የቴዲ አፍሮ “ጥቁር ሰው”የተሰኘውን አዲስ አልበም ክሊፕ በይፋ ተመረቀ

ግንቦት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ትናንት “ጥቁር ሰው”የተሰኘውን አዲስ አልበም ክሊፕ በይፋ ባስመረቀበት ጊዜ ፦”ዳግማዊ ምኒልክ” የሚል ተጨማሪ አዲስ  ነጠላ ዜማ አሰማ።

በሂልተን ሂቴል በተካሄደው በዚሁ የምርቃት ሥነ ስርዓት ላይ ከ 700 በላይ ታዳሚዎች የተገኙ ሲሆን፤መድረኩን የመራው አንጋፋው አርቲስት ተስፋዬ ገሰሰ ነው።

በዚህ ፕሮግራም ላይ የተገኙት  የደጃዝማች ባልቻ አባነፍሶ፣ የፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲኒግዴ (አባመላ) እና የራስ መኮንን ቤተሰቦች ለቴዎድሮስ ያላቸውን አድናቆት ገልጸው የተለያዩ ስጦታዎችን አበርክተውለታል፡፡

ቴዲ፦”ዳግማዊ ምኒልክ የተሰኘውን አዲስ ነጠላ ዜማ ካሰማ በሁዋላ አርቲስት ስለሽ ደምሴ(ጋ ሽ አበራ ሞላ) አባይ የተሰኘ ሙዚቃ አሰምቷል።

አርቲስት አበበ ባልቻ በበኩሉ ከሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን “እሳት ወይ አበባ”መጽሐፍ ፦”አድዋ”የተሰኘውን ግጥም አሰምቷል።.

ከቅርብ ጊዜ በኩል በተከለይ የህወሀት አባላት  የአድዋን ታሪክ የሚያዛባ ታሪክ እያሳተሙ ባሉበት በአሁኑ ጊዜ ቴዎድሮስ ካሳሁን ስለ ዳግማዊ ምኒልክ ብልህ መሪነትና ስለ አድዋ ጀግኖች ውለታ በተደጋጋሚ ማቀንቀኑ ብዙሀኑን ኢትዮጵያውያን ማስደሰቱ ታውቋል።

በዚያው ልክ አንዳንድ የአገዛዙ ቁንጮዎች እንደተለመደው  አርቲስቱን እንዳይተናኮሉት  የሚለው ሥጋት በብዙዎች ዘንድ ይሰማል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide