የአሳይታ መምህራን ኮሌጅ ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ መቱ

(ኢሳት ዲሲ–ህዳር 5/2011) የአሳይታ መምህራን ኮሌጅ ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ መምታታቸው ተገለጸ።

ፋይል

በአፋር ክልል በህዝቡ የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማስቆም በክልሉ መንግስት እየተወሰደ ያለው አፈናና እስራት እስኪቆም ትምህርት እንደማይጀምሩ ተማሪዎች አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል በአፋር የሚካሄደው ተቃውሞ ቀጥሎ በዛሬው ዕለት ሎጊያ በተሰኘችው ከተማ ለውጥ እንፈልጋልን በሚል ተቃውሞ መካሄዱን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

በሳምንቱ መጨረሻም በተለያዩ የአፋር ከተሞች ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ መደረጉ ተገልጿል።