(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/2011) በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ብር ጭኖ በሚጓዙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ተሽከርካሪዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ጨምሮ ሶስት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ። ባልታወቁ ታጣቂዎች በተፈጸመውጥቃት አንደኛው ተሽከርካሪ ሙሉ በሙሉ መውደሙን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ተሽከርካሪዎቹ 6 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ይዘው ሻኪሶ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ለማድረስ እያመሩ እንደነበረ ታውቋል። ሻኪሶ ከተማ ለመድረስ 20 ኪሎሜትር ሲቀራቸው ጥቃቱ ...
Read More »ከፊል አውቶማቲክ የሆኑ የጦር መሳሪያዎችን ግለሰቦችና የግል ኩባንያዎች እንዳይጠቅሙ ህግ ወጣ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2011) ከፊል አውቶማቲክ የሆኑ የጦር መሳሪያዎችን ግለሰቦችና የግል ኩባንያዎች እንዳይጠቅሙ የሚከለክል መመሪያ የአሜሪካ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አወጣ። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከመጋቢት23/2018 ጀምሮ መሳሪያዎቹን መጠቀም የተከለከለ በመሆኑ ግለሰቦችም ሆኑ አምራቾች እንዲያወድሙ አሊያም ለሚመለከተው አካል እንዲያስረክቡትላንት መመሪያ ወጥቷል። ከአውቶማቲክ መሳሪያዎች ውጭ ከፊል አውቶማቲክና አውቶማቲክ ያልሆኑ መሳሪያዎችን ገዝቶ መታጠቅ በማይፈቀድባት አሜሪካ የአሰቃቂ ግድያዎች እየጨመሩ መምጣት ብርቱ ተቃውሞን ሲያስከትል ቆይቷል። በተለይም ከአንድ ...
Read More »የፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የቀብር ስነስርአት ተፈጸመ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ10/2011) የቀድሞው የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የቀብር ስነስርአት ተፈጸመ። ለ12 አመታት በፕሬዝዳንትነት ያገለገሉት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ባለፈው ቅዳሜ በ94 አመታቸው ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተገኙበት በዛሬው ዕለት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን የቀብራቸው ስነስርአት ተፈጽሟል።
Read More »የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰጠው ብድር ከ550 ቢሊዮን ብር በለጠ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2011)የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመንግስትና ለግል ኩባንያዎች ያበደረው ብድር ከ550 ቢሊዮን ብር መብለጡ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምንጮችለኢሳት እንደገለጹት ትልቁን ብድር የወሰደው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ሲሆን የስኳር ኮርፖሬሽንና የባቡር ኮርፖሬሽንበተከታይነት ከፍተኛ ብድር መውሰዳቸው ተመልክቷል። ከ550 ቢሊዮን ብር ውስጥ 74 በመቶውን 6 የመንግስት ድርጅቶች የወሰዱ ሲሆን የዚህም ጠቅላላ ድምር 413 ቢሊዮን ብር ያህል እንደሆነም ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያሳያል። የብድሩ ...
Read More »በአማራ ክልል ሶስት ቀበሌዎች በቁጥጥሩ ስር ዋሉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2011) ከቅማንት የመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጥባቸው የቆዩ ሶስት ቀበሌዎችን በቁጥጥሩ ስር ማዋሉንየአማራ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። ላለፉት ሶስት ዓመታት ከክልሉ መንግስት ቁጥጥር ውጪ ሆነው በቆዩት ጉባይ ጀጀቢት፣ሌንጫና መቃ በተሰኙ ቀበሌዎች የቅማንትን ጥያቄ በጉልበት ለመፍታት በሚፈልግ ሃይል አማካኘነት የተደራጀ ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጥባቸው መቆየቱን የኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቀዋል። የአማራ ክልል የሰላምና ደህንነት ቢሮ ሃላፊ ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ...
