ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከተለያዩ የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት ጋር ተነጋገሩ

ኀዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአርበኞች ግንቦት7 ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ትናንት ለአውሮፓ ህብረት አባላት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በማስመልከት ንግግር ካደረጉ በሁዋላ፣ ዛሬ ደግሞ ከህብረቱ የተለያዩ ሃላፊዎች ጋር ሲነጋገሩ ውለዋል።
በዛሬው ውሎአቸው በአውሮፓ ህብረት የተለያዩ የፓርላማ ኮሚቴ አባሎችን፣ የኮሚሽኑንና የካውንስሉን የተለያዩ ባለስልጣኖችን ረጅም ሰአት ወስደው አነጋግረዋል።
ነገና ከነገ ወዲያም የተለያዩ የህብረቱን ባለስልጣናት ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘዋል። በውይይታቸው ስለወቅታዊው የኢትዮጵያ ችግር ዝርዝር ማብራሪያና የመፍትሄ ሀሳብ ያሉትን አቅርበዋል።