ግንቦት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰማያዊ ፓርቲ በሚቀጥለው እሁድ በጠራው ህዝባዊ ሰልፍ ላይ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ እንደሚሳተፍ አስታወቀ። የፓርቲው ተቀዳሚ ም/ል ሊቀመንበር አቶ ወንድማገኝ ደነቀ ከኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ሰልፉ መደረጉን መደገፍና ማበረታታት ብቻ ሳይሆን ተከታታይነት እንዲኖረው ቅስቀሳ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።= የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት ህዝቡ ለሰላማዊ ሰልፉ በነቂስ እንዲወጣ መልእክት ...
Read More »የአፋር ክልል ፕሬዚዳንት ታመው በጀርመን ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው
ግንቦት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ባለስልጣናት ከፍተኛ ቀረቤታ በማሳየት በአፋር ተወላጆች ዘንድ ከፍተኛ ትችት የሚቀርብባቸው አቶ ኢስማኤል አሊሰሮ በጀርመን ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው። በህወሀት የደህንነት ሰዎች ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግላቸው አቶ እስማኤል ጤናቸው እየተሻሻለ መምጣቱን ለኢሳት ተናግረዋል። ” ተሽሎኛል፣ ጥሩ ህክምናም እያገኘሁ ነው፣ አላህ ከፈቀደ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ልመለስ እችላለሁ በማለት” ፕሬዚዳንቱ አክለዋል። ፕሬዚዳንቱን ...
Read More »ኢህአዴግ በአማራ ክልል ሹሞች ላይ ጥብቅ ግምገማ እያካሄደ ነው
ግንቦት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከብአዴን ያገኘነው መረጃ እንደሚጠቁመው በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች የመገናኛ ብዙሀን ሽፋን እንዳይሰጡት በተደረገበት ሁኔታ ከግንቦት19 ጀምሮ ግምገማ እየተካሄደ ነው። የግምገማው ዋና አላማ ኢህአዲግ በትጥቅ ትግል እንዲወድቅ አልመው ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅት አባላት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ የሚጠረጠሩ ባለስልጣናትን ሰበብ በመፍጠር ለማውረድና ለመምታት ያቀደ ነው ተብሎአል። በአብዛኞቹ ግምገማዎች ላይ ከፍተኛ ውጥረት መኖሩንም የደረሰን ...
Read More »የኢትዮጵያ ማአድን ልማት አክሲዮን ማህበር የተቋረጠውን የታንታለም ምርት ለመጀመር ፈቃድ ጠየቀ
ግንቦት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር እንደዘገበው የኢትዮጵያ ማዕድን ልማት አክሲዮን ማኅበር ከአንድ ዓመት በፊት ያቋረጠውን የታንታለም ኮንሰንትሬት የማምረት ሒደት ለመቀጠል የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲን ፈቃድ ጠይቋል። በኦሮሚያ ጉጂ ዞን ሰባቦሩ ወረዳ ቀንጢጫ በተባለ አካባቢ ከ1982 ዓ.ም. ጀምሮ የታንታለም ኮንሰንትሬት ሲመረት ቢቆይም፣ ጥሬ ምርት ከመላክ እሴት በመጨመር የተለያዩ የታንታለም ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ የተሻለ የውጪ ...
Read More »አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አዲስ ክብረ-ወሰን በማስመዝገብ አሸነፈች
ግንቦት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው እሁድ እንግሊዝ ውስጥ ማንችስተር ከተማ ላይ በተደረገው ዓመታዊ የሩጫ ውድድር፤ ዝነኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በአስደናቂ ብቃት የዓለምን የ10 ኪሎ ሜትር ክብረወሰን በማሻሻል ማሸነፏ ታወቀ። እስከ አምስት ኪሎሜትር ድረስ ያለውን ርቀት ከኋላ ሆና ስትሮጥ የነበረችው ጥሩነሽ፣ ከዚህ በኋላ ግን ድንገት አፈትልካ በመውጣት ቀሪውን አምስት ኪሎሜትር ውድድሩን በመምራት ነበር ያጠናቀቀችው። አትሌት ...
