በአዲስ አበባ የተፈረመው የሰላም ስምምነት በደቡብ ሱዳን ሰላም  ሊያሰፍን አልቻለም ተባለ

ግንቦት ፳፰(ሃያ ስምን)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሱዳን ትሪቡዩን እንደዘገበው ብዙ በኢጋድ አስተባባሪነት በአዲስ አበባ የተፈረመው የሰላም ስምምነት በአገሪቱ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም አልቻለም።

በፕሬዚዳንት ሳልቫኪር እና በተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር መካከል የሚካሄደው ጦርነት የበርካታ ደቡብ ሱዳናውያንን ህይወት እየቀጠፈ ነው።

የሰላም ስምምነቱ ውጤት አለማምጣቱን ተከትሎ ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ አገራት የሰላም እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።