(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 5/2011) የሃይማኖት አባቶች ጎሰኝነትን ከማራገብ እንዲቆጠቡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ጥሪ አቀረቡ። ፕሬዝዳንቱ አቶ ለማ መገርሳ ከሃይማኖትአባቶችና ምሁራን የተውጣጣውን ስብስብ ባነጋገሩ ጊዜ በአንዳንድ አካባቢዎችመጽሀፍ ቅዱስ በአንድ እጃቸው በሌላኛው ደግሞ የጎሳ ፓለቲካን የሚያቀነቅኑ የሃይማኖት አባቶች ጉዳይ አስቸግሮናል ሲሉ ገልጸዋል። ሰላም እየታጣ ነው፣ ሀገራችን ውሎና አዳሯ እሳት ማጥፋት መሆኑ አሳሳቢ ነው ብለዋል ፕሬዝዳንት ለማ። የሃይማኖት አባቶቹ ትዕግስት አስፈላጊ ቢሆንም ሀገር ...
Read More »የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሰላምና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ጀመረች
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 5/2011)የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሃገሪቱ እየታየ ያለውን አለመረጋጋትና ግጭት ለማስቆም በሚል በመላ ኢትዮጵያ የሰላምና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ጀመረች። በመላ ሀገሪቱ 52 አህጉረ ስብከት የሚዳረሱበት ይህው የሰላምና የወንጌል ዘመቻ ለአንድ ወር የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል። ወደ ተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች የተሰማሩት የዘመቻው አባላት በ5 ቡድኖች የተከፈሉና እያንዳንዳቸው በሊቀጳጳስ የሚመሩ እንደሆነ ከቤተክህነት አካባቢ የተገኘ መረጃ ያመለክታል። ለዚህ ሃገር አቀፍ የሰላምና የወንጌል ዘመቻ ...
Read More »በአዲስ አበባ ከ2ሺህ በላይ ነዋሪዎች ቤተክርስቲያን መጠለላቸው ታወቀ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 4/2011) ከአዲስ አበባ በተለምዶ አጃምባ በሚባል አካባቢ ቤት ሰርተው ለዓመታት የቆዩ ከ2ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተፈናቅለው ቤተክርስቲያን መጠለላቸውን ገለጹ። ህገወጥ ናችሁ ተብለው በሌሊትበተኙበት በአፍራሽ ግብረሃይል ቤታቸው የፈረሰባቸው ተፈናቃዮች በፋኑዔል ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ተጠልለው መኖር ከጀመሩ 15ቀናትያለፋቸው መሆኑን ለኢሳት ገልጸዋል። በወቅቱ በድንገት በተወሰደው የማፍረስ ተግባር በተፈጠረ ግርግር በጥይትና በግፊያ 3 ሰዎች መሞታቸው ተመልክቷል። የከተማው አስተዳደር ምላሽ አልሰጠንም የሚሉት ተፈናቃዮቹ ህጻናትን ...
Read More »የማዕከላዊ አፍሪካ ሚኒስትር በጦር ወንጀል በቁጥጥር ስር ዋሉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 4/2011)የማዕከላዊ አፍሪካ ሚኒስትር የነበሩ የአፍሪካ እግር ኳስ ፌደሬሽን የኮሚቴ አባል በጦር ወንጀል በቁጥጥር ስር ዋሉ። ግለሰቡን የያዘችው ፈረንሳይ ስትሆንወደ አለም አቀፍ ፍርድ ቤት ዘሔግ እንደሚወሰዱም ተመልክቱል። ፓትሪስ ኤድዋርድ ናጊሶና የተባሉት የማዕከላዊ አፍሪካ የስፖርት ባለስልጣን በቁጥጥር ስር የዋሉት በሃገሪቱ ከ4 ዓመት በፊት በተካሄደ ሃይማኖት መሰረት ባደረገ ጥቃት ተዋናይ ሆነው በመገኘታቸው እንደሆነም ተዘግቧል። እንደ አውሮፓውያኑ በ1958 ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት የወጣችው ...
Read More »ማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ክፍል መዘጋቱ ተረጋገጠ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 4/2011) ማዕከላዊ በመባል የሚጠራው የወንጀል ምርመራ ክፍል መዘጋቱን አረጋግጬአለሁ ሲል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ። ኮሚቴው ማዕከላዊን ተዘዋውሮ ከጎበኘበኋላ በሰጠው መግለጫ ማዕከላዊ ተዘግቶ ክፍሎቹ ለቡራዩ ተፈናቃዮች በጊዜያዊ መኖሪያነት እያገለገሉ ነው ብሏል። የኮሚቴው አባላት አረጋገጥን እንዳሉትም በማዕከላዊ አንድም እስረኛ የለም። የነበሩት 139 እስረኞችም ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ማረሚያ ቤት በአደራ መሰጠታቸውን ተረድተናል ብለዋል ...
