የማእከላዊ ስታትስቲክስ ቢሮ የዋጋ ንረቱ በ3 በመቶ ቀንሷል ይላል ህዝቡ ግን አልተቀበለውም

ግንቦት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-መስሪያ ቤቱ ባወጣው አዲስ መረጃ የዋጋ ንረቱ ካለፈው ወር ጋር ሲነጣጠር የ3 ነጥብ 7 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል። የምግብ እህል ዋጋ በአንድ ወር ብቻ የ7 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን መስሪያ ቤቱ ገልጧል፡፡

የመስሪያ ቤቱን ሪፖርት ህዝቡ የሚቀበለው አልሆነም። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አሁንም የእህል ዋጋ ሲጨምር እንጅ ሲቀንስ አይታይም። ጤፍ በአማራ ክልል ከ1200 እስከ 1300 ብር በመሸጥ ላይ ነው። በአዲስ አበባም ባለፈው ወር ውስጥ ምንም አይነት ለውጥ ሳያሳይ ቀጥሎአል።

የኑሮ ውድነቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ዋነኛው የመነጋገሪያ አጀንዳ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ። በአንዳንድ አካባቢዎች የሚታየው የዝናብ እጥረት ከቀጠለ በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ የእህል ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር የሚል ስጋት አለ።

አለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት በኢትዮጵያ የሚታየው የዋጋ ንረት አሳሳቢ መሆኑን በተደጋጋሚ ይገልጧል። በያዝነው ወር ውስጥም የድርጅቱ ባለስልጣናት ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ይመክራሉ።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide