የኮሞሮስ ተቀናቃኞች ችራቸውን በሰላም እንዲፈቱ የአፍሪካ ኅብረት አሳሰበ

የኮሞሮስ ተቀናቃኞች ችራቸውን በሰላም እንዲፈቱ የአፍሪካ ኅብረት አሳሰበ
( ኢሳት ዜና ጥቅምት 07 ቀን 2011 ዓ/ም ) በኮሞሮስ አንጁዋን ደሴት በጸጥታ አስከባሪዎች እና ነፍጥ ባነገቱ ተቃዋሚዎች መሃከል በተፈጠረ ግጭት እስካሁን ሁለት ሰዎች ተገለዋል። ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እልባት እንዲያገኝ የአፍሪካ ኅብረት ለሁለቱም ወገኖች የሰላም ስምምነት ጥሪ አቀረበ። የኅብረቱ ፕሬዚዳንት ሙሳ ፋቂ ማህማት መንግስት እና ተቃዋሚዎች ከራሳቸው ጥቅም ይልቅ የአገራቸውን ዘላቂ ጥቅም ግምት ውስጥ ሊያስገቡ ይገባል ብለዋል።
ግጭቱ የተፈጠረው በህገ መንግስታዊ ህዝበ ውሳኔ ሶስቱ ዋና ዋና ደሴቶች በዙር በፕሬዝዳንታዊ ስልጣኑን እንዲቆጣጠሩ መወሰኑን ተከትሎ ነው። በወቅቱ ተዋሚዎቹ ድምጸ ተአቅቦ አድርገው ነበር። የወቅቱ የአገርቱ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ በህገወጥ መንገድ ስልጣናቸውን ይዘዋል ሲሉም ይከሳሉ። ፕሬዚዳንቱ ለሶስተኛ ጊዜ አገሪቱን መምራታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።