የመተማገንዳውሃአመራሮች በርካታ ችግሮች አሉብን ሲሉ ተናገሩ

ነሃሴ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢውን ህዝብ ለማወያየት የተንቀሳቀሱት ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ፣

ከተመረጡ የመተማ ገንዳውሃ ህዝብ መሪዎች፣ ከስርአቱ ደጋፊዎችና ከድርጅቱ ካድሬዎች ጋር ባደረጉት ውይይት የህዝብ ተወካዮች

የመልካም አስተዳዳር፣ የመሰረተ ልማትና የጸጥታ ችግሮችን አንስተው መንግስት አፋጣኝ መልስ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።ገንዳውሃ

የመብራት፣ የውሃ እና ሌሎች የመሰረተልማት ችግሮችን እንዳሉባት አንድ ተናጋሪ ገልጸዋል። የከተማዋ ወጣቶች ቀርፀው የላኩልን

የድምጽ መልእክት እንደሚያሳየው አንድ የኢህአዴግ ካድሬ የሱዳንሺፍታዎችእረኞችን  እየገደሉ፤ከብቶችን እየነዱወስደው

እንደሚያስቀሩባቸው ፣ ኢትዮጵያኖች ከሱዳን አንድ ነገር ሲወስዱ ግን የኢትዮጵያ መንግስት አሳዶንብረታቸውን እንደሚያስመልስላቸው

በትዝብት ተናግረዋል። ከኤርትራ የሚመጡት ታጣቂዎች ህዝቡን እያነሳሱ እንዲጋደል እያደረጉት ስለሆነ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ

አሳስበዋል አንዲት ሴት ተናጋሪ በበኩሏ በጤና ተቋማት የመድህኒትአቅርቦትአለመኖሩን፣ የመሬትይዞታ ጉዳይ ችግር መፍጠሩን ገልጻለች

“ግንቦት በመጣ ቁጥር ህዝቡ ይሰጋል፣ የእኛ መብራት ንፋስ በመጣ ቁጥር ይጠፋል፣ ምሰሶዎች ይወድቃሉ” ሲሉ የተናገሩ ሌላ አስተያየት

ሰጪ፣ ሰሞኑን ብቻ ከ300 አላነሱ ምሰሶችመውደቃቸውን ገልጸዋል።