮጵያዊ ወገን የሚያደርገውን ጥረት የአውስትራሊያ መንግስት እንዲያግዝ የሚጠይቁ ልዩ ልዩ መፍክሮችን ሲያሰማ አርፍዷል። በሰልፉ ...
Read More »የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ግጥሚያውን ከደቡብ አፍሪካው “ባፋና ባፋና” ጋር ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያዬ
ግንቦት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ግጥሚያውን ከደቡብ አፍሪካው “ባፋና ባፋና” ጋር ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያዬ:: የሴት ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ከ 1000 ብር እስከ 2000 ብር ተሸለሙ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሜዳው ውጪ በመጫዎት ያገኘው ውጤት ብዙሀኑን የስፖርት ቤተሰብ አስደስቷል። በመጀመሪያው 45 ደቂቃ ክፍለ-ጊዜ ‘ባፋና ባፋናዎች’ አልፎ አልፎ ያደረጓቸው ...
Read More »