በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች ተማሪዎች ተቃውሞ እያሰሙ ነው

ኀዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት የአዲስ አበባን አስተዳደር ለማስፋት ያዘጋጀው አዲሱ የመሬት ካርታ ወይም ማስተር ፕላን ተግባራዊ እንደሚደረግ የመንግስት ባለስልጣናት የተለያዩ መግለጫዎችን መስጠታቸውን ተከትሎ፣ የክልሉ ተማሪዎች ተቃውሞአቸውን እየቀጠሉ ሲሆን፣ በአምቦ፣ ኤሉባቦር፣ በምእራብ ወለጋና በሌሎችም የተካሄዱት ተቃውሞዎች ወደ ሃሮማያ (አለማያ)ዩኒቨርስቲ ተዛምቶ፣ በተማሪዎችና በፖሊስ መካከል በተነሳው ግጭት፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተማሪዎች ተጎድተው ሆስፒታል ገብተዋል። ተማሪዎቹ ተቃውሞአቸውን በሰላም በማሰማት ...

Read More »

በሃረሪ ፖሊስና መከላከያ መካከል በተፈጠረው ግጭት ሃረር ሰላም አጥታ ሰነበተች

ኀዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከተማዋ ውጥረት ነግሶ መሰንበቱን የገለጸው ወኪላችን፣ መንስኤውም አንድ የመከላከያ ሰራዊት አባል ተደብድቦና በጥይት ተመትቶ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን ተከትሎ ነው። ውጥረቱን ተከትሎ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ትራፊክ ዋና አዛዥ ኮማንደር አብዲ ኢብራሂም የተሰወሩ ሲሆን፣ በመከላከያ ሰራዊት አባላት በጥብቅ እየተፈለጉ ነው። ጉዳዩን ለማጣራት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር በከተማዋ የተገኙ ሲሆን፣ የክልሉ ...

Read More »

በሰሜን ወሎ ጠረፋማ ቀበሌዎች የቁም እንስሳት እየሞቱ መሆኑ ተነገረ፡፡

ኀዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፋር አጎራባች በሆኑ 15 ቀበሌዎች የድረቁ ሁኔታ እየተባባሰ በመምጣቱ ከ500 በላይ የቁም እንስሳት መሞታቸውን የሐብሩ ወረዳ የግብርና ባለሙያዎች ተናገሩ፡፡ ዝናቡ ለአንድ ወር በመዘግየቱ በሃምሌ ወር መጨረሻ መዝነቡ የሰብሉን እድገት ማስተጓጎሉን የሚናገሩት ባለሙያ፣ በወረዳው ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው የከብት መኖ እጥረት ቆላማ በሆኑ አካባቢዎች አሁንም ችግሩ ተባብሶ በመቀጠሉ በነዋሪው ላይ ከፍተኛ ስጋት ማሳደሩን ተናግረዋል፡፡ ...

Read More »

በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ችግር በከፋ ሁኔታ ተባባሰ።

ኀዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ቅዳሜ፣ እሁድ እና ሰኞ ባል ድፍን አዲስ አበባ ጭለማ ውጧታል። ካለፉት ሁለት አመታት ወዲህ የሃይል መቆራረጡ እየተባባሰ የመጣ ሲሆን የመንግስት ሹማምንት አንዴ ችግሩ የመልካም አስተዳደር ብልሽት ውጤት ነው፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ የመስመር እርጅና ነው እያሉ ፣ እርስበርሱ የተምታታ መግለጫ ከመስጠት ባለፈ ሁነኛ መፍትሄ ሳያበጁለት ቀርተዋል። ችግሩ በተባባሰበት ባለፉት ሁለት ቀናት ዳቦ ...

Read More »

223 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ከማላዊ ወደ አገራቸው ተመለሱ

ኀዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዓለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት IOM ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ ማላዊ ላይ ተይዘው በእስር ቤት ውስጥ ሲንገላቱ የነበሩትን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን አሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በሰጡት 9 ሺ የአሜሪካ ዶላር ቁጥራቸው 223 የሚሆኑትን በቻርተር አውሮፕላን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል። እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከመስከረም ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ ድርጅቱ ወደ ትውልድ አገራቸው እንዲመለሱ ያደረገ ሲሆን ...

