አርበኞች ግንቦት7 በኦሮምያና በጎንደር የተፈጸሙትን ግድያዎች አወገዘ

ኀዳር ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ሰበብ በከተማዋ ዙርያ ያሉ ወገኖቻችንን ማፈናቀል በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተፈፀመ ጥቃት ነው” ያለው አርበኞች ግንቦት7፣ በማስተር ፕላኑ ሰበብ የሚፈናቀሉ ገበሬዎች የሁላችን ወላጆች፣ ወንድሞችና እህቶች በመሆናቸው ይህንን ድርጊት በመቃወም ላይ ያሉት የኦሮሞ ተወላጅ ወገኖቻችን ትግል ፍትሀዊ በመሆኑ ንቅናቄው ከጎናቸው ይቆማል።” ብሎአል። በጎንደር ህወሓት ከሶስት ሺህ በላይ ዜጎቻችንን ...

Read More »

በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች የተነሳው ተቃውሞ አድማሱን እያሰፋ ነው

ኀዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል መንግስት ያወጣውንና የኦሮምያ ክልል ምክር ቤት ወይም ጨፌ ኦሮምያ በአዲስ አመት የስራ ዘመኑ ያጸደቀው አዲሱን የአዲስ አበባ ካርታ ተከትሎ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከደምቢዶሎ እስከ ሃረር ተዛምቷል። ተቃውሞውን ተከትሎ በብዙ የዩኒቨርስቲዎች፣ የሁለተኛና አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዴን) ሊቀመንበር አቶ በቀለ ነገዓ እንዲሁም የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ ...

Read More »

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከተለያዩ የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት ጋር ተነጋገሩ

ኀዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአርበኞች ግንቦት7 ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ትናንት ለአውሮፓ ህብረት አባላት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በማስመልከት ንግግር ካደረጉ በሁዋላ፣ ዛሬ ደግሞ ከህብረቱ የተለያዩ ሃላፊዎች ጋር ሲነጋገሩ ውለዋል። በዛሬው ውሎአቸው በአውሮፓ ህብረት የተለያዩ የፓርላማ ኮሚቴ አባሎችን፣ የኮሚሽኑንና የካውንስሉን የተለያዩ ባለስልጣኖችን ረጅም ሰአት ወስደው አነጋግረዋል። ነገና ከነገ ወዲያም የተለያዩ የህብረቱን ባለስልጣናት ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘዋል። በውይይታቸው ...

Read More »

በጎንደር እስር ቤት በደረሰ ቃጠሎ በርካታ እስረኞች ማለቃቸው ተነግሯል።

ኀዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባታ እስር ቤት ውስጥ በተነሳ ቃጠሎ አንዳንድ ወገኖች እስከ 30 ሰዎች መሞታቸውን ሲዘግቡ መንግስት በበኩሉ 17 ሰዎች መሞታቸውን ገልጿል። በርካታ እስረኞች በጠባቂ ፖሊሶች በተተኮሰባቸው ጥይት መሞታቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። እስከ 200 የሚጠጉ እስረኞች ማምለጣቸውንም መረጃዎች ያመለክታሉ። በአካባቢው መንግስት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ታጣቂ ሃይል አሰማርቷል።

Read More »

የኤሌክትሪክ ኃይል ለተከታታይ ቀናት መቆራረጥን ተከትሎ በአዲስ አበባ የዳቦ እጥረት እና ከወትሮው በተለየ መልኩ የውሃ ስርጭት መስተጓጎል ተከሰተ፡፡

ኀዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት አራት ቀናት በተከታታይ በመላ ሀገሪቱ የኤሌክትሪክ መቆራረጥን ተከትሎ ዳቦ ቤቶች በሙሉ አቅማቸው መስራት ባለመቻላቸው በርካታ ዳቦ ቤቶች ደንበኞቻቸውን ማስተናገድ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ አንድ የሁለት ልጆች አባት እንደሆነ የተናገረ ነዋሪ ሰሞኑን ዳቦ ቤቶች ጠዋት አንድ ሰዓት ግድም ጀምሮ ዳቦ አልቆአል ስለሚሉ ልጆቹ ቁርሳቸውን ሳይመገቡ እንደሚያረፍዱ ጠቅሶአል፡፡ ያነጋገርናቸው የዳቦ ቤቶች ባለቤቶች የመብራቱ መቆራረጥ ...

