ሚያዚያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ያለፉትን ሳምንታት በከፍተኛ ጭንቅ ውስጥ ሆነው ያሳለፉት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ከማሺ ዞን የተፈናቀሉ አርሶአደሮች ወደ ቤታቸው ሲገቡ የተደበላለቀ ስሜት እንደፈጠረባቸው ለኢሳት ገልጸዋል። “ንብረት ቢወድም ይተካል፣ በህይወት ተርፈን ወደ ቤታችን በመግባታችን እግዝአብሄርን እና የተባበሩንን ሁሉ እናመሰግናለን፣ ደስ ብሎናል” በማለት አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ ይፈለጉ ተፈናቃይ ተናግረዋል። ሌላ ተፈናቃይም እንዲሁ ወደ ቤቱ ሲመለስ ደስታ እንደፈጠረበት ገልጾ፣ ሁኔታው ...
Read More »የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች እና የሲቪክ ተቋማት መንግስት በዜጎቹ ላይ የሚፈጽመውን ወንጀል እያወገዙ ነው
ሚያዚያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል ” የአማራ ህዝብ ስቃይ እንዲያበቃ ወያኔን መቅበር ይኖርብናል ” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ” ወያኔ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ያፈናቀላቸው አማሮች የመጀመሪያዎቹ የወያኔዎች የጥቃት ሰለባዎች አይደሉም። የመጨረሻዎቹም አይሆኑም። ወያኔ ከነ ጸረ አማራ ፖሊሲው በስልጣን እስካለ ድረስና በአማራ ስም አማራውን እያፈኑ፣ እየሰለሉ ከወያኔ ፍርፋሪ እየለቀሙ ለመኖር የቆረጡ ከአማራው መሃል የወጡ ከሃዲዎች አማራውን መቆጠጠር ...
Read More »የአፋር ከፍተኛ ባለስልጣናት ሽኩቻ ቀጥሎአል
ሚያዚያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከክልሉ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው የአብዴፓ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ከፕሬዚዳንቱ ከአቶ አሊ ሴሮ ጋር በፈጠሩት የፖለቲካ ውዝግብ ከስልጣን እንዲወርዱ ከተደረጉ በሁዋላ ከእርሳቸው ጀርባ በመሆን ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን ለማውረድ ይሰራሉ የተባሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ እና የትምህርት ቢሮ ሀላፊው አቶ አወል ወግሪስ ከስልጣን ተባረዋል። በግምገማው ወቅት አቶ አባይ ጸሀየ በስፍራው ተገኝተው ከአቶ አሊሴሮ ጋር በመቆም ፕሬዚዳንቱን ይቃወማሉ የተባሉትን ...
Read More »ከከማሺ ዞን የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ወደ ቀበሌያቸው ተመለሱ
ሚያዚያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ከከማሺ ዞን ተፈናቅለው በፍኖሰላም ከተማ ሰፍረው የቆዩት የአማራ ተወላጆች ያሶ ወረዳ ውስጥ በሚገኝ አንድ ጫካ ውስጥ እንዲሰፍሩ ከተደረጉ በሁዋላ ዛሬ አርብ ከሰአት በሁዋላ ወደ የቀበሌያቸው እንዲመለሱ መደረጉን ኢሳት ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች ገልጸዋል። ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ አብዛኛው ተፈናቃይ ወደ የቀበሌው የተጓዘ ሲሆን ቀሪዎቹም ወደ ቦታቸው ለመመለስ መኪና በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ...
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፍትህ ይሰጠን በማለት ተቃውሞ ሲያሰሙ ዋሉ
ሚያዚያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአርብ ስግደትን በማስከተል ከአንድ አመት በላይ ሲካሄድ የነበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን የመብታችን ይከበር ጥያቄ፣ በዚህ ሳምንት ” ፍትህ ፍትህ” በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል። በአዲስ አበባ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች “ፍትህ ” የሚል ጽሁፍ የያዙ ወረቀቶችን በመያዝ ፍትህን ሲጠይቁ የዋሉ ሲሆን፣ ፍትህ አጥተው በእስር ቤት የሚሰቃዩ መሪዎቻቸውን እጃቸውን በማጣመር በድጋሜ አስበዋቸዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ...
