መኢአድ እሁድ የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደግፍና እንደሚያስተባብር አስታወቀ

ግንቦት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ሰማያዊ ፓርቲ በሚቀጥለው እሁድ በጠራው ህዝባዊ ሰልፍ ላይ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ እንደሚሳተፍ አስታወቀ።

 የፓርቲው ተቀዳሚ ም/ል ሊቀመንበር አቶ ወንድማገኝ ደነቀ  ከኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ጋር  ባደረጉት ቃለምልልስ ሰልፉ መደረጉን መደገፍና ማበረታታት ብቻ ሳይሆን ተከታታይነት እንዲኖረው ቅስቀሳ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።=  

 የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት ህዝቡ ለሰላማዊ ሰልፉ በነቂስ እንዲወጣ መልእክት እያስተላለፉ ነው። ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉን በተመለከተ ሰፊ ዘገባ ዛሬ በኢሳት ራዲዮ ይቀርባል።

 ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰልፍ በመንግስት እውቅና ተሰጥቶታል። በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እንደሚሳተፉበት ከወዲሁ ግምቶች እየቀረቡ ነው።