በጊኒ በተከሰተ የኢቮላ ቫይረስ በትንሹ 208 ሰዎች መሞታቸውን  የዓለም የጤና ጥበቃ ባለስልጣናት አስታወቁ።

ግንቦት ፳፰(ሃያ ስምን)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለስልጣናቱን ጠቅሶ ቢቢሲ እንደሰገበው፤ ካለፈው ሜይ እስከ ጁን ድረስ ባለው የአንድ ወር ጊዜ ጊኒ ውስጥ በ ኢቦላ 21 ሰዎች ሲሞቱ 37 አዲስ ተጠቂዎች ተመስግበዋል።

ይህም በምእራባዊቱዋ አፍሪቃሀገር በኢቦላ የተጠቁትን ሰዎች አጠቃላይ ድምር ወደ 328 ከፍ ይደርገዋል።

ኢቦላ ፤መድሀኒት የሌለው፣  ክትባት ያልተገኘለት እና በዓለማችን ዋነኛ ገዳይ በሽታዎች ተብለው ከተመሰገቡት መካከል አንዱ ነው።

በርካታዎች የሞቱት ቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊሴ በተቀሰቅሰባት በደቡባዊ  ጉኬዶው ክልል መሆኑንም ቢቢሲ አእመልክቱዋል።

በተመሳሳይ ወቅት በጎረቤት ሴራሊዮን በተደረገ ምርመራ ሶስት ሰዎች በ ቫይረሱ መጠቃታቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ ሌሎች አስር ሰዎችም  በቫይረሱ ሳይጠቁ እንዳልቀሩ ተገምቱዋል።

እንዲሁም በላይቤሪያ አስር ሰዎች በሲሁ በኢቦላ ቫይረስ መሞታቸው ይታመናል።

ኢቦላ ወይም ሀይሞራጂክ ትኩሳት ተብሎ የሚታወቀው ይህ በሽታ ከተጠቂ ሰው ጋር በሚደረግ ንክኪ በቀላሉ የሚተላለፍ ሲሆን፤ በሲህ ቫይረስ ከሚጠቁት መካከል 90 በመቶ የሚሆኑት ለሞት እንደሚዳረጉ የህክምና መረጃዎች ያሳያሉ።

ይሁንና ህመሙን ገና ሲጀምራቸው በመጠርጠር በቶሎ ወደ ህክምና የሚሄዱ ወይም ቫይረሱ ገና እንዳጠቃቸው ህክምና የማግኘት እድሉ ያላቸው ከሞት የመትረፍ እድሉ አላቸው።

በአሁኑ ወቅት  የዓለም የጤና ድርጅት ባለሙያዎች እና  የዶክተር ዊዝአውት ቦርደርስ ሰራተኞች  ወደ ስፍራው በማቅናት ህክምና እየሰጡ መሆናቸውን የጠቀሰው ቢቢሲ፤  በቫይረሱ ሳይጠቁ እንዳልቀሩ የተገመቱ ወደ 600 የሚጠጉ ሰዎች ምርመራና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ አመልክቱዋል።