Read More »

ከአንድ ሺ ያላነሱ የአዲስ አበባ ፖሊሶች የሥራ መልቀቂያ አስገብተው በመጠባባቅ ላይ ናቸው

የፖሊስ ምንጮች እንደገለጹት በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ ስራቸውን ለመልቀቅ ማመልከቻ ያስገቡ ፖሊሶች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል።7 አመት ያላገለገሉ ፖሊሶች ያገለገሉበት ዘመን ታስቦ ገንዘብ ከፍለው የሚሰናበቱ ሲሆን፣ ይህንን ክፈተት በመጠቀም ብዙዎች ስራውን እየለቀቁ ሄደዋል። ከፖሊስ የሰው ሃይል ክፍል የደረሰን አስተማማኝ መረጃ እንደሚያሳያው መልቀቂያ አስገብተው ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ፖሊሶች 1 ሺ ይደርሳሉ። ብዙዎች ለመልቀቃቸው የሚሰጡት ምክንያት ከስራ ጫና፣ ከአስተዳደር፣ ዘረኝነትና ...

Read More »

የአዲስ አበባ የተለያዩ ወረዳዎች ተወካዮች የተባሉ መንግስት አይሰማንም አሉ

ኀዳር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሁለተኛውን የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አስመልከቶ የህዝብ ተወካዮች ናቸው ከተባሉ ሰዎች ጋር የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ በውይይቱ ተወካዮች በየአካባቢው የሚታዩ ችግሮችን ተናግረዋል። የህዝብ ተወካዮቹ ” ብንናገርም የሚሰማን መንግስት” የለንም ብለዋል። ምንም እንኳ ብዙዎቹ ተወካዮች ለገዢው ፓርቲ ካላቸው ቀረቤታ እና በድርጅት አባልነት ተመርጠው የመጡ ቢሆንም ፣ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ በነበረው ...

Read More »

የተባበሩት መንግስታት የረድኤት ክፍል በኢትዮጵያ የሚታየውን ድርቅ የተመለከተ ፎቶግራፍ ይፋ አደረገ

ኀዳር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ ድርቁ እያስከተለ ያለውን ጉዳትና የደቀነውን ፈተና ወደ ተለያዩ ቦታዎች በመዟዟር በፎቶ ግራፍ በማስደገፍ አቅርቧል። በሰሜን ወሎ ዳውንት ወረዳ የሚኖሩት አርሶአደርን፣ የስንዴ ማሳቸው በዝናብ እጥረት የተነሳ ደርቆባቸው ሃሳብ ገብቷቸው ይታያሉ በጊዳን፣ ዳውንት፣ አበርጌሌ ወረዳዎች የጤፍ፣ የስንዴ፣ የዳጉሳና የማሽላ ማሳዎች በዝናብ እጥረት ምክንያት ደርቀው መሬቱም ተሰነጣጥቆ ይታያል። በአፋር ፋንቲ ዞን ያሎ ወረዳ ...

Read More »

105 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ታንዛኒያ ውስጥ ተያዙ

ኀዳር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሕገወጥ መንገድ ወደ ታንዛኒያ ግዛት ገብተዋል ተብለው የተጠረጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በዋና ከተማዋ ዳሬሰላም ውስጥ መያዛቸውን የከተማዋ የፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ሱሌይማን ኮቫ ገልጸዋል። አዛዡ ቁጥራቸው 105 የሚሆኑ ያሉዋቸውን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በዳሬሰላም በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተደብቀው መያቻውን ገልጸዋል። ስደተኞቹን ጨምሮ ሕገወጥ የሰው ዝውውር ሥራ ይሰራል የተባለው የ25 ዓመቱ ሩዋንዳዊ ዜጋም ተይዟል። በስደተኞች ...

Read More »

ኢትዮጵያዊቷ ሯጭ ገንዘቤ ዲባባ በረዥምና መሃከለኛ ርቀት ሩጫ የዓመቱ ኮከብ ተብላ ተመረጠች

ኀዳር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዓለምአቀፉ አትሌቲክስ ማኅበር እንደ አውሮፓዊያን ዘመን አቆጣጠር የ2015 ዓ.ም የዓመቱ ኮከብ ሯጮች በማለት ኢትዮጵያዊቷ ትንሿ ልዕልት ገንዘቤ ዲባባ እና አሜሪካዊው አሽተን ኤተንን መርጧል። የ24 ዓመቷ ወጣት የበቆጂ ፍሬ ገንዘቤ ዲባባ በዓመቱ ውስጥ በ1 ሽህ 500 ሜትር የሩጫ ውድድር በፈረንሳይ ሞናኮ እርቀቱን በ3 ደቂቃ 50.07 ሰከንድ ክብረወሰን ከመስበሯም በተጨማሪ በቻይና ቤጅንግ የአለም ...

Read More »