የኢሳት 4ኛ አመት በኒውዚላንድ ተከበረ

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈዉ ቅዳሜ ኦገስት 2፣2014 በኒዉዚላንድ አገር በኦክላንድ ከተማ በተደረገዉ የኢሳት አራተኛ አመት በዓል አከባበር በርካታ

ኢትዮጵያዉያኖች ቦታዉ ተገኝተው በአሉን አክብረዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባት የሆኑት የ በውጭ የሚገኘው ሲኖዶስ አባል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሳሙኤል ቃለ ቡራኬ የሰጡ ሲሆን፣ አቡነ ሳሙኤል ባደረጉት

አጭር ንግግር ኢትዮጵያዉያኖች ይህንን ለ ኢትዮጵያ ሕዝብ አይንና ጆሮ ሆኖ እያገለገለ ያለ ተቋም አቅም በፈቀደ ሁሉ መርዳት እንደሚገባ ተናግረዋል።

አቡነ ሳሙኤል አገራችን ዛሬ ላለችበት ዉድቀት መንስኤ የሆነዉ እኛ ኢትዮጵያዉያኖች አንድ ሆነን መቆም ባለመቻላችን መሆኑን ተናግረው፣ ከዚህ በሗላ በትልቅ በትንሹ መናቆሩ ቆሞ

ላገራችን ሰላም መሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ እጅ ለእጅ ተያይዞ ካለንበት ችግር እንዲወጣ ፈጣሪዉን መለመን ይገባል ብለዋል።

ይህ ለኢትዮጵያዉያኖች ድምፅ የሆነ ኢሳትንም መርዳት ጊዜዉ ከሚጠይቀን ምግባር አንዱ ነዉ በማለት ኢሳት መደገፍ ያለበት መሆኑን አቡነ ሳሙኤል ተናግረዋል።

የአልነጃሽ ሙስሊም ትረስት ተወካይ የሆኑት አቶ ጅብሪልም እንዲሁ ለዘመናት በሰላምና በፍቅር የኖረችዉ አገራችን ዛሬ ሰላም ርቋት ልጆቿ በየቦታዉ  በቃል የማይገለፅ ችግሮችን በአገር

ዉስጥም ካገር ዉጭም እየተስቃዩ በመሆናቸዉ ፣አላህ ከዚህ ሁሉ መከራና ችግር እንዲጠብቀን መጪዉ ጊዜም ኢትዮጵያዉያኖች  ከስደት ተመልሰዉ አገራቸዉ በሰላም ወጥተዉ በሰላም

የሚመለሱባት አገር ትሆን ዘንድ በአላህ ስም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የእለቱ የክብር እንግዳ ሆኖ የቀረበዉ የኢሳት ጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደዉ የኢሳትን አቋምና  ኢሳት ያለበትን ሂደት አሁንም እያደረገ ያለዉን በኢሳት ጥላ ስር የተሰባሰቡትንም ጋዜጠኞች ላገራቸዉ

ካላቸዉ ቀናይ አስተሳሰብ በመነሳት ለኢትዮጵያዉያን አማራጭ ድምፅ በመሆን እያገለገለ መሆኑን እና

በርካታ ኢትዮጵያዉያኖች ለኢሳት ወራዊ መዋጮ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን አንዱአለም ሃ/ማርያም ከኦክላንድ የላከው ዘገባ ያመለክታል።