የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ላይ ጠንካራ አቋም እንዲይዝ ጠየቁ

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢ/ር ይልቃል ከ20 የአውሮፓ ህብረት አገራት ልኡካን ጋር በህብረቱ ጽ/ቤት ተገኝተው በተወያዩበት ወቅት እንደገለጹት ፣ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ችግር ወደ ባሰ ችግር ሳትገባ ህብረቱ አፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ ይገባዋል። ኢ/ር ይልቃል ገዢው ፓርቲ ስለሚያደርገው አፈና፣ በሚዲያው ላይ ስለሚወሰደው እርምጃ፣ በእስር ላይ ስለሚገኙት ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞችና ጸሃፊዎች የተናገሩ ሲሆን፣ ኢህአዴግ በርእዮታለም መደናበርና በአመራር ብቃት ማነስ መቸገሩን በመግለጽ መጪውን ...

Read More »

ኢህአዴግ በከፍተኛ ደረጃ ለሚገኙ አመራሮች ስልጠና መስጠት ጀመረ

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል አቃቢያነ ህጎች እና ዳኞች፣የፈደራልማረሚያቤቶችባለስልጣናት፣የፌደራልናየአዲስአበባፖሊስ አመራሮችናየደህንነትሃላፊዎችበአቶአባዱላገመዳአሰልጣኝነት  የኢትዮጵያህዝቦችትግልናሃገራዊሕዳሴያችንበሚልርእስስልጠናጀምረዋል። ስልጠናው ምናልባትም በቅርቡበቀድሞውም/ል ጠ/ሚ  አዲሱለገሰ  በቀረበዉና የኢህአዴግን የአመራር ችግር በሚዘረዝረውን  ጥናት ላይ ለመወያየት ሳይሆን እንደማይቀር ምንጮች ጠቁመዋል። በዚህጥናትኢህኣዴግበከፍተኛየአመራርእጥረትእየተቸገረመሆኑን፣ኦሮሞየሆኑየኦህዴድኣባላትሙሉበሙሉወደኦነግእንዳደሉእንዲሁምደግሞ፣የአማራው ክፍልየሆነውብሄረ አማራዲሞክራሲያዊንቅናቄ ከግንቦት7 ጋር ሽርክና መፍጠሩን መግለጻቸው ይታወሳል። አቶ አዲሱ የትራንስፎርሜሽኑ እቅድ ሊሳካ ያልቻለው በአመራር ችግር ምክንያት መሆኑንም ተናግረዋል። ስብሰባው ነሃሴ5የተጀመረሲሆንለ3 ሳምንት ያክል ይቆያል ተብሎ ይጠበቃል።

Read More »

የኢሳት 4ኛ አመት በኒውዚላንድ ተከበረ

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈዉ ቅዳሜ ኦገስት 2፣2014 በኒዉዚላንድ አገር በኦክላንድ ከተማ በተደረገዉ የኢሳት አራተኛ አመት በዓል አከባበር በርካታ ኢትዮጵያዉያኖች ቦታዉ ተገኝተው በአሉን አክብረዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባት የሆኑት የ በውጭ የሚገኘው ሲኖዶስ አባል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሳሙኤል ቃለ ቡራኬ የሰጡ ሲሆን፣ አቡነ ሳሙኤል ባደረጉት አጭር ንግግር ኢትዮጵያዉያኖች ይህንን ለ ኢትዮጵያ ሕዝብ አይንና ጆሮ ሆኖ እያገለገለ ያለ ...

Read More »

በቡርጅና ቦረና ኦሮሞዎች መካከል ያለው ችግር ተባብሶ መቀጠሉን መድረክ አስታወቀ

ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተለያዩ ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ባወጣው መግለጫ በቡርጅ ብሄረሰብና በቦረና ህዝብ መካከል ለዘመናት ሰፍኖ የኖረው መልካም ግንኙነት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጸረ-ሰላም ሃይሎች እየደፈረሰ እንደሚገኝ ገልጿል። ከ2 ሺ በላይ የሆኑ የቡርጅ ብሄረሰብ አባላት ከታህሳስ ወር 2006 ኣም ጀምሮ  ከአካባቢው ተፈናቅለው ወደ ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የሰገን ዞን በመሰደድ አስቸጋሪ ...

Read More »

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን በምርጫና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለማወያየት ስብሰባ ተጠራ

ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእረፍት ላይ የሚገኙ ነባር የዩኒቨርስቲ  ተማሪዎችን፣ የኮሌጅና የቴክኒክ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎችን እንዲሁም የዘንድሮውን የሁለተኛ ደረጃ ፈተና አልፈው ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎችን ስለመጪው ምርጫ እና ስለአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ለማወያየት በየክልሎች ስብሰባ መጠራቱ ታውቋል። ከነሃሴ 10 እስከ ነሃሴ 25 በሚቆየው ሰሚናር ላይ ተማሪዎች ምርጫውን ተከትሎ ስለሚፈጠሩ  ረብሻዎች፣ ስለአገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ትኩሳትና ስለ ገዢው ፓርቲ ፕሮግራርሞች በገዢው ...

