የደቡብ ሱዳን አማጽያን በጋንቤላ ሆስፒታል እየታከሙ ነው

ነሃሴ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሪክ ማቻር የሚመራው በአብዛኛው የኑዌር ጎሳ አባላት ሆኑ የደቡብ ሱዳን አማጽያን

ቁስለኞች በጋምቤላ ሆስፒታል እየታከሙ መሆኑን የጋምቤላ ምንጮች ገልጸዋል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ተዋጊዎች የነጻ ህክምና

እየተሰጣቸው ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በተዘዋዋሪ መንገድ ለሪክ ማቻር ድጋፍ እንደምትሰጥ ያሳያል ሲሉ ምንጮች አስተያየታቸውን

አክለዋል። ከሳምንታት በፊት መንግስት 3 አውቶቡስ ሙሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ወደ አካባቢው የላከ ሲሆን፣ ምንጮች

እንደሚሉት የተላኩት ወታደሮች ለሪክ ማቻር ተዋጊዎች የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ ነው። መንግስት በበኩሉ የተላኩት የሰራዊት

አባላት  በድንበር አካባቢ ያለውን አለመረጋጋት ለማስቆም ነው ይላል። የአማጺው መሪ ሪክ ማቻር በቅርቡ በአዲስ አበባ ተደርጎ

በነበረው ጉባኤ ላይ አለመገኘታቸውን ተከትሎ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ማእቀብ እንደሚጣልባቸው አስጠንቅቀው ነበር። የፕ/ት

ሳልቫኪር መንግስት በይፋ በይገልጸውም ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አማጽያንን ትረዳለች ብሎ እንደሚያምን ቀደም ብሎ የወጡ

ዘገባዎች ያመለክታሉ።