ግንቦት ፳፰(ሃያ ስምን)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከተማዋ አውቶቡስ መናሃሪያ ውስጥ ይሰሩ የነበሩ 27 ወጣቶች ጣቢያ 2 ወደ ሚባለው እስር ቤት ተወስደው መታሰራቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ከታሰሩት መካከል 9ኙ በማግስቱ ሲፈቱ ቀሪዎቹ አሁንም በእስር ላይ ናቸው። ከተፈቱት መካከል አንዳንዶቹ ያለምንም ምክንያት ወይም የፖሊስ ምርመራ ታስረው እንደተለቀቁ ተናግረዋል። በጉዳዩ ዙሪያ የባህርዳር ፖሊስ ጽ/ቤትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
Read More »በአዲስ አበባ የተፈረመው የሰላም ስምምነት በደቡብ ሱዳን ሰላም ሊያሰፍን አልቻለም ተባለ
ግንቦት ፳፰(ሃያ ስምን)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሱዳን ትሪቡዩን እንደዘገበው ብዙ በኢጋድ አስተባባሪነት በአዲስ አበባ የተፈረመው የሰላም ስምምነት በአገሪቱ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም አልቻለም። በፕሬዚዳንት ሳልቫኪር እና በተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር መካከል የሚካሄደው ጦርነት የበርካታ ደቡብ ሱዳናውያንን ህይወት እየቀጠፈ ነው። የሰላም ስምምነቱ ውጤት አለማምጣቱን ተከትሎ ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ አገራት የሰላም እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።
Read More »በጊኒ በተከሰተ የኢቮላ ቫይረስ በትንሹ 208 ሰዎች መሞታቸውን የዓለም የጤና ጥበቃ ባለስልጣናት አስታወቁ።
ግንቦት ፳፰(ሃያ ስምን)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለስልጣናቱን ጠቅሶ ቢቢሲ እንደሰገበው፤ ካለፈው ሜይ እስከ ጁን ድረስ ባለው የአንድ ወር ጊዜ ጊኒ ውስጥ በ ኢቦላ 21 ሰዎች ሲሞቱ 37 አዲስ ተጠቂዎች ተመስግበዋል። ይህም በምእራባዊቱዋ አፍሪቃሀገር በኢቦላ የተጠቁትን ሰዎች አጠቃላይ ድምር ወደ 328 ከፍ ይደርገዋል። ኢቦላ ፤መድሀኒት የሌለው፣ ክትባት ያልተገኘለት እና በዓለማችን ዋነኛ ገዳይ በሽታዎች ተብለው ከተመሰገቡት መካከል አንዱ ነው። በርካታዎች የሞቱት ...
Read More »በደብረ ዘይት ነዋሪዎች ብሄራቸውንና ሃይማኖታቸውን እንዲያስመዘግቡ መገደዳቸው አስግቶዋቸዋል
ግንቦት ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከተማዋ ቀበሌ አንድ የሚገኙ ነዋሪዎች እንደገለጹት ፖሊሶች ከስቪል ሰራተኞች ጋር በመሆን ቤት ለቤት እየዞሩ የነዋሪዎችን ብሄር እና ሃይማኖት ሲመዘግቡ ውለዋል። “የምዝገባው አላማ ሰዎችን እየመረጡ ለማፈናቀል ሊሆን ይችላል” በማለት ስጋታቸውን የገለጹት ነዋሪዎች፣ብሄርን መመዝገቡ ለምን እንዳስፈለገ ሲጠይቁ ከላይ የተላለፈ መመሪያ ነው በሚል እንደተነገራቸው ገልጸዋል። በጉዳዩ ዙሪያ የከተማውን ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሃላፊዎች ለማግኘት ሙከራ ብናደርግም ...
Read More »አንድ በጥብቅና ሙያ ሲያገለግሉ የነበሩ ሰው ለተቃዋሚ አባል ጥብቅና በመቆማቸው እየተሳደዱ ነው
ግንቦት ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ሊበን ታየ የተባሉ አርሶ አደር የተቃዋሚ ፓርቲ አባል በመሆናቸው ብቻ በወረዳው ፖሊሶች ተደብድበውና ጭንቅላታቸው ላይ በሽጉጥ ተመትተው በሞትና በህይወት መካከል ወድቀው መገኘታቸውን ተከትሎ ፣ አርሶ አደሩ ከህመማቸው ሲያገግሙ ለወረዳው ጠበቃ ይገርማል መልካሙ አሰፋ ጉዳያቸውን ማመልከታቸውን ተከትሎ ችግሩ መጀመሩን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። አቶ ሙጩ ዳኔ፣ አቶ ...
