መጋቢት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኖርዝ ዌስት ውስጥ ቡልም ኦፍ በምትባል ከተማ ውስጥ የሚገኙ ከ100 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ሱቆች ተዘርፈው ተቃጥለዋል። የከተማው ነዋሪዎች ከመሰረታዊ ልማት ጋር በተያያዘ ያስነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ ረብሻ መፈጠሩንና ኢትዮጵያውያን፣ ሶማሊያውያንና ፓኪስታናውያን ኢላማ መሆናቸውን ተናግረዋል። ኢትዮጵያውያኑ አካባቢውን ለቀው ወደ ተለያዩ ቦታዎች ተሰደዋል። በከተማዋ የሚታየው ግጭት ተባብሶ መቀጠሉንም ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል።
Read More »አንድነት ፓርቲ በደሴ የተሰካ የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ
መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሚሊዮኖች ድምጽ በሚል የተጀመረው ሁለተኛ ዙር የአንድነት ፓርቲ እንቅስቃሴ እሁድ መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓም በደሴ ከተማ የተካሄደ ሲሆን፣ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በሰልፉ ላይ ተገኝተዋል። የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ሀብታሙ አያሌው የዝግጅቱ አላማ ህዝቡ ወደ አደባባይ ወጥቶ ችግሩን እንዲናገር፣ እንዲተነፍስ፣ የህዝቡን ችግሮች ለማወቅ እና ህዝቡ ...
Read More »የአረና ትግራይ አመራሮችና ደጋፊዎች በህወሃት ካድሬዎች ሲዋከቡ መሰንበታቸውን የድርጅቱ አመራሮች ገለጹ
መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓም ፓርቲው በምስራቃዊ ዞን አጽቢ ወንበርታ ወረዳ የጠራው ህዝባዊ ስብሰባ በከፍተኛ የደህንነት አፈና ውስጥ ሆኖ መካሄዱን የፓርቲው የስራ አስፈጻሚና የህዝብ ግንኑነት አባል የሆነው አቶ አብረሃ ደስታ ገልጿል። ህዝቡ ከፍተኛ አቀባበል ቢያደርግላቸውም የህወሃት ካድሬዎች ምግብ እንዳያገኙ፣ አንዳንድ አመራሮች የያዙትን አልጋ እንዲለቁ ማድረጋቸውን በስብሰባው ዕለት መጋቢት 28 ደግሞ ህጻናቱ ...
Read More »ኢቦኒ የተባለው መጽሄት ተዘጋ
መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት 6 አመታት በህትመት ላይ የነበረው ኢቦኒ መጽሄት የተዘጋው ከመንግስት ከፍተኛ የሆነ የግብር እዳ ከተጣለበት በሁዋላ ነው። ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ የመጽሄቱን ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝን ጠቅሶ እንደዘገበው የመጽሄቱ አዘጋጆች ሙሉውን ግብር ቀርቶ ግማሹንም ለመክፈል ባለመቻላቸው መጽሄቱን ለመዝጋት ተገደዋል። ድርጅቱ ከወረቀት እና ከሌሎች የህትመት ወጪዎች ጋር በተያያዘ ለከፍተኛ የገንዘብ ችግር ተዳርጎ ...
Read More »በሀረር በቅርቡ ከታሰሩት መካከል አንዱ ወጣት ተገደለ
መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀበሌ 10 ነዋሪ የሆነው ዳንኤል ጎሳ የተበላው ወጣት ሀኪም ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ከታሰረ በሁዋላ በእስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶበት መሞቱን የፖሊስ ምንጮች ገልጸዋል። ፖሊስ በበኩሉ ወጣቱ በራሱ ቲሸርት ታንቆ መሞቱን የገለጸ ሲሆን፣ የእስር ቤት ምንጮች እንዳሉት ግን ወጣቱ ከፍተኛ ደብደባ ደርሶበት ሊሞት ተቃርቦ እንደነበር፣ ፖሊስ እጁ እንደሌለበት ለማስመሰል ቲሸርቱን አውልቆ ...
