የኢትዮጵያ መንግስት 28 የነበረውን የሚንስቴር መስሪያ ቤቶች ቁጥር ወደ 20 ዝቅ አደረገ ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት 28 የነበረውን የሚንስቴር መስሪያ ቤቶች ቁጥር ወደ 20 ዝቅ አደረገ ፡፡
( ኢሳት ዜና ጥቅምት 06 ቀን 2011 ዓ/ም ) ዛሬ በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ እንደጸደቀው ከ 20 የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አስሩ በእንስት ሚኒስትሮች ተይዟል ፡፡
በኢትዮጵያ የሚኒስቴር መስሪያ ቤተቶች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የመከላከያ ሚኒስቴር እንስት ሚኒስትር ተሾሞለታል፡፡
አሁንም በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በርካታ ኃላፊነቶች የተሰጡት የሰላም ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተቋቁሟል ፡፡ የምክር ቤቱ አፈጉባዔ የነበሩት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልም የሰላም ሚኒስትር ሆነው ተሸመዋል