Read More »በሁለት ዙር የሰለጠኑ 235 የድረ ገፅ መረጃ ማዛባት የሚችሉ ፕሮፓጋንዲስቶች በስራ ላይ መሆናቸው ታወቀ፡፡
ግንቦት ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ በመላ ሐገሪቱ በኢንተርኔት ድረ ገፅ መንግስት እየደረሰበት ያለውን ትችት ለመቀነስና ፤ የተደበቁ መረጃዎች ተጋላጭነታቸውን ለመቆጣጠር በማሰብ የሰለጠኑ ወጣቶች ስራ መጀመራቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል፡፡ ኢህአዴግ በአዳማ ናዝሬት በሁለት ዙር ያሰለጠናቸው 235 ብሎገሮች በፊስ ቡክና በተለያዩ የማህበራዊ የመገናኛ መንገዶች፣ተቃዋሚ የሚመስሉ ስያሜዎችን በማውጣት ህዝብ የማደናገር፤ መንግስትን በሚቃወሙ መረጃዎች ላይ ምላሽ የመስጠት ፤ መንግስትን ...
Read More »መንግስት አንድ የአልሸባብ ልኡክን መያዙን አስታወቀ
ግንቦት ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አልሸባብ በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ሊፈጽም ይችላል በሚል ምእራባዊያን አገራት ማስጠንቀቂያ ማውጣታቸውን ተከትሎ፣ ምንም ይፋዊ መግለጫ ሳይሰጥ የቆየው መንግስት፣ ዘግይቶ አንድ የአልሸባብ የጥቃት አቀነባባሪ የሆነ ግለሰብ መያዙን አስታውቋል። መንግስት የግለሰቡን ማንነት ይፋ አላዳረገም። ከዚሁ ጋር ተያይዞ መንግስት 70 የሚደርሱ የአልሸባብ ወታደሮችን መግደሉን አስታውቋል። ከሶማሊያ የሚወጡ ዘገባዎች በበኩላቸው በአልሸባብና በኢትዮጵያ ወታደሮች መካከል በተደረገው ከፍተኛ ...
Read More »ኢትዮጴያዊት የቤት ሰራተኛ በባርነት ለ 15 ዐመታት መገዛቱዋ ከፍተኛ ትኩረት ከመሳቡም በላይ ጥብቅ የሆነው የቤት ሰራተኞች ህግ መሻሻል እንዳለበት ያመላከተ እንደሆነ ተገለጸ።
ግንቦት ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሳንዲፕ ሲን ግሪዋል እንደዘገበው፤ ኢትዮጰያዊቱ ሰብለ አበበ ተሰማ በባህሬይን በቤት ሰራተኝነት ለ 15 ዓመታት ብታገለግልም፤ የተከፈላት ደመወዝ ከ 18 ወራት ያነሰ መሆኑ ትናንት የስደተኛ ሰራተኞች ተካላካይ ማህበር በአድሊያ በሰጠው ጋሴጣዊ መግለጫ ተወስቱዋል። በምህጻረ-ቃል “ ኤም.ደብሊው፣ ፒ ኤስ” የተሰኘው ይህ የስደተኞች ተንከባካቢ ድርጅት እንዳለው፤ ሰብለ በመጀመሪያ ባህሬን የገባችው እ.አ.አ በ 1999 ዓመተ ምህረት የ ...
Read More »ከ30 በላይ የኢትዮጵያ ታጣቂ ሚሊሺያዎች በአልሸባብ መገደላቸውን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደህንነት ክፍል የተገኘ መረጃ አመለከተ
ግንቦት ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሰራተኞቹ በላከው ማስጠንቀቂያ ላይ በሶማሊ ክልል ባሪ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ 33 የኢትዮጵያ ሚሊሺያዎች በአልሸባብ ታጣቂዎች መገደላቸውን ገልጾ ሰራተኞቹ አስፈላጊውን ጥንቃቄና ጥበቃ እንዲያደርጉ መክሯል። የኢትዮጵያ የብሄራዊ የደህንነት ጥበቃ መስሪያ ቤት አልሸባብ በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ሊፈጽም ይችላል የሚለውን ስጋት እንደሚጋራ የገለጸው ድርጅቱ ፣ ትምህርት ቤቶች እና ሌሎች ቦታዎች በጥንቃቄ እንዲጠበቁ አዟል። ...
Read More »በምዕራብ ኦሮምያ ዞን የፌደራል ፖሊሶች ከህዝብ ጋር መጋጨታቸው ተሰማ
ግንቦት ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ቅዳሜ አቡና በሚባል ወረዳ የፌደራል ፖሊሶች ነዋሪዎችን መደብደባቸውንና ቁጥራቸው ያልታወቁትንም ይዘው ማሰራቸውን የአካባቢዎች ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። የግጭቱ መነሻ በቅርቡ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ በወረዳው የተነሳውን ተቃውሞ አስተባብሮአል የተባለው መንጌ ጉደታ እንዲፈታ ህዝቡ ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ ነው። ወጣቱ እግሩ በድብደባ ብዛት መሰበሩን የሚገልጹት አካባቢው ነዋሪዎች፣ ነዋሪዎች ወጣቱ ካልተለቀቀ ፖሊስ ጣቢያውን እናቃጥላለን ...
Read More »