Read More »በሩዋንዳ የደረሰው የዘር ጭፍጫፋ 20ኛ አመት እየታሰበ ነው
መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ800 ሺ ያላነሱ ቱትሲዎችና ለዘብተኛ ሁቱዎች የተገደሉበትን 20ኛ አመት ለማክበር በርካታ ህዝብ በስታዲየሞች ተገንቶ ስነስርአቱን የተከተታለ ሲሆን፣ አንዳንድ ዜጎች በጊዜው ስለነበረው ሁኔታ ሲገለጽ ራሳቸውን ለመቆጣጠር ተስኖአቸው ታይቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ባንኪሙን ጭፍጨፋውን ለማስቆም ደርጅታቸው በቂ የሆነ እገዛ ባለማድረጉ ይቅርታ ጠይቀዋል። የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዎሪ ሙሰቬኒ፣ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ታቦ ...
Read More »የአንድነት ፓርቲ የተቃውሞ ሰልፍ መተላለፉን ፓርቲው አስታወቀ
መጋቢት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ መስተዳድር ለፓርቲው በጻፈው ደብዳቤ ፓርቲው ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የጠየቀባቸው ቦታዎች የተለያዩ ትምህርት ቤቶች እና ትላልቅ የመንግስት ተቋማት የሚገኙባቸው በመሆኑ እንዲሁም በእለቱ ሌሎች ተመሳሳይ የህዳሴ ግድብ ፕሮግራሞች ስለአሉ እውቅና እንደማይሰጥ ማሳወቁን ተከትሎ፣ አንድነት ፓርቲ የሰልፉን ቀን በአንድ ሳምንት አስተላልፏል። ጉዳዩን በማስመልከት ጥያቄ ያቀረብንላቸው የፓርቲው የአዲስ አበባ ጽ/ቤት ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ...
Read More »በጎንደር ከተማ በህገወጥ መንገድ ቤት ሰርታችሁዋል የተባሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲያፈርሱ ተጠየቁ
መጋቢት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ 15 ሺ በላይ ህዝብ ይኖርበታል ተብሎ በሚገመተው ቀበሌ 18 በገንፎ ቁጭ ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች ቤታቸውን በአስቸኳይ እንዲያፈርሱ የታዘዘው ፣ ቤቱቹ በህገወጥ መንገድ ተገንብተዋል በሚል ነው። ቤቱቹ የተገነቡት ከ10 አመታት በፊት መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች መንግስት ቤቶቹ ሲሰሩ ማስቀም እየቻለ ዛሬ በአካባቢው አስፈላጊው ልማት ከተካሄደ በሁዋላ አፍርሱ ማለቱ ተገቢ አይደለም ብለዋል። በዛሬው ...
Read More »በሀረር ታስረው ከነበሩት ሰዎች መካከል አንዳንዶች ተለቀቁ
መጋቢት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሀረር ከተከሰተው የእሳት አደጋ ጋር በተያያዘ ታስረው ከነበሩት ሰዎች መከካል አንዳንዶች ተለቀዋል። ፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቁ ውሳኔ ካስተላለፈባቸው 7 ሰዎች መካከል ለአሜሪካ ድምጽ ቃለምልልስ ሰጥተዋል ተብለው የታሰሩት አቶ ገብረመድህን ገብረ መስቀል እንዲሁም 4ቱ የመብራት ሀይል ሰራተኞችም ተለቀዋል። ይሁን እንጅ በሀረሪ የመገናኛ ብዙሃን ሰራተኛ የነበረው ጋዜጠኛ ጀማል ዳውድ አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኝና ...
Read More »በአዋሳ ታቦር ትምህርት ቤት የተነሳውን ግጭት ክልሉ ሆን ብሎ ያቀነባበረው እንደነበር አንድ የደኢዴግ አባል ገለጹ
መጋቢት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የገዢው ፓርቲ አባል የሆኑት ግለሰብ እንደገለጹት መድረክ የተባለው የተቃዋሚዎች ስብስብ በአዋሳ ከተማ በርካታ ህዝብ በተገኘበት ስብሰባ ማድረጉን ተከትሎ የተበሳጩት የገዢው ፓርቲ ሰዎች ግጭቱን ተቃዋሚዎች ያስነሱት ነው ለማለት ከውጭ የኒፎርም ለብሰው ወደ ትምህርት ቤቱ የገቡ 45 ተማሪዎች 500 ብር ተከፍሎአቸው እንዲነሳ ማድረጉን ገልጸዋል እቅዱ ሲዘግጀ ነበርኩ ያሉት ግለሰብ፣ ሁኔታው አበሳጭቷቸው ለመናገር እንደተገደዱ ...
Read More »