ፖሊስ ጦላይ ያሰራቸውን ከ1 ሺ በላይ እሰረኞች እንደሚፈታ አስታወቀ

ፖሊስ ጦላይ ያሰራቸውን ከ1 ሺ በላይ እሰረኞች እንደሚፈታ አስታወቀ
( ኢሳት ዜና ጥቅምት 06 ቀን 2011 ዓ/ም ) በአዲስ አበባ በነበረበው ብጥብጥ ተሳትፈዋል በሚል ፖሊስ በ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ውስጥ ከወር ላላነሰ ጊዜ በእስር ላይ ያቆያቸውን ከ1 ሺ 204 በላይ ወጣቶች፣ የፊታችን ሃሙስ ወይም አርብ ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል።
ፖሊስ ወጣቶች ስልጠና እንደተሰጣቸው እየገለጸ ቢሆንም፣ ወጣቶችን ለፍርድ ሳያቀርብ እስካሁን አስሮ በማቆየቱ ከፍተኛ ትችት እየደረሰበት ነው። ኢትዮጵያውያን ወጣቶቹ እንዲፈቱ በማህበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ ዘመቻ ሲያደርጉ ሰንብተዋል።
የአብይ አዲሱ መንግስት የቀድሞዎችን መሪዎች ድርጊት መልሶ እየደገመነ ነው በሚል ሲተች የሰነበተ ሲሆን፣ ለአብይ አስተዳደር ፍጹም ድጋፋቸውን ሲሰጡ የነበሩ በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተሳታፊዎች፣ አዲሱን አስተዳደር መጠራጠር መጀመራቸውን እየገለጹ ነው።