የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን በምርጫና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለማወያየት ስብሰባ ተጠራ

ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእረፍት ላይ የሚገኙ ነባር የዩኒቨርስቲ  ተማሪዎችን፣ የኮሌጅና የቴክኒክ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎችን

እንዲሁም የዘንድሮውን የሁለተኛ ደረጃ ፈተና አልፈው ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎችን ስለመጪው ምርጫ እና ስለአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ለማወያየት

በየክልሎች ስብሰባ መጠራቱ ታውቋል። ከነሃሴ 10 እስከ ነሃሴ 25 በሚቆየው ሰሚናር ላይ ተማሪዎች ምርጫውን ተከትሎ ስለሚፈጠሩ  ረብሻዎች፣ ስለአገሪቱ

ወቅታዊ የፖለቲካ ትኩሳትና ስለ ገዢው ፓርቲ ፕሮግራርሞች በገዢው ፓርቲ አባላት ገለጻ ይሰጣል። ተማሪዎች በስብሰባው ላይ እንዲገኙ ጥሪ የተላለፈላቸው

ሲሆን፣ በፖለቲካ አቋማቸው የተሻሉ የሚባሉትን ለመመልመል እቅድ መያዙም ታውቋል። የኢህአዴግ የስልጠና ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ ለገሰ በቅርቡ በጻፉት

ጽሁፍ ኢህአዴግ በዩኒቨርስቲዎች ላይ ትኩረት በማድረግ አዳዲስ አባላትን በማፍራት ግንባሩ ያለበትን የአመራር እጥረት መቅርፍ ይቻላል ማለታቸው መዘገቡ ይታወቃል።