የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ኮሚቴ መንግስት ለሱዳን አሳልፎ የሰጠው እጅግ ሰፊ መሬት ህገወጥ ነው አለ

ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የድንበሩ ኮሚቴ ከፍተኛ አካል የሆነው ምክር ቤት ግንቦት 10 እና 11 ቀን 2005 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ጠበብቶች የተሳተፉበት ታላቅ ጉባዔ በሲሊቨር ስፕሪንግ ከተማ፣ ሜሪላንድ፣ አሜሪካ  አካሂዶ ባወጣው መግለጫ የሻለቃ ቻርልስ ጉዊን ድንበር ከለላ መሥመር ሕገወጥ መሆኑን በተጨባጭ ውድቅ አድርጓል።   መንግስት ለሱዳን በስጦታ ያስረከበው ዳር- ድንበራችን የኢትዮጵያ መሬት መሆኑን የገለጸው  ኮሚቴው ፣ ...

Read More »

ጆን ኬሪ ለአፍሪካ ህብረት 50ኛ አመት በአል ለመገኘት አዲስ አበባ ገቡ

ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ጆን ኬሪ በአዲስ አበባ ከጠቅላይ ሚኒሰትር ሀይለማርያም ጋር ተወያይተዋል። ኬሪ በኢትዮጵያ በሚታየው ሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዙሪአ ከአቶ ሀይለማርያም ጋር ስለመነጋገራቸው የተገለጸ ነገር ይለም። ባለስልጣኑ የኢህአዴግ መንግስት የህዝብን መብቶች እንዲያከብር ግፊት እንዲያደርጉ የተለያዩ አለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ሲወተውቱ  ከርመዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ 50ኛው አመት የአፍሪካ ህብረት በአል በሚከበርበት ...

Read More »

በደሴ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በፌደራል ፖሊሶች ተደበደቡ

ግንቦት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዘወትር አርብ የጁመዓን ስግደት ተከትሎ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ” ድምጻችን ይሰማ” በማለት የሚያቀርቡት ተቃውሞ ከአዲስ አበባ ውጭ የተካሄደ ሲሆን  በደሴ ሸዋ በር መስጂድ የተካሄደው ተቃውሞ በጸጥታ ሀይሎች እንዲበተን ተደርጓል። የፌደራል ፖሊስ አባላት በወሰዱት እርምጃም ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶች ተደብድበዋል። አንዳንድ ወጣቶች በጽኑ ቆስለው ሆስፒታል መግባታቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶችም ታፍሰው በመኪና ...

Read More »

ኢህአዴግ ግንቦት 20ን የአባይን ወንዝ አቅጣጫ በማስቀየር ሊያከብር ነው

ግንቦት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ኢህአዴግ አዲስአበባን የተቆጣጠረበትን 22ኛ ዓመት ክብረበአል የአባይን ግድብ አቅጣጫ በማስቀየር ለማክበር በዝግጅት ላይ መሆኑን የኢህአዴግ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። ስነስርዓቱ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በጉባ ከተማ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በሚገኙበት እንደሚካሄድ ታውቋል። ኢህአዴግ የወንዙን አቅጣጫ በማስቀየር የኢትዮጵያን ህዝብ በእለቱ ለማስደመም ማቀዱን ለማወቅ ተችሎአል። የወንዙን አቅጣጫ የማስቀየር ሥራ ክንውን አስመልክቶም የፊታችን ሰኞ ግንቦት 19/2005 ...

Read More »

የኡራዔል አካባቢ ነጋዴዎች ሱቆቻቸው ከታሸጉ አራት ወራት መቁጠሩን ተናገሩ

ግንቦት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ በተለምዶ ኡራኤል ተብሎ በሚጠራው ቂርቆስ ክፍለከተማ በአሁኑ አጠራር ወረዳ 8 የንግድ ክልል ውስጥ የሚገኙ ነጋዴዎች የመስሪያ ቦታቸውን ሕይወት ብርሃን ለተባለ ቤተክርስቲያን በአስቸኳይ ለቀው እንዲያስረክቡ መገደዳቸውን ባለመቀበላቸው ሱቆቻቸው በክፍለከተማው ከታሸጉ አራት ወራት እንደሞላው በምሬት ገለጹ፡፡ በአካባቢው የኮንስትራክሽን የፋብሪካ ውጤቶች በችርቻሮና በጅምላ የሚቀርብበትና ከፍተኛ ግብር ከፋይ የንግዱ ኀብረተሰብ አባላትን ያቀፈ አካባቢ ነው። ...