Read More »

የኢትዮጵያ የድንበር ኮሚቴ ከሱዳን ጋር ያለውን ድንበር ለማካለል የሚደረገውን እንቅስቃሴ አወገዘ

ኀዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በህወሃት የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች የኢትዮጵያን ሕዝብ ሳያማክሩና ታሪካዊ ተግዳሮቶችን ከግምት ሳያስገቡ ለዘመናት በኢትዮጵያ ስር የነበሩትን ድንበሮች ለሱዳን አሳልፈው ለመስጠት የሚያደርጉትን ሚስጥራዊ ድርድሮች በአፋጣኝ አቁመው ሕጋዊን መንገድ እንዲከተሉ ማሳሰቢያቸውን ሰጥተዋል። ቁጥራቸው 25 የሚሆኑት የሲቪክና የፖለቲካ ማህበራት በጋራ ያቋሙት የኢትዮጵያ የድንበር ኮሚቴ፣ የአገሪቱ ሉአላዊ ህልውና ለ አደጋ የሚያጋልጡና ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት በቀጣናው ...

Read More »

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሠራተኞች ከፍተኛ ክስ ቀረበባቸው፡፡

ኀዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሳሞንት የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞችና መምህራን ለትምህርት ሚኒስቴሩ ሽፈራው ሽጉጤ ሰብስበው እንዲያነጋግሯቸው በፃፉት ደብዳቤ መሰረት ሚኒሰቴሩ በዩኒቨርሲቲው ግቢ በመገኘትና ስብሰባ በማዘጋጀት ያነጋገሯቸው ሲሆን ፣ በስብሰባው የተገኙት ታዳሚዎች ተራ በተራ እየተነሱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት በሆኑት ዶ/ር ስለሺ ቆሬ ላይ 29 የሚደርሱ በማስረጃ የተደገፉ የተቃውሞ ክሶችን አሰምተዋል፡፡ በፕሬዝዳንቱ የግል የባንክ አካውንት ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ...

Read More »

የጎንደር ማረሚያ ቤት በእሳት ጋየ እስረኞችም ተገደሉ

ኀዳር ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎንደር ከተማ የሚገኘውና ባሕታ በመባል የሚጠራው ማረሚያ ቤት ግቢ ውስጥ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ማረሚያ ቤቱ ከፍተኛ የሆነ አደጋ የደረሰበት ሲሆን ቁጥራቸው ከ30 እስከ 50 የሚሆኑ ታራሚዎች መገደላቸውንና ከ300 እስከ 500 በላይ የሚሆኑ እስረኞች ደግሞ አምልጠው ከሕዝቡ ጋር ሲቀላቀሉ ከ100 በላይ የሚሆኑት እስረኞች በእሳት ቃጠሎው ጉዳት ደርሶባቸዋል። የፌዴራል ፖሊሶች ከውስጥና ከውጭ የተኩስ ...

Read More »

በሃሮማያ ዩንቨርሲቲ የተማሪዎች አመጽ አሁንም አልበረደም

ኀዳር ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሃሮማያ ዩንቨርሲቲና በተለያዩ ዩንቨርሲቲዎች ውስጥ የሚገኙ የኦሮሚያ ተወላጆች የሆኑ ተማሪዎች አዲሱ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን አርሶአደሮችን ከቀያቸውና ከእርሻ ማሳቸው ላይ ያፈናቅላል በማለት ቁጣቸውን በሰላማዊ ተቃውሞ የገለጹ ቢሆንም መንግስት እንደተለመደው የኃይል እርምጃ ወስዷል። ተቃውሞ ለማፈን በተወሰዱ እርምጃዎች የፌደራል ልዩ ጦር በማሰማራት ግድያና አካላዊ ጥቃት ተፈጸሟል። በዚህም ሳቢያ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ...

Read More »

አርቲስት ግርማዬ ታደሰ ልማታዊ አርቲስቶችን ማዋረድ የሚል ክስ ቀረበበት

ኀዳር ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰዎች ምን ይላሉ የተሰኘው ኮሜዲ ድራማ አዘጋጆች ለእስር እየተዳረጉ ሲሆን አርቲስቶቹ ልማታዊ አርቲስቶችን ማዋረድ የሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል።ከአዘጋጆቹ አንዱ የሆነው አርቲስት ግርማዬ ታደሰ እስካሁን ድረስ ለሶስት ሳምንታት በእስር እንደሚገኝ የታወቀ ሲሆን ዋና አዘጋጁ በዋስና ወጥተዋል። ሰዎች ምን ይላሉ የሚለው ኮሜዲ ፊልም ታትሞ ለገበያ ከቀረበ ከዓመት በላይ የቆየ ሲሆን ልዩ ልዩ የማኅበረሰቡን እለታዊ ...

Read More »