በሩዋንዳ የደረሰው የዘር ጭፍጫፋ 20ኛ አመት እየታሰበ ነው

መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ800 ሺ ያላነሱ ቱትሲዎችና ለዘብተኛ ሁቱዎች የተገደሉበትን 20ኛ አመት ለማክበር በርካታ ህዝብ በስታዲየሞች ተገንቶ ስነስርአቱን የተከተታለ ሲሆን፣ አንዳንድ ዜጎች በጊዜው ስለነበረው ሁኔታ ሲገለጽ ራሳቸውን ለመቆጣጠር ተስኖአቸው ታይቷል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ባንኪሙን ጭፍጨፋውን ለማስቆም ደርጅታቸው በቂ የሆነ እገዛ ባለማድረጉ ይቅርታ ጠይቀዋል።

የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዎሪ ሙሰቬኒ፣ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ታቦ ምቤኪና የቀድሞው የእንግሊዝ ጠ/ሚንስትር እና ሩዋንዳ መንግስት አማካሪ ቶኒ ብሌየር በስነስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

የሩዋንዳ መንግስት ፈረንሳይና ቤልጂየም በጭፍጨፋው ላይ እጃቸው እንዳለበት ማሳወቁን ተከትሎ የፈረንሳይ አምባሳደር በዝግጅቱ ላይ እንዳይገኙ ተደርጓል።