Read More »ኢህአዴግ “ሕዝቡ ለመምረጥ ላይወጣ ይችላል” በሚል ስጋት ውስጥ ገብቷል
ሚያዚያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ኢህአዴግ በመጪው እሁድ ብቻውን በሚወዳደርበት የአዲስአበባ እና የአካባቢ ምርጫ ላይ ለመምረጥ የተመዘገበው ሕዝብ ወጥቶ ላይመርጥ ይችላል በሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መውደቁን ምንጮቻንን ጠቆሙ፡፡ ከምርጫ በፊት ባሉት ችግሮች ላይ ውይይት እንዲቀድም በይፋ ያቀረቡት ጥያቄ በኢህአዴግና በኢህአዴግ መራሹ ምርጫ ቦርድ በኩል ተቀባይነት አለማግኘቱን ተከትሎ ከ28 በላይ ፓርቲዎች ራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን፣ የኢህአዴግ አጋር እንደሆነ የሚነገርለት ...
Read More »ሲአን አባሎቹ በመገደላቸውና በመታሰራቸው ከእሁዱ ምርጫ ራሱን ማግለሉን አስታወቀ
ሚያዚያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ ለኢሳት እንደገለጡት ከ787 በላይ አባሎቻቸው በመታሰራቸውንና ባለፈው ሳምንት በዳሌ ወረዳ እጩ ተወዳዳሪው ተሾመ ካሰና የሚባል ሰው ተገድሎ በመገኘቱ እንዲሁም የሲአን አባላትን ማዋከብ፣ ከስራ ማፈናቀል እና ተማሪዎችን ማባረሩ በመቀጠሉ ድርጅቱ ራሱን ለማግለል መወሰኑን ዋና ጸሀፊው አቶ ለገሰ ላንቃሞ ተናግረዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት በአካባቢው ተሰማርተው በድርጅቱ አባሎች ላይ ወከባ እየፈጸሙ መሆኑን ...
Read More »ወደ ቤንቺ ማጅ ዞን የተመለሱ የአማራ ተወላጆች ጫካ ውስጥ ወድቀናል ይላሉ
ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከቤንሻነጉል ጉሙዝ ከከማሺ ዞን ከያሶ ወረዳ ተፈናቅለው ፍኖተሰላም ከተማ ሰፍረው የነበሩት የአማራ ተወላጆች ወደ መጡበት ቦታ እንዲመለሱ ቢደረጉም፣ መጠለያ እና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ነገሮች ባልተሟሉበት ጫካ ውስጥ እንዲሰፍሩ መደረጋቸውን በቦታው ደርሰው ያነጋገርናቸው ተፈናቃዮች ገልጸዋል። ተፈናቃዮቹ ህጻናቱም ሆኑ አዋቂዎች ምግብ ሳይመገቡ መዋላቸውን፣ ከአንድ ቀን በሁዋላ ዱቄት ተሰፍሮ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል። የቀይ መስቀል ሰራተኞች አብረዋቸው እንደመጡ ...
Read More »የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዚዳንት መግለጫ አነጋጋሪ ሆኗል
ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አህመድ ናስር የአማራ ተወላጆችን ለመመለስ የክልላቸው ካቢኔ መወሰኑን በሚመለከት በአገር ቤት ለሚታተሙ ጋዜጦች እና ለኢሳት የሰጡት መግለጫ በተለይ በአዲስአበባ ከተማ አነጋጋሪነቱን ቀጥሎአል፡፡ “የተፈጠረ ስህተት አምኖ ይቅርታ በመጠየቅ ለማረም መንቀሳቀስ ተገቢ እርምጃ ነው” በሚል ሒደቱን አንዳንድ ምሁራን ያደነቁ ሲሆን ሌሎች ደግሞ “እርምጃው የጭንቅት ውጤት ነው” በማለት አጣጥለውታል፡፡ እነዚሁ ምሁራን ...
Read More »በኢትዮጵያ አይሁዶች ላይ ድብደባ የፈጸሙ 5 አይሁዶች ተያዙ
ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጀሩሳሌም ፖስት እንደዘገበው ኢትዮጵያውያንን በመደብደብ የተለያዩ ንብረቶችን የወሰዱ እ5 አይሁዶች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው። አንድ ወጣት ራሱ ላይ በመመታቱ ሆስፒታል ገብቶ እንደነበር የገለጠው ዘገባው፣ ሌሎች ሁለት ኢትዮጵያውያንም ቀላል የሚባል ጥቃት ድርሶባቸዋል ብሎአል። በቴሌላቪቭ የሚኖሩ አፍሪካዊያን ተደጋጋሚ ጥቃት እንደሚደርስባቸው ጋዜጣው ዘግባል።
Read More »