በጎንደር እስር ቤት በደረሰ ቃጠሎ በርካታ እስረኞች ማለቃቸው ተነግሯል።

ኀዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባታ እስር ቤት ውስጥ በተነሳ ቃጠሎ አንዳንድ ወገኖች እስከ 30 ሰዎች መሞታቸውን ሲዘግቡ መንግስት በበኩሉ 17 ሰዎች መሞታቸውን ገልጿል።
በርካታ እስረኞች በጠባቂ ፖሊሶች በተተኮሰባቸው ጥይት መሞታቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። እስከ 200 የሚጠጉ እስረኞች ማምለጣቸውንም መረጃዎች ያመለክታሉ። በአካባቢው መንግስት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ታጣቂ ሃይል አሰማርቷል።