Read More »በቤንሻንጉል 10 ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2011)በቤንሻንጉል መንገደኞችን አሳፍሮ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ የቦምብ ጥቃት 10 ሰዎች ተገደሉ። መንገድላይ የተቀበረው ቦምብ ፈንድቶ በርካታ ሰዎች ሰዎች መቁሰላቸውም ተነግሯል። ቦምቡን ያጠመደው አካል ማን እንደሆነ አለመታወቁን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። የቤንሻንጉል ፖሊስ ኮሚሽነር ሰይፈዲን ሐሩን እንደገለጹት ከአሶሳ ከተማ ወደ ቶንጎ ሲጓዝ በነበረ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ የተጠመደ ቦምብ ጥቃት አድርሶ ከ10 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ...
Read More »በሞያሌ ከ80ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተፈናቀሉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2011) በሞያሌ ካለፈው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ እንደአዲስ ባገረሸው ግጭት ከ80ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ። በግጭቱ የተፈናቀሉት አብዛኞቹነዋሪዎች በአቅራቢያ ባሉ ወረዳዎች ተጠልለው እንደሚገኙ ነው ለማወቅ የተቻለው። አንደኛ ሳምንቱን የደፈነው ግጭት ከትላንት ጀምሮ ጋብ ያለ ቢመስልም የተኩስ ድምጽ በከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች እንዳለ ተገልጿል። በሞያሌ ከህክምና መስጪያ ማዕከላት ውጪ የከተማዋ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ መቆሙንም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የቦረና ዞን የመንግስት ...
Read More »አሜሪካ በደቡብ ሱዳን በሶስት ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ ጣለች
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/2011) አሜሪካ በደቡብ ሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት እጃቸውን አስገብተዋል ያለቻቸውን የእስራኤል የጦር ጄኔራል ጨምሮ በሶስት ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ ጣለች። ሁለቱ የደቡብ ሱዳን ዜጎች መሆናቸውምታውቋል። በደቡብ ሱዳን ግጭት ውስጥ እጃቸውን በማስገባትና ቀውሱን በማባባስ በሃገሪቱ ለተከሰተው ለ400 ሺህ ሰዎች ዕልቂት አስተዋጽኦ አድርገዋል የተባሉትን እስራኤላዊ ጡረተኛ ጄኔራል እስራኤል ዚቭ ሶስት ኩባንያዎች ላይም የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ማዕቀብ መጣሉን ኢየሩሳሌም ፖስት ዘግቧል። እስራኤል ...
Read More »በሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ላይ የተገኙ አዳዲስ መረጃዎች ይፋ ሆኑ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/ 2011) መርማሪ ፖሊስ በሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ላይ የተገኙ አዳዲስ ተሳትፎዎችን ይፋ አደረገ። በቀድሞው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ላይ በምርመራ ወቅት ያገኛቸውን አዲስ የወንጀል ተሳትፎዎች ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል። መርማሪ ፖሊስ እንደገለጸው ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ከሕዳሴው ግድብ እና ከልዩ ልዩ ዓለምአቀፍና የሀገር ውስጥ ተቋማት ጋር ያደረጓቸው ውሎች እንዲሁም የተከፈሉ ገንዘቦች ...
Read More »ሶስት ሃገራት የዲሞክራሲ ርምጃ አሳይተዋል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 09/2011) በዓለማችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ሶስት ሃገራት በ2018 የዲሞክራሲ ርምጃ ማሳየታቸውን ዋሽንግተን ፖስት ዘገበ። ለዲሞክራሲ እጅግ ፈታኝና አደገኛበሆነውና አምባገነኖች ይበልጥ አፋኝ ሆነው በወጡበት በዚህ ዓመት በኢትዮጵያ እጅግ አስደናቂ ሁኔታ ተከስቷል ስትል በዋሽንግተንፖስት ላይ ጽሁፏን ያቀረበችው ፍረዳ ጊቲስ በትግራይ የበላይነት ስር የቆየው ዘረፋና ስርዓት በዚህ ዓመት ማብቃቱን አመልክታለች። የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣት በውጭም ሆነ በሃገር ውስጥ በሚኖሩ ...
Read More »