Read More »የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በገንዘብ የአለማችን ሀብታም ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን የበቁ መሆናቸው ተዘገበ
ግንቦት ፲፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ዘ ሪቸስት ዳት ኦርግ” የተሰኘው ድረ-ገፅ ይፋ እንዳደረገው፤ የቀድሞው ጠ/ ሚ/ር መለስ ዜናዊ የ3 ቢሊዮን ዶላር ባለቤት በመሆን ነው ከዓለማችን ፖለቲከኞች የሁለተኛ ደረጃን የያዙት። “ዘ ሪቸስት” የተሰኘው ይህ ድረ-ገፅ፤ በአንደኛ ደረጃ ባለፀጋ ሲል ያሰፈራቸው የቀድሞውን የጣሊያን ጠ/ሚ/ር ሲልቪዮ በርሎስኮኒን ሲሆን አንደኛ ደረጃ ያስቀመጣቸውን የ5.9 ቢሊዮን ዶላር ያፈሩት ከፖለቲካው መድረክ ሳይሆን በሜዲያው መስክ ከተሰማሩበት ...
Read More »የእንግሊዝ መንግሥት ለመክሰስ ጠበቃ መቅጠሩን አንድ ኢትዮጵያዊ አስታወቀ
ግንቦት ፲፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀል ምክንያት የሆነውን የኢትዮጵያ የመሬት ፖሊሲ የሚደግፍ 1.3 ቢሊዮን ዩሮ የሰጠውን የእንግሊዝ መንግሥት ለመክሰስ ጠበቃ መቅጠሩን አንድ ኢትዮጵያዊ አስታወቀ። ሚስተር “ኦ” በሚል ስያሜ በዋሽንግተን ፖስት ላይ ስሙ የሰፈረው ይህ ኢትዮጵያዊ፤ የብሪታኒያ ዓለም-ዐቀፍ የልማት አገልግሎትን ከቤት ንብረታቸው በተፈናቀሉት አራት ሚሊዮን በሚሆኑት ደሀ ኢትዮጵያውያን ስም እፋረዳለሁ ሲል አስታውቋል። ለም ከሆነውና የዘሩት ሁሉ ...
Read More »በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ የፓርቲ አባላት ሆኑ ሕዝቡ ሊሳተፍ ይገባል አሉ
ግንቦት ፲፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- መኢአድ ደግሞ በዚህ በቀሩት ጥቂት ቀናት በ33 ፓርቲ ተመክሮበት ከተስማማን ቅስቀሳ አድርገን ሕዝቡን በስፋት እናሳትፋለን ብሏል። ዛሬ ከኢሳት ጋር ቃል የተመላለሱት የ33 ፓርቲዎች የጋራ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ አቶ ግርማ በቀለ በሰልፉ ላይ በጋራ አባላትንም ሆነ ሕዝቡን ለማሳተፍ ለመወሰን ነገ የሥራ አስፈፃሚ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተናል ብለዋል። ሰልፉ በመንግሥት ላይ ያለውን ተቃውሞ በመግለፅ ለትግሉ አንድ ...
Read More »በፀጋው ታደለ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ስለኔ የተናገሩት ከራሳቸው ጋር አነፃጽረውኝ በመሆኑ ክብር ተሰምቶኛል አለ
ኢትዮጵያዊው በፀጋው ታደለ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ስለኔ የተናገሩት ከራሳቸው ጋር አነፃጽረውኝ በመሆኑ ክብር ተሰምቶኛል አለ ግንቦት ፲፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የሞር ሃውስ የ2013 የኮምፒዩተር ሳይንስ ተመራቂ በፀጋው ታደለ አስቂኝ ስም ያለውና ቀጭኑ ሰው ሲሉ በንግግራቸው የጠቀሱት የሳቸው ሰእምም ለአሜሪካኖች እንግዳ (አስቸጋሪ) በመሆኑና በተማሪነታቸው ጊዜ ቀጭኑ ኦባማ ይባሉ እንደነበር ስላነበብኩ እኔንም ከዚህ ማንነታቸው ጋር እንዳመሳሰሉኝ ስለምቆጥረው ኮርቼበታለሁ ብሏል። በሞር ...
Read More »የአባይ ወንዝ ቅየሳ የግንቦት20 በአል ማድመቂያ ሆኖ ዋለ
ግንቦት ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት የአባይን ወንዝ አቅጣጫ በማስቀየስ የግንቦት20 በአልን ሲያከብር ቢውልም ሰራተኞች ግን ስራው ለበአል ተብሎ በይድረስ ይድረስ እንደሰራ በመደረጉ የታቀደው አልተሳካም ይላሉ። መንግስት የግንቦት20 በአልን አባይን የፍሰት አቅጣጫ በማስቀየር ለማክበር ማቀዱን በዚህም የኢትዮጵያን ህዝብ ለማስደመም ወይም በእንግሊዝኛው አጣራር ሰርፕራይዝ ለማድረግ ማቀዱን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል። ዛሬ ግድቡ በሚሰራበት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት ...
Read More »