Read More »በኢትዮጵያ ምድር ተሳዳጅም አሳዳጅም ሊኖር አይገባም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 3/2011) በኢትዮጵያ ምድር ተሳዳጅም አሳዳጅም ሊኖር አይገባም ሁላችንም ተከባብረን መኖር ይገባናል ሲሉ ብጹእ አቡነ አብርሃም ጥሪ አቀረቡ። ቋንቋ ለመግባቢያ እንጂ ለመለያያ መሆንየለበትም ያሉት ብጹእ አቡነ አብርሃም ሰዎች በአደባባይ ተቀጥቅጠው የሚገደሉበትና በአደባባይ በሚሰቀሉበት ሁኔታ ኢትዮጵያ የሃይማኖትሃገር ነች ብሎ መናገሩም የሚያሸማቅቅ ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል። ዜጎች ከግብረገብ ድርጊቶች እንዳያፈነግጡም መክረዋል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የናህርዳር ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት ...
Read More »የተቃውሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ ተጠራ
(ኢሳት ዲሲ–በታህሳስ 3/2011) በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ለውጥ ለማደናቀፍ የተለያዩ ግጭቶችን እየፈጠሩ ያሉ አካላትን የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ ተጠራ። የፊታችን እሁድ የሚካሄደውን ሰልፍየአዲስ አበባ መስተዳድር እውቅና እንዲሰጠው አስተባባሪዎቹ ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም መስተዳድሩ ግን እውቅና እንዳልሰጠው አስታውቋል። ፋይል የታቀደው ሰልፍ በኢትዮጵያውያን የህሊና እስረኞች ላይ በህወሃት አገዛዝ ሰቆቃ የፈጸሙ ግለሰቦች ለፍርድ እንዲቀርቡ ይጠይቃል ተብሎ ይጠበቃል። በሃገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱት መፈናቀሎች እንዲቆሙና የለውጡን ሂደት ...
Read More »ዩ ኤስ አይ ዲ የሚያቀርበውን ድጋፍ ማቋረጡን አስታወቀ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 3/2011) የአሜሪካው የሰብዓዊ እርዳታ ተቋም ዩ ኤስ አይ ዲ በጌዲዮና ጉጂ አካባቢዎች ባገረሸው ውጥረት ምክንያት ለተፈናቃዮች የሚያቀርበውን ድጋፍ ማቋረጡን አስታወቀ። ካለፈው ሳምንት መጨረሻ አንስቶድርጅቱ የሚሰጠውን ድጋፍ ላልተወሰነ ጊዜ ማቆሙን ያስታወቀው የድርጅቱ ዳይሬክተር በአካባቢዎቹ ቆየተው ከተመለሱ በኋላ ነው። ፋይል የዩኤስ አይዲ ዳይሬክተር ሌስሊ ሪድ ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በጌዲዮና ጉጂ አካባቢዎች ዳግም የተፈጠረው አለመረጋጋት የድርጅቱን እንቅስቃሴ ...
Read More »በቤንሻንጉል የአማራ ተወላጆች በመስጊድ ውስጥ ተጠልለዋል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 3/2011) ቤንሻንጉል ጉምዝ ካማሼ ዞን ያሶ ወረዳ የተፈናቀሉ ከ900 በላይ የአማራ ተወላጆች በምስራቅ ወለጋ መስጊድ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ተገለጸ። ወደ አማራ ክልል በመጓዝ ላይየሚገኙት እነዚህ ተፈናቃዮች መንግስት ይድረስልን ሲሉ ጥሪ አድርገዋል። በምስራቅ ወለጋ አንገር ጉቴ ከተማ በሚገኝ መስጊድ ውስጥ የተሰባሰቡት ተፈናቃዮች ቁጥር በየዕለቱ በመጨመሩ ከፍተኛ ችግር እንደደረሰባቸው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ባለፈው ሳምንት ከካማሼ ዞን ያሶ ወረዳ የተፈናቀሉ 600 ...
Read More »የሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ስጋት ገብቶናል አሉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 3/2011)የሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የከተማዋ ጸጥታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ስጋት ገብቶናል ሲሉ ገለጹ። ኤጄቶ በሚል የሚንቀሳቀሱ የሲዳማወጣቶች ስም የተደራጁ ሃይሎች የአካባቢውን ነዋሪ እያዋከቡ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ምሬታቸውን ገልጸዋል። ኢሳት ያነጋገረውና ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ የኤጄቶ አባል አንዳንድ የሲዳማን ወጣቶች መልካም ስም ለማጉደፍ ተገቢ ያልሆነ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላት እንዳሉ ተናግሯል። ሰሞኑን በመኪና አደጋ ህይወታቸውን ያጡ 5 የሲዳማ ወጣቶችን ሃዘን ከመግለጽ ...
Read More »