Read More »

የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ባለቤትና አዘጋጆች ተሰደዱ

ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአንባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት የነበረው ሳምንታዊ መጽሔት ባለቤት  እና የመጽሔቱ ሶስት አዘጋጆች ሀገር ለቀው ተሰደዋል። የመጽሔቱ ባለቤት አቶ እንዳልካቸው ተስፋዬ ለኢሳት እንደገለጸው፤ እርሱና ጋዜጠኞቹ  በስርአቱ ሲደርስባቸው የነበረውን ወከባና አፈና ተቋቁመው የአዲስ ጉዳይ መጽሔትን  ህልውና ለማስቀጠል ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ፤ መጽሔቱዋ  በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍ ያለ ተቀባይነት ከማግኘቷም ባሻገር በገንዘብ አቅምም ረገድ ጥሩ ደረጃ ላይ መድረስ ...

Read More »

በመላ አገሪቷ የምግብ ነክ አግልግሎቶች እጥረት መፈጠሩን ታወቀ

ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ነዋሪዎች እንደሚገልጹት ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ የስኳር፣ የቡናና ዱቄት እጥረት ተፈጥሯል። በዱቄት እጥረት የተነሳ በተለይ በአማራ ክልል ሰዎች ዳቦ ለማግኘት ራጃጅም ሰልፎችን ተሰልፈው ወረፋ ለመተበቅ ተገደዋል። ቡና የመጨረሻ ደረጃ የሚባለው በኪሎ እስከ 100 ብር በመሸጥ ላይ ሲሆን፣ ሁለተኛና አንደኛ ደረጃ የሚባሉትን የቡና አይነቶች ፈልጎ ማግኘት አስቸጋሪ ሆናል ብለዋል። የስኳር ...

Read More »

የአዲስ አበባ የባቡር ፕሮጀክት ከመስተዳድሩ የመንገዶች ባለስልጣን ጋር ያለው ውዝግብ እንደቀጠለ ነው

ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪፖርተር የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፈቃዱ ሃይሌን ጠቅሶ እንደዘገበው ከባቡር ፕሮጀክቱ ጋር የተያያዙትን መንገዶች ከመምራት ጋር የተያያዘ ችግር አለ። ዋና ስራ አስኪያጁ ያለምንም ዝግጅትና እውቀት የአስፋልት መንገድ ይቆራጣሉ፣ በቅንጅትም ለመስራት ፈቃደኞች አልሆኑም በማለት ተናግረው፣ “የባቡር ኮርፖሬሽን ቦርድ አባል ሆኜ እንዲህ የተቸገርኩኝ እዚያ ውስጥ ያልገባ ሰው ቢሆን ምን ያደርግ ነበር ሲሉ ...

Read More »

የሂውማን ራይትስ ወች ባለስልጣናት ከግብጽ ተባረሩ

ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በግብጽ ከስልጣን በተወገዱት ሙሀመድ ሙርሲ ዳጋፊዎች ላይ የጸጥታ ሃይሎች  የወሰዱትን እርምጃ የሚዘረዝረውንሪፖርት ይፋ ለማድረግ ካይሮ የተገኙት የሂውማር ራይትስ ወች ዋና ስራ አስኪያጅ ኬኒስ ሮዝና ሌላዋ ከፍተኛ ባለስልጣን ሳራ ሊህ ወደ መጡበት አገር እንዲመለሱ ተደርጓል። ከ1500 በላይ የተገደሉበትን በአንዳንዶች ዘንድ እንደመፈንቅለ መንግስት የሚታየውን ድርጊት ሂውማን ራይትስ ወች በተደጋጋሚ ሲያወግዝ መቆየቱ ይታወቃል። የሰብአዊ መብት ድርጀቱ እንዲህ ...

Read More »

የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጡ መጠየቃቸውን ተቃወሙ

ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጹት የሰራዊቱ አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጡ በተጠየቁበት ወቅት ተቃውሞ አሰምተዋል። በባድሜ አካባቢ የሰፈሩት የመከላከያ አባላት በደሞዝ ክፍያ ሳምንት መነሻው 200 ብር ሆኖ በየደረጃው ያሉ ወታደሮች እንደ ማእረጋቸውና ደሞዝ መጠናቸው እንዲከፍሉ ሲጠየቁ፣ የሰራዊቱ አባላት ደሞዛችን አይቆረጥም በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል። ደሞዝ ከፋዮቹ ከላይ የመጣ መመሪያ ነው በሚል ሊያግባቡዋቸው ቢሞክሩም የሰራዊቱ አባላት ፈቃደኞች ...

Read More »