ኢህአዴግ በአማራ ክልል ሹሞች ላይ ጥብቅ ግምገማ እያካሄደ ነው

ግንቦት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ከብአዴን ያገኘነው መረጃ እንደሚጠቁመው በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች የመገናኛ ብዙሀን ሽፋን እንዳይሰጡት በተደረገበት ሁኔታ ከግንቦት19 ጀምሮ ግምገማ እየተካሄደ ነው። የግምገማው ዋና አላማ ኢህአዲግ በትጥቅ ትግል እንዲወድቅ አልመው ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅት አባላት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ የሚጠረጠሩ ባለስልጣናትን ሰበብ በመፍጠር ለማውረድና ለመምታት ያቀደ ነው ተብሎአል።

በአብዛኞቹ ግምገማዎች ላይ ከፍተኛ ውጥረት መኖሩንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ግምገማው እስከ ግንቦት 30 እንደሚቀጥልም ለማወቅ ተችሎአል። የግምገማውን ውጤት እንደደረሰን እናቀርባለን።