በአዲስ አበባ መስተዳደር የነተጠቀ ቦታ በጠ/ሚንስትር ጽ/ቤት እንዲመለስ ታዘዘ

ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሼክ ሙሃመድ አላሙዲን ንብረት የሆኑ በአዲስ አበባ ለአመታት ታጥረው የተቀመጡ የግንባታ ቦታዎች፣ የመስተዳድሩ

ባለስልጣናት እንዲነጠቁ ውሳኔ አስተላልፈው ውሳኔውም ተግባራዊ ሆኖ ቆይቷል። ይሁን እንጅ ሪፖርተር እንደዘገበው ሼክ ሙሃመድ አላሙዲን ለጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤ

የግባኝ በማለታቸው የተወሰደባቸው ቦታ እንደሚለስላቸው መደረጉንና የመስተዳድሩ ውሳኔ መቀልበሱን ገልጿል። ተወስደው የነበሩት ቦታዎች ልደታ ክ/ከተማ ዋቢ

ሸበሌ ጎንና በየካ ክፍለከተማ በሻሌ ሆቴል አካባቢ እንደሚገኙ ጋዜጣው ዘግቧል። በሸራተን አካባቢ ለማስፋፊያ ስራ ተብሎ በአካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎች እንዲነሱ

ቢደረግም እስካሁን ግንባታ አለመጀመሩን ነገር ግን በፒያሳና ካዛንችስ አካባቢ ታጥረው በተቀመጡ ቦታዎች ላይ የተወሰኑ ስራዎችን ለመስራት እንቅስቃሴ መጀመሩን

ጋዜጣው ዘግቧል።  የአቶ ሃይለማርያም ጽ/ቤት በምን መስፈርት የአዲስ አበባን መስተዳደር ውሳኔ እንደቀለበሰው የተጠቀሰ ነገር የለም።