Read More »

ሰማያዊ ፓርቲ በማንኛውም መልኩ ሰልፉን ለማካሄድ መወሰኑን አስታወቀ

ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጀነር ይልቃል ጌትነት ትናንት ለኢሳት ሬዲዮ እንደገለጹት የፓርቲው አመራሮች የፈቃድ ደብዳቤ ለማስገባት ወደ አዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት የሰላማዊ ሰልፍና የህዝባዊ ስብሰባ ማስታወቂያ ቢሮ ቢሄዱም ሃላፊዎቹ ደብዳቤውን ለመቀበል ፈቀደኛ አልሆኑም። ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የቢሮ ሀላፊ ደብዳቤ አልቀበልም በማለታቸው የፓርቲው አመራሮች ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉ ከከንቲባው ጽህፈት ቤት ሀላፊ እሰከ ...

Read More »

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው አፈና ቀጥሏል አለ

ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለሰብአዊ መብቶች መከበር በመሟገት አለማቀፍ እውቅና ያለው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይፋ ባደረገው የዚህ አመት ሪፖርት መንግስት ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ማፈኑን፣ የነጻውን ሚዲያ ፣ የፖለቲካ ድርጅቶችንና የሲቪክ ማህበራት እንቅስቃሴዎችን መግታቱን ገልጿል። “ሰላማዊ ተቃውሞ ማድረግ ተከልክሏል፣ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰዎችን ማሰር ፣ ማሰቃየት እና በእስር ቤቶች ውስጥ ሰቆቃዎችን መፈጸም ቀጥሏል” ያለው አምነስቲ “ዜጎችን በሀይል ...

Read More »

የፌደራል መንግስት የባህርዳር ጊዮን ሆቴል በአስቸኳይ እንዲመለስ ትእዛዝ መስጠቱ ታወቀ

ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ለኢሳት እንደገለጹት የፌደራሉ መንግስት ለአማራ ክልል ኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ ባስተላለፈው ተእዛዝ ፣ የሆቴሉ ኪራይ ተስልቶ አስፈላጊው እርክክብ እንዲደረግ አዟል። የክልሉ የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲም ለባለሀብቶቹ በጻፈው ደብዳቤ ሆቴሉን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2005 ዓም ፣ አስፈላጊውን ኪራይ ከፍለው እንዲያስረክቡ ማዘዙ ታውቋል። ባለሀብቶቹ ለወደፊቱ የመረጡት ቦታ ላይ መሬት እንደሚሰጣቸው ቃል ...

Read More »

የመንግስት ባለስልጣናት በበጎ ነገር ምሳሌ የሚሆነን መሪ አጥተናል አሉ

ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዛሬ በባህርዳር ከተማ በኩሪፍቱ መናፈሻ በከፍተኛ ጥበቃ በተካሄደው የፌደራል እና የክልሎች የሰቪል ሰርቪስ የቢሮ አመራሮች ግምገማ  ተሰብሳቢዎቹ ” በበጎ የምናነሳው ምሳሌ የሚሆን መሪ አጥተናል ፣ ኢህአዴግ እና  ሲቪል ሰርቪሱ ሆድና ጀርባ ሆነዋል በማለት” ተናግረዋል። በመንግስት የሚወጡ መመሪያዎች ያለሰራተኛው ፈቃድ ተግባራዊ እንደሚሆኑ የገለጹት ተሰብሳቢዎች፣ሲቪል ሰርቪሲ የፓርቲ አገልጋይ በመሆኑ ትክክለኛ አገልግሎት መስጠት አልተቻለም በማለት ...

Read More »

መንግስት የጎዳና ተዳዳሪዎችን ሰብስቦ በየወረዳው ፖሊስ ጣቢያ አጎረ

ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአፍሪካ ህብረት 50ኛ አመት ክብረ በአል ጋር በተያያዘ የመንግስትን ምስል ያበላሻሉ የተባሉ የጎዳና ተዳዳሪዎች በፌደራልና በአዲስ አበባ ፖሊሶች እየተያዙ በየጣቢያው እንዲታጎሩ ተደርገዋል። ትናንት ፖሊሶች ሲቪል በመልበስ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ያፈሱ ሲሆን ዛሬ ደግሞ በልመና የሚተዳደሩትን  አፍሰዋል። መንግስት አለማቀፍ ስብሰባዎች ሲኖሩ ወይም የኢህአዴግ በአላት ሲከበሩ የመንግስትን መልካም ገጽታ ያበላሻሉ የሚባሉ የጎዳና ተዳዳሪዎች እየታፈሱ በፖሊስ ...

Read More »