(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 7/2011)የኦነግ አባላት ናቸው የተባሉ ታጣቂዎች ህብረተሰቡን መሳሪያ እየነጠቁ መሆናቸው ተገለጸ። በህጋዊ መንገድ ከመንግስት ፍቃድ ተሰጥቶን የታጠቅነውን መሳሪያ የኦነግ ታጣቂዎች ነን ባሉ ሃይሎች እየተወሰደብን ነው ሲሉ በወለጋ ቆሪና ሚንኮሎንጫ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነዋሪው ጥቃት ይደርስብናል በሚል ስጋት አከባቢውን ለቆ በመውጣት ላይ እንደሆነም የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በኦነግ ሰራዊት የመሳሪያ ነጠቃው መፈጸሙን በተመለከተ ከአመራሮች ምላሽ ለማግኘት ያአረግነው ጥረት አልተሳካም። ባለፈው ሳምንት በቤንሻንጉል ...
Read More »በአፋር ክልል የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የወጡ ዜጎች በልዩ ሃይል አባላት ጥቃት ደረሰባቸው
በአፋር ክልል የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የወጡ ዜጎች በልዩ ሃይል አባላት ጥቃት ደረሰባቸው ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 07 ቀን 2011 ዓ/ም ) የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን አንግበው በሰመራ ከተማ ወደ አደባባይ በወጡ ዜጎች ላይ የልዩ ሃይል አባላት በወሰዱት እርምጃ ቢያንስ 8 ሰዎች በጥይት ቆስለው ዱብቲ ሆስፒታል መግባታቸውን ነዋሪዎች በስልክ ለኢሳት ገልጸዋል። የመከላከያ ሰራዊት ገብቶ ግጭቱን ማስቆሙም ታውቋል። የአፋር ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት የክልሉ ...
Read More »ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የአርጎባ ብሄር ተወላጆች ከተጠለሉበት ትምህርት ቤት ተባረሩ። ለዜጎች መፈናቀል የወረዳ መስተዳሮች እጅ አለበት ተባለ።
ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የአርጎባ ብሄር ተወላጆች ከተጠለሉበት ትምህርት ቤት ተባረሩ። ለዜጎች መፈናቀል የወረዳ መስተዳሮች እጅ አለበት ተባለ። ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 07 ቀን 2011 ዓ/ም ) ከኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ቦሌ እና በምስራቅ ሸዋ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች በማንነት ላይ ባነጣጠሩ ጥቃቶች ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ቁጥራቸው ከ146 በላይ የሚሆኑ የአርጎባ ብሔር ተወላጆች አስታዋሽ አጥተን ለችግር ተዳርገናል አሉ። እስካሁንም በመንግስት በኩል በቂ ...
Read More »የኮሞሮስ ተቀናቃኞች ችራቸውን በሰላም እንዲፈቱ የአፍሪካ ኅብረት አሳሰበ
የኮሞሮስ ተቀናቃኞች ችራቸውን በሰላም እንዲፈቱ የአፍሪካ ኅብረት አሳሰበ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 07 ቀን 2011 ዓ/ም ) በኮሞሮስ አንጁዋን ደሴት በጸጥታ አስከባሪዎች እና ነፍጥ ባነገቱ ተቃዋሚዎች መሃከል በተፈጠረ ግጭት እስካሁን ሁለት ሰዎች ተገለዋል። ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እልባት እንዲያገኝ የአፍሪካ ኅብረት ለሁለቱም ወገኖች የሰላም ስምምነት ጥሪ አቀረበ። የኅብረቱ ፕሬዚዳንት ሙሳ ፋቂ ማህማት መንግስት እና ተቃዋሚዎች ከራሳቸው ጥቅም ይልቅ የአገራቸውን ዘላቂ ጥቅም ...
Read More »የአዲስ አበባ ወጣቶች እንዲፈቱ የተከፈተውን ዘመቻ ተከትሎ ሊፈቱ መሆኑ ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 6/2011)በጦላይ ወታደራዊ ካምፕ በስቃይ ላይ የሚገኙ የአዲስ አበባ ወጣቶች እንዲፈቱ የተከፈተውን ዘመቻ ተከትሎ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ እንደሚፈቱ ተገለጸ። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደግፌ በዲ ለቢቢሲ አማርኛው እንደገለጹት ከ1ሺህ በላይ የሚሆኑት ወጣቶች በዚህ ሳምንት መጨረሻ ይለቀቃሉ። ኮሚሽነሩ ወጣቶቹ የታሰሩት በጎዳና ላይ ንብረት ሲያወድሙና ሁከት ሲፈጥሩ ነው ብለዋል። ከአንድ ወር በላይ ሆናቸው። ክስ አልተመሰረተባቸውም። ፍርድ ቤትም ...
