የጣት አሻራ መረጃን ለደህንነት ተግባር ለመጠቀም ታቅዷል

ሰኔ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጽያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥርን በጣት አሻራ ለማስደገፍ ባለፉት ሶስት ዓመታት እየሰበሰበ ያለውን በፎቶግራፍ የተደገፈ የአሻራ መረጃ ከታለመለት ዓላማ ውጪ ለአገሪቱ ደህንነት ተቋም ሥራ ለማዋል ዕቅድ መኖሩን አንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ ገለጹ፡፡ ባለሥልጣኑ በሐምሌ ወር 2001 ዓ.ም የጣት አሻራ መሰብሰብ ሲጀምር ታሳቢ አድርጎ የነበረው የታክስ ሥርዓቱን ...

Read More »

አቶ መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ በቅርቡ የነዳጅ ሀብት ባለቤት እንደምትሆን መናገራቸው ጠንከር ያለ ትችት አስከተለ

ሰኔ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዜናዊ በቅርቡ በአዲስ አበባ በተካሄደው የ አለም ኢኮኖሚ ፎረም ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ በቅርቡ የነዳጅ ሀብት ባለቤት እንደምትሆን መናገራቸው ጠንከር ያለ ትችት አስከተለ። የማዕድን ሚኒስትሯ በበኩላቸው የነዳጅ ዘይት ግኝት ሊረጋገጥ ሚችለው ነዳጁ ተቆፍሮ ሲወጣ ብቻ ነው በማለት የጠቅላይ ሚኒስትሩን  የችኮላ ንግግር ውድቅ አድርገውታል። “ከነዳጅ ዘይት ግኝቱ በፊት ወሬው ምነው ቀደመ?” በሚል ርዕስ  ...

Read More »

አቶ መለስ ዜናዊ የህክምና ምርመራ ለማድረግ ብራሰልስ ገቡ

ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዛሬ በቤልጂየም ዋና ከተማ ብራሰል የተገኙት በህክምና ቀጠሮዋቸው መሰረት ነው። በአእምሮ እጢ በሽታ እንደተጠቁ የሚነገርላቸው አቶ መለስ፣  ብራሰልስ የገቡት  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑትን አቶ ብርሀነ ገብረክርስቶስን አስከትለው መሆኑን ከኢምባሲ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። አምባሳደር ብርሀነ ከአቶ መለስ ጋር የመምጣታቸው ምክንያት ቀደም ሲል ለ10 አመታት ብራሰልስ በነበሩበት ወቅት የአቶ መለስን ህክምና ...

Read More »

በአፋር የተጀመረው ግጭት ቀጥሎ 8 ሰዎች ተገደሉ

ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዛሬው እለት የኢሳ ተወላጅ የሆኑ ልዩ  ሀይል የሚባሉት ታጣቂዎች 8 የአፋር ከብት አርቢዎችን  ገድለዋል። የአካባቢው ህዝብም በስጋትላይ መሆኑ ታውቋል ። የአፋር ህዝብ መሬቱ ለሸንኮራ አገዳ ተክል ይወሰደብኛል ብሎ እየሰጋ ባለበት ጊዜ  ጥቃት መፈጸሙ ችግራቸውን ይበልጥ እንዳወሳሰበባቸው ተወላጆች ይናገራሉ።፣ አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የአካባቢው ተወላጅ እንደተናገሩት በዛሬው እለት በ7 ላንድ ክሩዘር መኪና የመጡ የኢሳ ...

Read More »

የኢህአዴግ መንግሥት በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት (መጅሊስ) ምትክ የሚመረጠው አዲሱ መጅሊስ በቀበሌና በወረዳ በካድሬዎች ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ነው ተባለ

ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዑላማዎች ምክር ቤት በበላይነት ይመራዋል በተባለው የመጅሊስ ምርጫ በቀበሌና በወረዳ በመንግሥት መዋቅር የሚካሄድ ሲሆን የፌዴራል ጉዳዮች ጽ/ቤት በሚመድበው ቀጥተኛ በጀት ደግሞ ከሰኔ 13 እስከ ሰኔ 15 ቀን 2004 ዓ.ም የክልሎች የእስልምና ምክር ቤት (መጅሊስ) ይመረጣል።   ሰኔ 30 ቀን 2004 ዓ.ም ደግሞ የአዲስ አበባ እስልምና ምክር ቤት ምርጫ ይካሄዳል የሚል መርሃ- ግብር በመንግሥት በኩል ...

