በኮልፌ ቀራኒዮ ወይራ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው በተነሳ ተቃውሞ ሰዎች ተገደሉ

ግንቦት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በኮልፌ ቀራኒዮ ወይራ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ይዞታ ጋር ተያይዞ በተነሳ ተቃውሞ ሰዎች ተገደሉ

የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጡት ግጭቱ የተከሰተው ቤተክርስቲያኑዋ ለትምህርት የምትገለገልበትን ቦታ መስተዳድሩ ለመንጠቅ ሙከራ በማድረጉ ነው። ምእመናኑ የመንግስትን እርምጃ መቃወማቸውን ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አባላት በወሰዱት እርምጃ በርካታ ሰዎች ሲቆስሉ አንድ ፖሊስ መሞቱም ታውቋል። ግጭቱን ተከትሎም በርካታ ምእመናን ከቤተክርስቲያኑዋ ቅጥር ግቢ እንዳይወጡ በፌደራል ፖሊስ ታግተው ነበር። ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎችም ታስረዋል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide