የአፋር ከፍተኛ ባለስልጣናት ሽኩቻ ቀጥሎአል

ሚያዚያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ከክልሉ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው የአብዴፓ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ከፕሬዚዳንቱ ከአቶ አሊ ሴሮ ጋር በፈጠሩት የፖለቲካ ውዝግብ ከስልጣን እንዲወርዱ  ከተደረጉ በሁዋላ ከእርሳቸው ጀርባ በመሆን ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን ለማውረድ ይሰራሉ የተባሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ እና የትምህርት ቢሮ ሀላፊው  አቶ አወል ወግሪስ ከስልጣን ተባረዋል።

በግምገማው ወቅት አቶ አባይ ጸሀየ በስፍራው ተገኝተው  ከአቶ አሊሴሮ ጋር በመቆም ፕሬዚዳንቱን ይቃወማሉ የተባሉትን ባለስልጣናት እንዲባረሩ አድርገዋል።

ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ አወል ወገሪስ ማስተሰርስ ዲግሪ የነበራቸው ናቸው። ፕሬዘዳንቱ አቶ አሊ ሴሮ በበኩላቸው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አልጨረሱም።

አቶ አሊ ሴሮ ላለፉት 17 አመታት በስልጣን ላይ ቢቆዩም፣ የክልሉ ህዝብ ሲፈናቀልና በህወሀት መራሹ መንግስት ከፍተኛ በደል ሲደርስበት እርምጃ አልወሰዱም በሚል ከውስጣቸው ተቃውሞ ተነስቶባቸው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።