ወንጀለኞችን እያደኑ ለፍርድ የማቅረቡ ተግባር ይቀጥላል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ህዳር 6/2011)ወንጀለኞችን እያደኑ ለፍርድ የማቅረቡ ተግባር እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ገለጹ። ኢትዮጵያ ቢሊየን ብር የመዘበሩ በነጻነት የሚኖሩባትና አንድ ብር አጥተው ከቆሻሻ ገንዳ ምግብ የሚፈልጉ ሁለት አይነት ዜጎች ሊኖሩባት አይገባም ሲሉም አሳስበዋል። አራዊት እንኳን የማይፈጽመውን ኢሰብአዊ ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎች ለወገናቸው ሊራሩ አይችሉም ሲሉም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ እየተወሰደ ያለውን መንግስታዊ ርምጃ በተመለከተ “ካንሰርን በጋራ እንከላከል” በሚል ...

Read More »

የ205 ግለሰቦች የባንክ ሒሳብ ታገደ

(ኢሳት ዲሲ–ህዳር 6/2011) የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የ205 ግለሰቦች የባንክ ሒሳብ እንዲታገድ አደረገ። ፌደራል ፖሊስ በቀድሞ የደህንነትና የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮችና ቤተሰቦቻቸው ስም የተከፈቱ የባንክ ሂሳቦች መረጃ እንዲሰጠው በጠየቀው ደብዳቤ በተጠርጣሪዎቹ ግለሰቦች ሚስትና ልጆቻቸው ስም የተከፈቱትን በዝርዝር ገልጿል። በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ የሜቴክ ሃላፊዎች ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ የ147 ሰዎች የባንክ ሂሳብ በሙስና ተጠርጠረው የባንክ ሂሳባቸው ሲታገድ የአቶ ...

Read More »

ኮለኔል ገብረእግዚአብሔር አለምሰገድ በቁጥጥር ስር ዋሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 6/2011) በሶማሊያ የኢትዮጵያ ጦር አዛዥና በኢጋድ የዋና ጸሃፊው የፖለቲካ አማካሪ ኮለኔል ገብረእግዚአብሔር አለምሰገድ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ። በኮንትሮባንድ ንግድና በሶማሌ ክልል በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እጃቸው እንዳለበት የሚጠረጠሩት ኮለኔል ገብረእግዚያብሄር ባለፈው ሳምንት በጂጂጋ ከተፈጠረው ግጭት ጋር በመሪነት እንደተሳተፉ ይነገራል። ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ በወታደራዊ መረጃ ዋና መምሪያ ለ10 ተከታታይ አመታት የቆዩት ኮለኔል ገብረእግዚያብሄር በሃገር ሃብት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ካደረሱ ...

Read More »

በኤርትራ ላይ ተጥሎ የነበረው ማዕቀብ ተነሳ

(ኢሳት ዲሲ–ህዳር 5/2011) በኤርትራ ላይ ተጥሎ የነበረው ማዕቀብ መነሳቱ ተገለጸ። ለዘጠኝ ዓመታት የተጣለው ማዕቀብ  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ በሙሉ ድምጽ በመወሰን አንስቶታል። ኤርትራ ውሳኔውን የዘገየ፡ ማዕቀቡም ህገወጥ ስትል ገልጻለች። የኢትዮጵያ መንግስትም በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ በመነሳቱ ደስታውን ገልጿል። የማዕቀብ መነሳት የውሳኔ ሀሳብ የረቀቀው በእንግሊዝ መንግስት ሲሆን ባለፈው መስከረም ወር በመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ...

Read More »

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልኡካን መወያየት ጀመሩ

(ኢሳት ዲሲ–ህዳር 5/2011) የኢትዮጵያን የምርጫ ስርአት ለመገምገም ኢትዮጵያ የገቡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልኡካን ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር መወያየት ጀመሩ። ላለፉት ሁለት ሳምንታት ያህል በኢትዮጵያ የሚገኙት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቴክኒክ ቡድን አባላት በኢትዮጵያ የምርጫ ሕግና በምርጫ ስርአቱ ላይ ከሚመለከታቸው ወገኖች ጋር በመወያየት ላይ መሆናቸው ተመልቷል። ከአንድ አመት ተኩል በኋላ ይካሄዳል በሚል አስቀድሞ መርሃ ግብር የተያዘለትን ምርጫ በተመለከተ እየተደረገ ...