Read More »

ጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ ይግባኝ ጠየቀች

ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአቶ መለስ ዜናዊ መንግሥት አሸባሪ ተብላ 14 ዓመት ጽኑ እስራት የተፈረደባትና  33 ሺህ ብር የተቀጣችው ጋዜጠኛና መምህርት ርዮት ዓለሙ ከመንግሥት በኩል በተዘዋዋሪ የቀረበላትን የይቅርታ ጥያቄ ችላ ትናንት ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ አቤቱታ አቀረበች፡፡ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረበችው አቤቱታ ላይ ጋዜጠኛ ርዮት ምንም ዓይነት ወንጀል እንዳልሰራች ገልጣለች። ይልቁኑም መንግሥት በእርሷ ላይ ወንጀል መፈጸሙን፣ ...

Read More »

ለልማት የሄዱ ዲያስፖራዎች ፦”የመንግስት ያለህ!”እያሉ ነው

ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “የመንግስትን የልማት ጥሪ አምነን ወደ አገራችን  ከገባን በሁዋላ  በሙስና እየተንገላታንና እየተሰቃየን ነው” ሲሉ  ለሪል ስቴት ግንባታ   ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ያቀኑ  ዲያስፖራዎች  እሮሮ እያሰሙ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ  ዲያስፖራው ወደ አገሩ ገብቶ በኢንቨስትመንት አስንዲሳተፍ በተደጋጋሚ ጥሪ ሲያቀርቡ ሰምተን ነው ለዓመታት በምቾት ስንኖርባት አሜሪካ ለልማት ወደ አገራችን ያቀናነው ይላሉ-የ ጂ. ኤም.ኤ.ኤስ ሪል ስቴት አክስዮን ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት የአረብሳት ባለስልጣናትን ተማፀነ

ግንቦት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች ድምጾች በቴሌቪዥን የማያቀርብ ከሆነ ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚተላለፈውን ስርጭት የኢትዮጵያ መንግስት ለማቋረጥ ዝግጁ መሆኑን መግለጡ ታወቀ:: የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጡት የኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄውን ያቀረበው ለአረብሳት ነው።   መንግስት በመጀመሪያ በአረብ ሳት ሲተላለፍ የነበረውን  ኢሳትን ፣ ቀጥሎም የኤርትራን ቴሌቪዥን ለማፈን ሙከራ ማድረጉን ተከትሎ፣ ከአረብ ሳት ባለስልጣናት ጋር ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ...

Read More »

ሥራ ተቋራጮች ለህዳሴው ግድብ ቃል ከገቡት ውስጥ የሰጡት 10 በመቶውን ብቻ በመሆኑ መንግስት አቸኳይ ስብሰባ ጠራቸው

ግንቦት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በስብሰባው የተገኙት ተቋራጮች ፦”መንግስት ፕሮጀክቶችን ሁሉ ለቻይና እና ለጃፓን ተቋራጮች እየሰጠ ባለበት ሁኔታ መሥራት አልቻልንም” ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። በተለያዩ የኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ሥራ ተቋራጮች ለህዳሴው ግድብ ቃል ከገቡት 150 ሚሊዮን ብር ውስጥ እስካሁን የለገሱት 10 በመቶውን ማለትም 15 ሚሊዮን ብር ብቻ እንደሆነ   ተዘግቧል፡፡ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩና  በማኅበር የተደራጁ 1 ሺ 400 ተቋራጮች ...

Read More »

የማእከላዊ ስታትስቲክስ ቢሮ የዋጋ ንረቱ በ3 በመቶ ቀንሷል ይላል ህዝቡ ግን አልተቀበለውም

ግንቦት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መስሪያ ቤቱ ባወጣው አዲስ መረጃ የዋጋ ንረቱ ካለፈው ወር ጋር ሲነጣጠር የ3 ነጥብ 7 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል። የምግብ እህል ዋጋ በአንድ ወር ብቻ የ7 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን መስሪያ ቤቱ ገልጧል፡፡ የመስሪያ ቤቱን ሪፖርት ህዝቡ የሚቀበለው አልሆነም። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አሁንም የእህል ዋጋ ሲጨምር እንጅ ሲቀንስ አይታይም። ጤፍ በአማራ ክልል ከ1200 እስከ 1300 ...

Read More »