የፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የቀብር ስነስርአት ተፈጸመ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ10/2011) የቀድሞው የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የቀብር ስነስርአት ተፈጸመ።

          ለ12 አመታት በፕሬዝዳንትነት ያገለገሉት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ባለፈው ቅዳሜ በ94 አመታቸው ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

          ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተገኙበት በዛሬው ዕለት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን የቀብራቸው ስነስርአት ተፈጽሟል።