Read More »

በሕገ ወጥ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦችን በህግ ቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባር ይቀጥላል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 5/2011) በሕገ ወጥ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦችንና ግብረ አበሮቻቸውን በህግ ቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባር  ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢሕአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ገለጸ። የክልል መንግስታትም በህገ ወጦች ላይ የሚወሰደውን ርምጃ በመደገፍ መግለጫ አውጥተዋል። የኢሕአዴግ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ ከእንግዲህ የህዝቡ ቅሬታ  ምላሽ ሳያገኝ እንዲቆይ ማድረግ የሚቻልበት አንዳችም መንገድ የለም። ከፍተኛ የሕዝብ ቅሬታና እሮሮ ከሚሰማባቸው ውስጥ ሀገራዊ የፍትህ ስርዓቱ በሀገሪቱ የተንሰራፋውን ...

Read More »

ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው መንግስት ጠበቃ ያቁምልኝ አሉ

(ኢሳት ዲሲ–ህዳር 5/2011) ከሃገር ሲያመልጡ ድንበር ላይ ተይዘው ፍርድ ቤት የቀረቡት ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው መንግስት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ጠየቁ። በቢሊየን ብር ምዝበራና ብክነት ተጠያቂ ነዎት በሚል ፍርድ ቤት የቀረቡት ጄኔራል ክንፈ ዳኘው መንግስት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው የጠየቁት አቅም የለኝም በሚል መሆኑ ታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም በሰብአዊ መብት ረገጣና መሰል ወንጀሎች ከሚፈለጉት አንዱ የሆኑት አቶ ያሬድ ዘሪሁንን አስመልጠዋል የተባሉ ሰዎች ዛሬ ፍርድ ...

Read More »

የአሳይታ መምህራን ኮሌጅ ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ መቱ

(ኢሳት ዲሲ–ህዳር 5/2011) የአሳይታ መምህራን ኮሌጅ ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ መምታታቸው ተገለጸ። በአፋር ክልል በህዝቡ የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማስቆም በክልሉ መንግስት እየተወሰደ ያለው አፈናና እስራት እስኪቆም ትምህርት እንደማይጀምሩ ተማሪዎች አስታውቀዋል። በሌላ በኩል በአፋር የሚካሄደው ተቃውሞ ቀጥሎ በዛሬው ዕለት ሎጊያ በተሰኘችው ከተማ ለውጥ እንፈልጋልን በሚል ተቃውሞ መካሄዱን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በሳምንቱ መጨረሻም በተለያዩ የአፋር ከተሞች ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ መደረጉ ተገልጿል።  

Read More »

በመስቃንና ማረቆ ወረዳዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ሰዎች ተጎዱ

(ኢሳት ዲሲ–ህዳር 5/2011)በመስቃንና ማረቆ ወረዳዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ሰዎች መጎዳታቸው ተገለጸ። በእስካሁኑ ግጭት ከ15 በላይ ቤቶች በእሳት መጋየታቸውም ተሰምቷል። ይሄ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ በሃሙስ ገበያ፣በኢንሴሮ ከተሞችና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉን፣ የሰው ሕይወት ማለፉንና በርካታ ቤቶች በእሳት እየተቃጠሉ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ወደ አካባቢው የተላከው ሃይል ቁጥር አነስተኛ መሆንና የግጭቱ ስፋት አለመመጣጠን ለችግሩ መፍትሄ ሊያስገኝ አልቻለም ተብሏል። ለሁለቱ ...

Read More »

በሞያሌ ግጭት ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 5/2011)በሞያሌ ግጭት ተቀሰቀሰ። ባለፉት ሶስት ቀናት በተደረገ ግጭት 12 ሰዎች መገደላቸው ታውቋል። ያዝ ለቀቅ ሲያደርግ የነበረው ግጭት ከእሁድ ጀምሮ ተጠናክሮ እየተካሄደ መሆኑን የሶማሌ ክልል የፕሬዝዳንቱ የህግ አማካሪ ለኢሳት ገልጸዋል። የህግ አማካሪው አቶ ጀማል ዲሪዬ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጪ ሊወጣ ስለሚችል የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች አስቸኳይ መፍትሄ ማፈላለግ አለባቸው ብለዋል። በግጭቱ 17 ሰዎች መቁሰላቸውንም አቶ ጀማል ገልጸዋል። ጉዳዩን በተመለከተ ኢሳት ያነጋገራቸው ...

Read More »