የአረና ትግራይ አመራሮችና ደጋፊዎች በህወሃት ካድሬዎች ሲዋከቡ መሰንበታቸውን የድርጅቱ አመራሮች ገለጹ

መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓም ፓርቲው በምስራቃዊ ዞን አጽቢ ወንበርታ ወረዳ የጠራው ህዝባዊ ስብሰባ በከፍተኛ የደህንነት አፈና ውስጥ ሆኖ መካሄዱን የፓርቲው የስራ አስፈጻሚና የህዝብ ግንኑነት አባል የሆነው አቶ አብረሃ ደስታ ገልጿል።

ህዝቡ ከፍተኛ አቀባበል ቢያደርግላቸውም የህወሃት ካድሬዎች ምግብ እንዳያገኙ፣ አንዳንድ አመራሮች የያዙትን አልጋ እንዲለቁ ማድረጋቸውን በስብሰባው ዕለት መጋቢት 28 ደግሞ ህጻናቱ ድንጋይ እየወረወሩ የአረና አባላትን መማታታቸውን ተናግሯል

አቶ አብረሃ እንደሚለው አረና በትግራይ ተጠናክሮ መቀጠሉ ህወሃትን ስጋት ላይ የጣለው ሲሆን፣ ድርጅቱን የሚቀላቀሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱንም ገልጿል።