በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ግጭቶች ተቀሰቀሱ

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 12/2011) በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ግጭቶች መቀስቀሳቸው ተገለጸ።

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ዩኒቨርስቲ በተነሳው ግጭት ሶስት ሰዎች ተገድለዋል።

34 ሰዎችም ክፉኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በቴፒ ሳምንታት የዘለቀው ግጭት አሁንም አልበረደም።

በልዩ ሃይል በርካታ ሰዎች ተደብድበው ሆስፒታል ገብተዋል። በአፋርም የህዝብ ተቃውሞ ቀጥሏል።

በቢሾፍቱ ደብረዘይት ቄሮ ነን ባሉ ወጣቶች ሱቃችንን ልቀቁ እየተባልን ነው ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች መለስተኛ ግጭቶች መፈጠራቸውን የገለጸው ትምህርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ለማደናቀፍ የሚሰሩ ወገኖች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ዒላማ አድርገዋል ብሏል።