(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 14/2011)ቀጣዩን ሐገር አቀፍ ምርጫ በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ መያዛቸው ተገለጸ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ዛሬ ይፋ ባደረገው የጥሪ ደብዳቤ በቀጣዩ ማክሰኞ ህዳር 18/2011 በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት በሚካሄደው የውይይት መድረክ የሁሉም የፖለቲካ አመራሮች ተጋብዘዋል። “በሃገራችን ስለተጀመረው የዲሞክራታይዜሽን ጉዞና በሚቀጥለው አመት የሚደረገውን ሃገራዊ ምርጫን ነጻና ፍትሃዊ ለማድረግ ሊወሰዱ በሚገባቸው የሪፎርም ስራዎች ዙሪያ ...
Read More »የደቡብ አቸፈር አመራሮች በሕዝብ ተቃውሞ ከሃላፊነታቸው ተነሱ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 14/2011) በአማራ ክልል የደቡብ አቸፈር ወረዳ አመራር አባላት በሕዝብ ተቃውሞ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደረገ። ቁጥራቸው 42 ይሆናል የተባለው የወረዳው አመራር አባላት ከለውጡ ጋር የማይሄዱ ስልጣን ይዘው ሕዝቡን ሲበድሉ የነበሩ ናቸው ተብሏል። የወረዳው ዋና ከተማ ዱርቤቴ ወደ ከተማ አስተዳደርነት እንድትሸጋገር ይዞን አስተዳደሩም ከፍኖተሰላም ወጥቶ ወደ ባህርዳር ምዕራብ ጎጃም ዞን እንዲዛወርም ሕዝቡ በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቋል። የደቡብና ሰሜን አቸፈር ሁለት ወረዳዎች ትርፍ ...
Read More »በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ግጭት የሚፈጥሩ አካላት አሉ ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 14/2011) የውጭ አጀንዳ ወይም ተልዕኮ ተሰጥቷቸው በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ግጭት የሚፈጥሩና የሚያውኩ አካላት እንዳሉ የሳይንስና ክፍተኛ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። በሃገሪቱ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ግጭቶች መፈጠራቸው ታውቋል። የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የግለሰቦች ግጭት ወደ ቡድን ወይም አካባቢ ወስዶ በተደራጀ ሁኔታ ተማሪዎችን ማጋጨት በምንም መንገድ ተቀባይነት አይኖረውም ብለዋል፡፡ ‘’ወደ አማራ ክልል የሚመጡ የየትኛውም አካባቢ ተማሪዎች የአማራ ልጆች ናቸው፡፡›› ...
Read More »የጥላቻ ንግግር ላይ አዲስ ህግ ሊወጣ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 14/2011) ኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግር ላይ አዲስ ህግ ልታወጣ መሆኗን አስታወቀች። ጠቅላይ አቃቤ ህግ የጥላቻ ንግግርን የተመለከተና ተጠያቂነትን የሚያመጣ አዲስ ረቂቅ ህግ እያዘጋጀ መሆኑን ገልጿል። የጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ አቶ ዝናቡ ቱኑ እንደገለጹት በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተስፋፉ የመጡት ሃላፊነት የጎደላቸው መልዕክቶችና የሀሰት ወሬዎች በሀገሪቱ ለሚከሰቱ ግጭቶች ምክንያት በመሆናቸው መንግስት ይህን አደጋ ለማስወገድ ህጋዊ ተጠያቂነት እንዲኖር የሚያስችል አሰራር በማርቀቅ ...
Read More »ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆኑ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 13/2011) ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ በመሆን በፓርላማው ተመረጡ። የወይዘሪት ብርቱካን በምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት መመረጥ ቀጣዩ ምርጫ እንዳይጭበረበርና ጨርሶውንም የማጭበርበር ዝንባሌ እንዳይኖረው ያግዛል ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናግረዋል። በመንግስትና በገዢው ፓርቲ ላይ ሲቀርብ የነበረውን ክስም የሚያስቀር ርምጃ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገልጸዋል። ወይዘሪት ብርቱካን ለሰብሳቢነት ሲታጩ ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች እንዲሁም ከሌሎች ወገኖች ጋር ...