Read More »ሜቴክ እንደገና ሊደራጅ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 6/2011) የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ወታደራዊ ምርት የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎችን ለመከላከያ ሚኒስቴር በማስረከብ የብሄራዊ የኢንዱስትሪያል ምህንድስና ኮርፖሬሽን በሚል ስያሜ እንደገና ሊደራጅ ነው። የኮርፖሬሽኑ የኮሜርሻልና ሲቪል ምርቶች ኦፕሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልዓዚዝ መሀመድ እንደገለጹት ሜቴክ አዲሱን ስያሜ ይዞ የሲቪልና የንግድ ምርቶችን ብቻ የሚያመርት ይሆናል። የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ከብቃት እጦትና ከብክነት ጋር በተያያዘ ስሙ በተደጋግሚ ሲነሳ ቆይቷል። እጁ ላይ ...
Read More »የካቢኔ አባላት ሹመት ጸደቀ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 6/2011)የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 16 የካቢኔ አባላትን ሹመት አጸደቀ። በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አቅራቢነት ሹመታቸው የጸደቀው ሚኒስትሮች ከኢሕአዴግና አጋር ድርጅቶች የተውጣጡ ሲሆን ከተለመደው አሰራር ብዙም የተለወጠ ነገር እንዳልታየበትም አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። አራት ነባር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ከነሚኒስትርነታቸው በቀጠሉበት በአዲሱ ካቢኔ አዲስ የሰላም ሚኒስቴር በሚል ለተቋቋመው ተቋምም ሚኒስትር ተመድቦለታል። 28 የነበሩ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶችን ወደ 20 በሰበሰበው አዲሱ ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት 28 የነበረውን የሚንስቴር መስሪያ ቤቶች ቁጥር ወደ 20 ዝቅ አደረገ ፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት 28 የነበረውን የሚንስቴር መስሪያ ቤቶች ቁጥር ወደ 20 ዝቅ አደረገ ፡፡ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 06 ቀን 2011 ዓ/ም ) ዛሬ በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ እንደጸደቀው ከ 20 የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አስሩ በእንስት ሚኒስትሮች ተይዟል ፡፡ በኢትዮጵያ የሚኒስቴር መስሪያ ቤተቶች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የመከላከያ ሚኒስቴር እንስት ሚኒስትር ተሾሞለታል፡፡ አሁንም በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በርካታ ኃላፊነቶች ...
Read More »በምዕራብ ወለጋ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች የኦነግ ታጣቂዎች ከቄሮና አባገዳዎች ጋር በመሆን በማስተዳደር ላይ መሆናቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ
በምዕራብ ወለጋ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች የኦነግ ታጣቂዎች ከቄሮና አባገዳዎች ጋር በመሆን በማስተዳደር ላይ መሆናቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 06 ቀን 2011 ዓ/ም ) ኦነግ በሰየ ወረዳ ወየ ቡቡካ በሚባለው ቀበሌ ከጥቅምት 1 ቀን 2011 ዓም ጀምሮ የመንግስት ታጣቂዎችን እንዲሁም በአካባቢው ከ32 ዓመታት ላላነሰ ጊዜ የሰፈሩትን የአማራ ተወላጆች መንግስት ፈቅዶላቸው የያዙትን የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ፣ የወያኔ ታጣቀዊዎች ናችሁ በማለት ...
Read More »ፖሊስ ጦላይ ያሰራቸውን ከ1 ሺ በላይ እሰረኞች እንደሚፈታ አስታወቀ
ፖሊስ ጦላይ ያሰራቸውን ከ1 ሺ በላይ እሰረኞች እንደሚፈታ አስታወቀ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 06 ቀን 2011 ዓ/ም ) በአዲስ አበባ በነበረበው ብጥብጥ ተሳትፈዋል በሚል ፖሊስ በ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ውስጥ ከወር ላላነሰ ጊዜ በእስር ላይ ያቆያቸውን ከ1 ሺ 204 በላይ ወጣቶች፣ የፊታችን ሃሙስ ወይም አርብ ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል። ፖሊስ ወጣቶች ስልጠና እንደተሰጣቸው እየገለጸ ቢሆንም፣ ወጣቶችን ለፍርድ ሳያቀርብ እስካሁን አስሮ በማቆየቱ ...
Read More »