ነሃሴ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዝክረ መለስ 2ኛ የሙት ዓመት አከባበርን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ በነበረው የፓናል ውይይት የመንግስትንስራተኛው ለግማሽ ቀን ስራ ሳይሰራ መዋሉን ዘጋያችን ገልጿል። በተለያዩ ቦታዎች የተዘጋጁትን የፓናል ውይይቶች የመስተዳድሩ የአመራር አባልአቶፋቃዱወ/አረጋይ፣ የአዲስአበባሴቶችናወጣቶችቢሮኃላፊና የምክትል ቢሮኃላፊበተናጠልመርተዋል። የወጣቶች መድረክ በሃገር ፍቅር አዳራሽ ፣የሴቶችመድረክበአዲስአበባማዘጋጃቤትየባህልአዳራሽእንዲሁምየልዩልዩአካላትመድረክበስድስትኪሎበሚገኘው የባህልማዕከልየፓናልውይይትተካሂዷል። በሶስቱም ውይይቶች ለተሳታፊዎችየሃሳብናየጥያቄማቅረቢያሰዓትበተጊቢውመንገድያላተሰጠሲሆንሁሉም የመድረኩ ተናጋሪዎች አቶ መለስዜናዊን በማወደስ ላይ ትኩረት አድርገው ነበር። በመድረኩ ላይ አቶ ...
Read More »የደቡብ ሱዳን አማጽያን በጋንቤላ ሆስፒታል እየታከሙ ነው
ነሃሴ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሪክ ማቻር የሚመራው በአብዛኛው የኑዌር ጎሳ አባላት ሆኑ የደቡብ ሱዳን አማጽያን ቁስለኞች በጋምቤላ ሆስፒታል እየታከሙ መሆኑን የጋምቤላ ምንጮች ገልጸዋል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ተዋጊዎች የነጻ ህክምና እየተሰጣቸው ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በተዘዋዋሪ መንገድ ለሪክ ማቻር ድጋፍ እንደምትሰጥ ያሳያል ሲሉ ምንጮች አስተያየታቸውን አክለዋል። ከሳምንታት በፊት መንግስት 3 አውቶቡስ ሙሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ወደ አካባቢው የላከ ሲሆን፣ ምንጮች እንደሚሉት ...
Read More »የመተማገንዳውሃአመራሮች በርካታ ችግሮች አሉብን ሲሉ ተናገሩ
ነሃሴ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢውን ህዝብ ለማወያየት የተንቀሳቀሱት ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ፣ ከተመረጡ የመተማ ገንዳውሃ ህዝብ መሪዎች፣ ከስርአቱ ደጋፊዎችና ከድርጅቱ ካድሬዎች ጋር ባደረጉት ውይይት የህዝብ ተወካዮች የመልካም አስተዳዳር፣ የመሰረተ ልማትና የጸጥታ ችግሮችን አንስተው መንግስት አፋጣኝ መልስ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።ገንዳውሃ የመብራት፣ የውሃ እና ሌሎች የመሰረተልማት ችግሮችን እንዳሉባት አንድ ተናጋሪ ገልጸዋል። የከተማዋ ወጣቶች ቀርፀው የላኩልን የድምጽ መልእክት እንደሚያሳየው አንድ የኢህአዴግ ካድሬ ...
Read More »በዩክሬን፤ ውጥረቱ አደገኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።
ነሃሴ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዩክሬን መንግስትና በአማጽያኑ መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ ሩሲያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከባድ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ወደ ስፍራው ማንቀሳቀሱዋ ውጥረቱን ወደ አደገኛ ጫፍ ላይ እንዳደረሰው አለማቀፍ ብዙሀን መገናኛዎች እየዘገቡ ነው።ቢቢሲ እንዳለው፤የሩሲያ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ዩክሬን ድንበር መጠጋታቸውን ተከትሎየዩክሬን አማጽያን የተቆጣጠሩዋትዶኔትስክ ከተማ በከባድ ፍንዳታ ተናውጣለች።ፍንዳታውን ተከትሎ የመንግስት ሰራተኞችና ነዋሪዎች ከቢሮአቸውና ከመኖሪያቸው በመውጣት ወደ ከተማዋ ማእከላዊ ቦታ ተሰባስበው ...
Read More »የአዲስ አበባ መስተዳድር በቤቶች ግንባታ ዙሪያ ለምርጫ እንዲደርስ በሚል አስቸኳይ ትእዛዝ ሰጠ
ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ40 በ60 በሚባለው የቤቶች መርሃግብር የታቀፉ የዲያስፖራ አባላት ከቀጣዩዓመት ምርጫበፊት ቤት እንዲሰጣቸው የአዲስ አበባ መስተዳድር መመሪያመስጠቱ ታውቋል። ሆኖምየጠቅላላተመዝጋቢውንየቤትፍላጎትለመሸፈንበትንሹከ16 ዓመታትበላይጊዜን እንደሚወስድ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ የአዲስ አበባቁጠባቤቶችኢንተርፕራይዝእስካሁን 13ሺህ 800 ቤቶችን በሰንጋተራእና ቃሊቲ ክራውን ሆቴልበመሳሰሉአካባቢዎችላይእየገነባመሆኑየታወቀሲሆን ፣ እነዚህን ቤቶችእስከሚቀጥለውዓመትአጋማሽድረስለዕድለኞችለማስተላለፍታቅዷል። የአስተዳደሩምንጮችእንደገለጹትቤቶቹከቀጣይዓመትምርጫበፊትሙሉበሙሉ ተጠናቀውእንዲተላለፉከአስተዳደሩመመሪያተሰጥቷል። ሆኖም ለ40 በ60 የቤቶች ፕሮግራምየተመዘገበውጠቅላላሕዝብቁጥር 164 ሺህ 779 ያህልሲሆንአስተዳደሩግን በዓመትከ10 ሺህቤቶችበላይቤቶችን የመገንባትአቅምባለመፍጠሩየተመዘገቡትንብቻ ለማዳረስከ16 ዓመታትበላይጊዜንእንደሚፈልግየአስተዳደሩምንጮችአስታውቀዋል፡፡ ይህደግሞ ከዛሬ ነገየመኖሪያቤትባለቤትእሆናለሁብሎተስፋላደረገውሕዝብተስፋ አስቆራጭዜናነውብለዋል፡፡ በ20/80 ...
