በኢትዮጵያ አይሁዶች ላይ ድብደባ የፈጸሙ 5 አይሁዶች ተያዙ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ጀሩሳሌም ፖስት እንደዘገበው ኢትዮጵያውያንን በመደብደብ የተለያዩ ንብረቶችን የወሰዱ እ5 አይሁዶች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው።
አንድ ወጣት ራሱ ላይ በመመታቱ ሆስፒታል ገብቶ እንደነበር የገለጠው ዘገባው፣ ሌሎች ሁለት ኢትዮጵያውያንም ቀላል የሚባል ጥቃት ድርሶባቸዋል ብሎአል።
በቴሌላቪቭ የሚኖሩ አፍሪካዊያን ተደጋጋሚ ጥቃት እንደሚደርስባቸው ጋዜጣው ዘግባል።