በባህርዳር 27 ወጣቶች ታሰሩ

ግንቦት ፳፰(ሃያ ስምን)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከተማዋ አውቶቡስ መናሃሪያ ውስጥ ይሰሩ የነበሩ 27 ወጣቶች ጣቢያ 2 ወደ ሚባለው እስር ቤት ተወስደው መታሰራቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።

ከታሰሩት መካከል 9ኙ በማግስቱ ሲፈቱ ቀሪዎቹ አሁንም በእስር ላይ ናቸው። ከተፈቱት መካከል አንዳንዶቹ  ያለምንም ምክንያት ወይም የፖሊስ ምርመራ ታስረው እንደተለቀቁ ተናግረዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የባህርዳር ፖሊስ ጽ/ቤትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።