Read More »ወንጀል የፈጸሙ ሰዎችን በሙሉ ለማሰር ቢታሰብ ያሉት እስር ቤቶች አይበቁም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 13/2011)በኢትዮጵያ ባለፉት 27ና 30 አመታት ወንጀል የፈጸሙ ሰዎችን እንሰር ብንል የሃገሪቱ እስር ቤት ስለማይበቃ ከተማ መገንባት ይኖርብናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ገለጹ። ከሰሞኑ እየታሰሩ ካሉ ሰዎች ጋር በተያያዘ የሚነሱ ተቃውሞዎችን እንደመብት የተቀበሉት ዶክተር አብይ አህመድ ሕግ ማክበርና ማስከበር ግዴታ መሆኑን ግን በአጽንኦት ተናግረዋል። የፓርላማ አባላት ውድቅ ያደረጉትን የቋሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫንም በተመለከተም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በርምጃቸው ቅሬታ እንደሌላቸውና ...
Read More »በሶማሌ ክልል የጅምላ መቃብሮች ፍለጋ ተጠናቀቀ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 13/2011)በሶማሌ ክልል ባለፉት 10 ዓመታት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለው የተቀበሩባቸው የጅምላ መቃብሮች ፍለጋ መጠናቀቁን የክልሉ መንግስት አስታወቀ። የክልሉ መንግስት ይፋ እንዳደረገው መረጃም የጅምላ መቃብሮቹን አጠቃላይ መረጃም ለሚመለከተው አካል ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለም በሶማሌ ክልል ተገድለው በጅምላ የተቀበሩበትን የ200 ሰዎችን የምርመራ ሒደት ማጠናቀቁን ፖሊስ አስታውቋል። የተገደሉት ዜጎች በቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ዒሌ የስልጣን ዘመን የጸረ ...
Read More »ኢትዮጵያ ጋዜጠኛ በእስር ቤት የማይገኝባት ሀገር ናት ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 13/2011)ኢትዮጵያ በ13ዓመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋዜጠኛ በእስር ቤት የማይገኝባት ሀገር መሆኗ ተገለጸ። የዓለም ዓቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ የቦርድ አባል ካትሊን ካሮል ሰሞኑን በኒዮርክ የተዘጋጀውን ፕሮግራም አስመልክተው እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እስር ቤቶች የታሰረ ጋዜጠኛ የለም። ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ የጋዜጠኞችን እስር በቅርበት እየተከታተለ ሪፖርት የሚያቀርበው ሲፒጄ በወቅቱ የነበረው የኢትዮጵያ አገዛዝ ከአፍሪካ ሁለተኛው የጋዜጠኞች ቀበኛ አገዛዝ ...
Read More »የኦብነግ ሰራዊት ሀገር ቤት ገባ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 12/2011) የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ኦብነግ ሰራዊት ትጥቁን ፈቶ ወደ ሀገር ቤት ገባ። የኦብነግ ወደ ሰላማዊ ትግል መግባት ለሶማሌ ክልል ህዝብ ታላቅ የምስራች ነው ሲል የክልሉ መንግስት አስታውቋል። ትጥቁን ፈቶ ለገባው የኦብነግ ሰራዊትም በጂጂጋ አቀባባል ተደርጎለታል። በሌላ በኩል በእስር ላይ በሚገኙት የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ዒሌ የተደራጀውና የክልሉን ሰላምና ደህንነት በማናጋት ነዋሪዎች ላይ አደጋ ሲጥል የቆየው ሄጎ ...
Read More »በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ግጭቶች ተቀሰቀሱ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 12/2011) በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ግጭቶች መቀስቀሳቸው ተገለጸ። በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ዩኒቨርስቲ በተነሳው ግጭት ሶስት ሰዎች ተገድለዋል። 34 ሰዎችም ክፉኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። በቴፒ ሳምንታት የዘለቀው ግጭት አሁንም አልበረደም። በልዩ ሃይል በርካታ ሰዎች ተደብድበው ሆስፒታል ገብተዋል። በአፋርም የህዝብ ተቃውሞ ቀጥሏል። በቢሾፍቱ ደብረዘይት ቄሮ ነን ባሉ ወጣቶች ሱቃችንን ልቀቁ እየተባልን ነው ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል። በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች መለስተኛ ...
Read More »