Read More »በአንዋር መስጊድ ከተፈጠረው ግጭት ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሙስሊሞች በድጋሜ ተቀጠሩ
ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በአንዋር መስጊድ የተፈጠረውን ተቃውሞ መርተዋል በሚል ከታሰሩት መካከል 6 ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የዋስትና መብታቸውን ተነጥቀው ለሰኞ ችሎት እንዲቀርቡ ታዘዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባሏ ወ/ት ወይንሸት ሞላ ፣ የፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ ሙሃመድ እና ኢብራሂም አብዱልሰላም በ5 ሺ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት በድጋሜ አዟል። እስረኞቹ ቀደም ብሎ እንዲለቀቁ ትእዛዝ ...
Read More »ፖሊሶች በአበል ጉዳይ እየተወዛገቡ ነው
ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዳግማዊ ሚኒልክና በሌሎችም አካባቢዎች የሚሰለጥኑ ፖሊሶች በቀን የሚታሰብላቸው ገንዘብ በቂ ባለመሆኑ ጥያቄ አንስተዋል። ፖሊሶቹ ለቁርስና ምሳ እንዲሁም ለሻሂና ቡና 24 ብር በቀን የሚታሰብላቸው ቢሆንም፣ ገንዘቡ አይበቃንም በሚል ጥያቄ አንስተዋል። ፖሊሶቹ ስልጣናውን ሳያቋርጡ ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ የኮሚሽኑ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ለማግባባት እየሞከሩ ነው። በዳግማዊ ሚኒሊክ ት/ቤት ውስጥ ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ ከ500 በላይ ፖሊሶች እየሰለጡ ነው። ስልጣናው ...
Read More »በአዲስ አበባ መስተዳደር የነተጠቀ ቦታ በጠ/ሚንስትር ጽ/ቤት እንዲመለስ ታዘዘ
ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሼክ ሙሃመድ አላሙዲን ንብረት የሆኑ በአዲስ አበባ ለአመታት ታጥረው የተቀመጡ የግንባታ ቦታዎች፣ የመስተዳድሩ ባለስልጣናት እንዲነጠቁ ውሳኔ አስተላልፈው ውሳኔውም ተግባራዊ ሆኖ ቆይቷል። ይሁን እንጅ ሪፖርተር እንደዘገበው ሼክ ሙሃመድ አላሙዲን ለጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤ የግባኝ በማለታቸው የተወሰደባቸው ቦታ እንደሚለስላቸው መደረጉንና የመስተዳድሩ ውሳኔ መቀልበሱን ገልጿል። ተወስደው የነበሩት ቦታዎች ልደታ ክ/ከተማ ዋቢ ሸበሌ ጎንና በየካ ክፍለከተማ በሻሌ ሆቴል አካባቢ እንደሚገኙ ...
Read More »ኬንያ በኢቦላ በሽታ የመጠቃት እድሏ ከፍተኛ ነው ተባለ
ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጊኒ ፣ ሴራሊዮንና ላይቤሪያ የታየው የኢቦላ ወረርሽኝ ወደ ሌሎች የአፍሪካ አገራት እንዳይዛመት ከፍተኛ ስጋት በደቀነበት በዚህ ወቅት፣ ከምስራቅ አፍሪካ ኬንያ በበሽታው ከሚጠቁ ቀዳሚ አገራት ተርታ ተሰልፋለች።ኬንያ የብዙ የምእራብ አፍሪካ አገራት የትራንስፖርት ማእከል በመሆኗ በበሽታው የመጠቃት እድላን ከፍ እንዳደረገው የተባበሩት መንግስታት የጤና ድርጅት አስታውቋል። ጀርመን ዜጓቿ ከላይበሪያ፣ ጊኒና ሴራሊዮን እንዲወጡ ስታዝ፣ጋናደግሞየትምህርት ቤት የመክፈቻ ጊዜን አራዝማለች። ...
Read More »በምእራብ አርማጭሆ ወረዳ የአብድራፊ ከተማ ህዝብ በሸፍቶች እየተዳደርን ነው ሲሉ አቤቱታ አቀረቡ
ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የክልሉን ከፍተኛ ባለስልጣናት በመያዝ ከአብድራፊ ከተማ ነዋሪዎች ተወካዮች ጋር የተነጋገሩ ሲሆን፣ ህዝቡ በአስተዳደር እና በጸጥታ ችግሮች ምክንያት መማረሩን ተወካዮቹ ተናግረዋል። አንድ የቀበሌ አስተዳዳሪ ህዝቡ በመብራት፣ ውሃ እና በመንገድ ችግር እየተቸገሩ መሆኑን ተናግረዋል። ሌላ ተናጋሪ ደግሞ ህዝቡ በድብቅ ጠመንጃ እየተዳደረ መሆኑንና ወረዳው ህዝቡን ማስተዳዳር እንደተሳነው ገልጸዋል። በትግራይ ክልል የድብቅ ...
Read More »